TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
107 ፓርቲዎች

#በፖለቲካ_ፓርቲዎች መካከል የሚኖርን ግንኙነት እንዲሁም በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሰራር ስርአት የቃል ኪዳን ሰነድ ዛሬ በፖለቲካ ፓርቲዎች በፊርማቸው አረጋግጠዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ለ2 ጊዜ ያክል ተወያይተው እንደነበር ይታወሳል። የቃል ኪዳን ሰነዱ 20 አንቀፆች እንዳሉት ተገልጿል።

ፎቶ፦ ጃዋር መሀመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከሰሞኑን የፌዴራሉ መንግስት የ #ሰላም_ስምምነቱን በተመለከተ ከ50 በላይ ለማሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር። ማብራሪያውን ከሰጡት መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ነበሩ። በወቅቱ ፤ የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አቅርበው ነበር። ምን ተጠየቀ ? ምንስ…
የወልቃይት ጉዳይ ...

" ለወልቃይት የአማራ ማንነት " መከበር የሚታገለው የልሳነ ግፉአን ድርጅት  የወልቃይት ችግር በፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅጣጫ፣ በሪፈረንደምም ሆነ በድርድር ሳይሆን በፖለቲካ ውሳኔ ነው የሚፈታው ብሏል።

ከሰሞነኛው የወልቃይት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የድርጅቱ ፕሬዜዳንት አቶ ዓብዩ በለው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ወቅት ጋዜጣው የወልቃይት ጉዳይ የፌዴሬሽን ም/ቤት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ እንደሚፈታ መንግሥት በቅርቡ ግልጽ ማድረጉን አስታውሶ ለምን ድርጅታቸው ምክር ቤቱ መፍትሄ አይሆንም እንደሚል ተጠይቀው አብራርተዋል።

(የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በቅርቡ የተናገሩትን በዚህ ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/75534 )

የድርጅቱ ፕሬዜዳንት አቶ ዓብዩ በለው ፦

" በቅርቡ  የጠቅላይ ሚኒስትሩ  የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) የተናገሩትን ማንሳት ይኖርብናል፡፡  ሕወሓት በጉልበት ወልቃይትን መውሰዱን ሬድዋን (አምባሳደር) በግልጽ አውስተዋል፡፡

ሕወሓት በጉልበት መሬቱን ሲወስድ ደግሞ ዝም ብሎ ሳይሆን ብዙ ግፍ ፈጽሞ መውሰዱን እኛ እናውቃለን፡፡ እኛ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዚያ አካባቢ ተፈጽሟል ነው የምንለው፡፡

ሕወሓት የወሰደውን መሬት፣ እንዲሁም የጨፈለቀውን ማንነት ሕጋዊ ለማድረግ ይጠቅመኛል ብሎ የራሱን ሕገ መንግሥት አውጥቷል፡፡

ሕወሓት ለራሱ ብሎ ባወጣው ሕገ መንግሥት ደግሞ የወልቃይት ችግርን ለመፍታት አይቻልም፡፡ ይህ ምናልባትም አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንደሚባለው ነው የሚሆነው፡፡

ሕወሓት ጉዳዩን ለማወሳሰብ ብሎ በፈጠረው አካሄድ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ የወልቃይት ጉዳይ ቅሚያ ነው፡፡ በጉልበት መወሰዱን የመንግሥት ኃላፊዎች አምነውታል፡፡ ስለዚህ #በጉልበት የተወሰደውን ወደ ነበረበት መመለስ ነው መፍትሔው፡፡  

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ችግሩን ይፍታው ማለት ችግሩን ያወሳስባል፡፡ አንደኛ ጉዳዩ የተፈጠረው የፌዴሬሽን ም/ቤት በሌለበት ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ሆነ ፌዴሬሽን ምክር ከመቋቋማቸው በፊት ነው በጉልበት የተወሰደው፡፡

ሕግ ደግሞ ወደኋላ ተመልሶ ባልነበረበት ቦታ የሆነ ችግርን አይፈታም፡፡  የፌዴሬሽን ም/ቤት ችግሩን ያወሳስበዋል እንጂ ይፈታዋል ብለን አናምንም፡፡

ምናልባትም እነሱ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና አሠራሩን እንዲሻሻል አድርገው ችግሩን ለመፍታት የተሻለ መፍትሔ ይዘው ከቀረቡ እኛ አናውቅም፡፡

በእኛ እምነት ግን ወልቃይት በወረራና በጉልበት ነው የተወሰደው፡፡ ችግሩ መፈታት ያለበትም #በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ነበረበት በመመለስ ነው፡፡

የተቀማን ማንነት  ፣ የተጨፈለቀን ማንነት ዕውቅና ሰጥቶ መመለስ ነው፡፡

የወልቃይት ጉዳይ የፍትሕ ጉዳይ ነው፡፡  ይህን የፍትሕ ጥያቄ አሳንሶ የድንበር ጉዳይ ማድረግ፣ የ2 ክልሎች ግጭት ማድረግ ተገቢነት አይኖረውም፡፡

ብዙ ጭፍጨፋ እና ዕልቂት የተፈጠረበትን #የፍትሕ ጉዳይ የሁለት ክልሎች ወሰን ወይም መሬት ግጭት አድርጎ ማየት ችግሩን ማቅለል ነው፡፡

ችግሩን አሳንሶ ወይም በተዛባ መንገድ መመልከት ደግሞ የችግሩን አፈታትም ያወሳስበዋል፣ እንዲሁም ያከብደዋል ብለን እናምናለን፡፡ "

ሙሉ ቃለምልልስ ፦ https://telegra.ph/Ethiopian-Reporter-01-08-2

Credit : www.ethiopianreporter.com

@tikvahethiopia