TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

" በ9 ወር 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 261 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል " - የትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ

የትግራይ የትራንስፓርትና የመገናኛ ቢሮ ከሰሞኑን አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

በዚህም በክልሉ ባለፉት 9 ወራት (ከመስከረም እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም) በትራፊክ አደጋ ምክንያት ብቻ 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

261 ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በንብረት ላይ የደረሰ ውድመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል።

በጥናት የተለየው የትራፊክ አደጋ መነሻ ምንድን ነው ?
- ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ መንዳት
- ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት
- ከተፈቀደ መስመር ውጪ ማሽከርከር
- ርቀት ጠብቆ አለማሽከርከር
- የአሽከርካሪዎች አቅም ማነስ ናቸው።

እግረኞች ዜብራ ተጠቀመው መንገድ አለማቋረጥ እና ቀኝ መስመር ይዘው መጓዝ በተጨማሪነት የአደጋ መነሻዎች ሆነው ተጠቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "

" የአንድ ዓመት ውዙፍ ደመወዝ አልተከፈለንም "  ያሉ የቀድሞ የትግራይ ኃይል አባላት ድምጻቸውን ለማሰማት ሰልፍ ወጡ።

የቀድሞ አባላቱ ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ አካሂደዋል።

በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- " የሰማእታት ቃል የሚከበረው የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው በማገዝ ነው ! "
- " መስዋእት ስለከፍልንና ከሰራዊት ስለተሰናበትን ደመወዛችን ማጣት አይገባንም ! "
- " ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "
- " ፍትህ ይሰጠን ! "
- " መብታችን ይከበርልን ! "
- " ድምፃችን ይሰማ ! " የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አስምተዋል። 

ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንዱ የሆነው ፀጋይ ገ/ስላሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጀምሮ ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችን አቅርበን የተሰጠን ምላሽ የለም " ብሏል።

" ፍትሃዊ ጥያቄያችን እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ ሳንታክት እንጠይቃለን " ሲል አክሏል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ለማቀረብ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ያመሩ ሲሆን በስብሰባ ምክንያት ጥያቄያቸውን ሰምቶ ያስተናገዳቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ትግራይ

ባለፉት 3 ወራት በዘራፊዎች ጥቃት ለደረሰባቸው 482 ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱን መቐለ የሚገኘው የዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አስታወቀ።

በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ብርሃነ ገ/ሚካኤል ለትግራይ ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ ከሚያዝያ እሰከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ባሉት ወራት በቢላዋ ሌሎች መሳሪዎች በዘራፊዎች ጥቃት የደረሰባቸው 482 ሰዎች በሆስፒታሉ የድንገተኛ የህክምና ክፍል ታክመዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች የ9 ዓመት ዕድሜ ካለው ህፃን አስከ የ70 አመት አዛውንት የሚያካትት እንደሆነ  ተናግረዋል።

ከነዚሁ ተጠቂዎች 69ኙ ሴቶች ናቸው።

የሆስፒታሉ የህክምና ተገልጋዮች የመቀበያ ሰነድ እንደሚያመላክተው፦

- በሚያዝያ 183 ሰዎች
- በግንቦት 136 ሰዎች
- በሰኔ 163 ሰዎች በዘራፊዎች ጥቃት ደርሶባቸው ታክመዋል።

ሆስፒታሉ ያለው ውስን የመድሃኒት ፣ የህክምና ቁሳቁስና ባለሙያ ለእርጉዝና የሚወልዱ እናቶች እንዲሁም ለሌሎች የቆየ ህመም ላለባቸው ተገልጋዮች የቅድምያ አገልግሎት ከመስጠት ፈንታ የዘራፊዎች የጥቃት ሰለባዎች ለሆኑ ድንገተኛ ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት በመስጠት መጠመዱ ሌላ ጫና እንደፈጠረበት ተገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#TigrayRadio

@tikvahethiopia            
" ከ2013 ዓ/ም በፊት በአከባቢው ሰላም እና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ " - ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " ለአመታት ከቄያቸው ተፈናቅለው በትግራይ የተለያዩ ከተሞች እና በሱዳን የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ወደ አከባቢያቸው ለመመለስ የተያዘው የጋራ እቅድ የዘገየው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተፈጠረ ችግር አይደለም " ብለዋል።

" የነበረ ክፍተት ተገምግሞ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ም/ፕሬዜዳንቱ ፥ " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ አከባቢያቸው የመመለስ ስራ የራያ እና ፀለምቲ ተፈናቃዮች በመመልስ የተገኘው ልምድ መስረት በማድረግ ይፈጸማል " ብለዋል። 

" ተፈናቃዮችን የመመለስ ተግባሩን የሚያቆም አካል የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የምዕራብ ትግራይ የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ ያለመ የሰፈራ ስራ በአማራ መንግስት ተካሂደዋል " ያሉት ሌ/ጀነራሉ " ከሌሎች አከባቢዎች ወደ ምዕራብ ትግራይ ገብተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ታጣቂዎች እንዲወጡ ይሰራል " ብለዋል።

" ከ2013 ዓ.ም በፊት በአከባቢው ሰላምና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ "  በማለትም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ቀላል እና ከባድ ወንጀሎች በመፈፀም ላይ እንዳሉ ተናግረው በአጭር ጊዜ ወንጀል ፈጻሚዎችን ወደ ተጠያቂነት ለመሸጋገር የሚስችል ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል።

በከባባድ ወንጀል በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አመልክተዋል።

እነማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ? የሚለውን በዝርዝር አልተናግሩም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Mekelle

መቐለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 14 የመኪና የማደሪያ ቦታዎች (ፓርክ የሚደረግበት) 140 ባለቤትነታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ማግኘቱ የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ በመቐለ ከተማ የመኪና ማደሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ አድርጎ ነበር።

በዚህም140 ባለቤታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ሊገኙ እንደቻሉ ገልጿል።

የተገኙት ተሽከርካሪዎች ባለቤትነታቸው ለማወቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

" ባለንብረት ነኝ " የሚል አካል ማረጋገጫ ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይችላል ተብሏል።

የመቐለ ፓሊስ ከተሽከርካሪ ፣ ብረታብረትና ሌሎች ንብረቶች ጋር ተያይዞ የማጣራት ስራ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

የሚካሄደው ምርመራ ግኝቶች በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሐምሌ 4 ባወጣው መግለጫ በክልሉ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ መግለፁ መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
#Tigray #TPLF

" ' አቶ ጌታቸው ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " - የስብሰባው ተሳታፊ

ከሰሞኑን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስብሰባ ላይ ነበር የከረመው።

ስብሰባው 11 ቀናትን የፈጀ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አበላት ከድርጅቱ የከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ሰብሰባ መቅረታቸውን ከአንድ የስብሰበው ተሳታፊ መስማት ችሏል።

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ተሳታፊ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ በስብሰባው የመጨረሻ ሁለት ቀናት ያልተገኙት ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ
- የማእከላይ ኮሚቴ አባልና የትእምት ዋና ስራ አስፈፃሚ በየነ ምክሩ
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራርና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት
- የክልሉ የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ሃላፊና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ነጋ ኣሰፋ 
- የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ብርሃነ ገብረየሱስ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ' ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " ያሉት እኚህ የመረጃ ምንጭ ፥ " ፕሬዜዳንቱ በፍቃድ ምክንያት ሀምሌ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ከሰአት በኋላ ያልተገኙ ሲሆን ሀምሌ 8 እና 9/2016 ዓ/ም ያልፍቃድ መቅረታቸው በስብሰባው ታውጇል " ብለዋል።

" የተቀሩት 4 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ጊዚያት በየግላቸው ከስብሰባው እንደወጡ አለመመለሳቸው ለተሰብሳቢው ተነግሮታል "  ሲሉ አክለዋል።

ከሰኔ 26 አስከ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ለ11 ቀናት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ያካሄደው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ 14ኛው ጉባኤ በተያዘው የሀምሌ ወር 2016 እንደሚካሄድ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Tigray

" ለረጅም ግዜ ታግሰናል። ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በህግና ስርዓት መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ቢሮ   

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ፤ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

" በአሁኑ ሰዓት የክልሉ የፀጥታ ሃይል በተናበበና በተቀናጀ  አኳሃን በመስራት በቅርቡ ከሌላው ጊዜ የተሻለ የፀጥታ ሁኔታ እንዲኖር በመስራት ላይ እንገኛለን " ብሏል።

የህግ ልዕልና ማረጋገጥ እንዳለ ሆኖ በተለይ  ከብረታ ብረት ስርቆት ጋር ተያይዞ የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደ መነሻ በመውሰድ በወርቅ ፣ ማዕድንና መሬት ዘረፋና እገታ እንዲሁም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ስርዓት የማስያዝ ስራዎችና እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል።

" የተጀመረው ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ ያስደነገጣቸው ህገ-ወጥ  አካላት ጉዳዩ ፓለቲካዊ መልክ ሊያስይዙት እየሞከሩ ነው " ያለው ቢሮው " በማህበራዊ የትስስር ገፆች በሚነዛው በሬ ወለደ ውዥንብር ሳንደናገጥ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲል አሳውቋል።

" ለረጅም ግዜ ታግሰናል ፤ ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በህግና ስርዓት መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን " ሲል አረጋግጧል።

እስካሁን በተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባሮች ተሳተፉ  ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

እነማን እንደሆኑ በስም የተጠቀሰ ነገር የለም።

ሳምንቱን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ከትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን 3 ከፍተኛ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተው በሌሎች መተካታቸው ሲዘዋወር ነበር።

ከብረታ ብረት ስርቆትና ሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ጋር በተያያዘም በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ቢነገርም መረጃውን የጊዚያዊ አስተዳደሩና የፀጥታና ሰላም ቢሮ ማረጋገጫ ሊሰጥበት አልቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " ' አቶ ጌታቸው ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " - የስብሰባው ተሳታፊ ከሰሞኑን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስብሰባ ላይ ነበር የከረመው። ስብሰባው 11 ቀናትን የፈጀ ነበር። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አበላት ከድርጅቱ የከፍተኛ…
#TPLF

" ህወሓት በሁለት ኔትወርክ ተከፍሎ እየታመሰ ነው " - የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበር ተክለብርሃን ኣርአያ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለ11 ቀናት ያካሄደው ዝግ ሰብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣትና በያዝነው ወርሃ ሀምሌ ጉባኤ ለማካሄድ ወስኖ ማጠናቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።

ህወሓት ዝግ ስብሰባው በማስመልከት የድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበር ተክለብርሃን ኣርአያ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለ-መጠይቅ አካሄደዋል።

ሊቀመንበሩ በቃለ-መጠይቃቸው ምን አሉ ?

ስብሰባውና ግምገማው ከመጀመሪያው በውጭ የተጠናቀቀ መጠላለፍ እና ተንኮል ያየለበት እንደነበር ጠቁመዋል።

" የአመራር አንድነት አልነበረም " ሲሉ ገልጸዋል።

ስብሰባውና ገምገማው በሁለት ኔትወርክ የተከፈለ እንደነበረ ገልጸውል።

" በሰብሰባው የመናገር አድል ያገኘው ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አድሉ ተነፍጎታል " በማለት አብራርተዋል።  

፣ የመናገር እድል ያገኙ ደጋፊዎች ለአንድ ወይም ለግማሽ ሰአት ብቻቸው በመናገር የሰብሰባ ጊዜ ሲያባክኑ ታይተዋል " ያሉት ተክለብርሃን " ስብሰባውና ገምገማው ነፃና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም " ሲሉ ተናግረዋል።

አመራሩ በኔትወርክ እየታመሰ ነው ሲሉም አክለዋል።

" የተፈጠረው ችግር ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ በህወሓት ውስጥ ሁለት ኔትወርክ መኖሩ አረጋግጧል " የሚሉት ሊቀመንበሩ  " ኔትወርኩ ሳይበጣጠስ የአመራር አንድነት አይረጋገጥም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስብሰባውና ገምገማው አሰልቺ ከመሆኑ የተነሳ ' ተሰበሰብኩ አልተሰበሰብኩ ለውጥ የለውም ' በማለት መድረኩ ረግጠው የወጡ አመራር አሉ " ብለው ፣ ግምገማው የሚፈለገውን ፍሬ አላፈራም "  በማለት ጨምረዋል።  

" ድርጅቱ ጉባኤውን እንዲያካሂድ እንደግፋለን ቢሆንም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንጂ አሁን ባለበት አፋኝ አካሄድ መሆን የለበትም " ሲሉ የመፍትሄ ሃሳብ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።  በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር…
#Tigray #TPLF

" እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ እና ህልውና ያዳነና ያስቀጠለ ነው።

- ሁሉም የትግራይ ችግሮች ከውጭ ተፅእኖ ነፃ ናቸው ባይባልም በአመዛኝ ውስጣዊ ፓለቲካዊ ችግሮች ናቸው ያሉት። ውስጣዊ ችግሮቻችን ባይጠልፉን የፕሪቶሪያው ስምምነት በፈጠረው እድል በርካታ ለውጦች ይታዩ ነበር።

- ውስጣዊ ፓለቲካዊ ድክመታችን ሰከን ብለን መመርመር አለብን፤ ከጥፋት ለጥቂት ያመለጠ ህዝብ መልሰን ወደ ጦርነት እንዳናስገባው በሃላፊነት መንፈስ መንቀሳቀስ አለብን።

- ጉባኤ መካሄድ የለበትም ያለ የለም ፤ አሁን ያለው ሩጫ ግን ስልጣን ለመቆጣጠርና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያለመ ነው።

- ህወሓት መዳን የሚችለው በጭቅጭቅ ሳይሆን በሳልና ተራማጅ ሃሳብ በማመንጨት ነው።

- እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30/2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር ቢሆንም ፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አስቀርቶታል። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?

- " ከፌደራል መንግስት ጥሩ መግባባት ደርሰናል ተስማምተናል " ይባላል እንጂ መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር የለም። አዲስ አበባ በመሄድ የሚስማሙትና እዚህ የሚነገረን የተለያየ ነው፤ ይህ ካድሬው ሊያውቀው ይገባል።

- የተጀመረው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ተግባር ከተጨማሪ ግጭት ቂምና ቁርሾ በፀዳ መልኩ እንዲፈፀም እየሰራን ነው።

- በእርስ በርስ ሽኩቻ ባሳለፍናቸው ጊዚያቶች ፀፀት ተስምቶን ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስና የፕሪቶሪያው ስምምነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፀም በተቀናጀ የአመራር ጥበብ መስራት ይጠበቅብናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።

ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።

ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia