TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OSA #ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ #BBC👇
https://telegra.ph/OSA-07-28
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ #በ2012 የተመደበው #በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ተኛ አመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባኤውን የከተማ አስተዳደሩን የ2012 በጀት በማጽደቅ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2012 በጀት አመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች ለሚቀርፉ ፤ነዋሪዎቿን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ለተባሉ እንዲሁም አንገብጋቢ ለተባሉ የልማት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ በጀት ምደባ ነው ተብሏል፡፡

በጀት ከመመደብ ባለፈ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጀቱን አዋጪ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የአስፈፃሚ ተቋማትን አቅምና አደረጃጃት የማስተካከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የተመደበው በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ "በያገባኛል ይመለከተኛል" የገቢ ማሰባሰቢያ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

"ከ6 ወር በላይ በመዲናዋ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬት ይወረሳል" - ኢንጂነር ታከለ ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ ከስድስት ወር በላይ መሬት አጥረው የሚያስቀምጡ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግስታት መሬት እንደሚወረስ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ በዘጠኝ ክፍለ ከተማዎች የሚገነቡ ከ20 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከስድስት ወር በላይ በከተማዋ ያለምን ግንባታ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬቱ እንደሚወረስበት ማረጋገጥ አፈልጋሉ ብለዋል።

ሀብት የሚባክንበት ወቅት አልፏል ያሉት ምክትል ከንቲባው፥ በእያንዳንዱ ቦታ በመንግስት እና በባለህብቶች ግንባታ ሳይካሄድባቸው ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች በጥናት ተለይተዋል ብለዋል። በመሆኑም ግንባታ ሳይካሄድባቸው የሚገኘት እነዚህ መሬቶች በቅርቡ ወደ መሬት ባንክ ይመለሳሉ ብለዋል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia