TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች። ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች። የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦ - ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024…
#ሀርጌሳ

" ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንቱ " ሀገራችንን አልሸጥንም " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር #በሊዝ ነው የምትከራየው " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠትም ተስማምታለች " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መቼ እንደሆነ ቀኑን በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት #በቅርቡ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደሚሰጥ በድጋሚ ለህዝባቸው ገልጸዋል።

" ይህ የሶማሌላንድ ህዝብ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የደረሰበት ትልቅ ስኬት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱም ወገን በኩል ፍላጎትና ጥቅማቸውን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሌላንድን እንደ ራሷ አንድ ግዛት የምትቆጥራትና የተፈረመው ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል በሚል የተቃወመችው ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፎች ሲደረጉ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ (ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 206 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል። አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች። የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር…
#Update

" የቀን ህልም ነው ... ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " - ሶማሌላንድ

" የሶማሊያ መንግሥት አንዳች ስልጣን የለውም " - ፑንትላንድ

#ፑንትላንድ እና #ሶማሌላንድ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ።

የሶማሊያ መንግሥት ፤ #ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት በማድረግና " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እየገባሽ ነው " በማለት ሞቃዲሹ ያሉት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ከዚህ ባለፈ ግን በሶማሌላድ ፣ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ፣ #ጋሮዌ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች በ7 ቀን እንዲዘጉ አስጠንቅቋል። ኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችም በ1 ሳምንት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ አዟል። ካልሆነ ወደሌላ እርምጃ ገባለሁ ብሏል።

ለዚህ ማስጠንቀቂያ ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊያ ፌዴራል መንግስትን ማስጠንቀቂያም ውድቅ አድርገዋል።

ዛሬ ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ሶማሊኛ ክፍል አጭር ቃላቸውን የሰጡት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር አምባሳደር ሮዳ ጃማ ፥ " የቀን ህልም ነው፤ ...ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " ሲሉ ማስጠንቀቂያውን አጣጥለዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ስልጣኑ በቪላ ሱማሊያ እና በሙቃዲሾ ዘሌን ቤዝ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ " በውስጥ ጉዳዩ ላይ ቢያተኩር ነው የሚሻለው ... ከአቅሙ በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑን ማቆም አለበት " ብለዋል።

የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ድሪር  በበኩላቸው " የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የመዝጋት አንዳችም ስልጣን የለውም " ብለዋል።

@tikvahethiopia