TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አስተያየት ከሰዓታት በፊት የዶክተር አብይ አህመድ መግለጫ እና ማብራሪያ ለምን በቀጥታ አልተላለፈም? በሚል እንደድሮው ሊቆርጡ ነው? አብይ በራሱ አይተማመንም! አብይ..ውሸታም ነው!እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብለው አንዳንድ ሰዎች በፌስቡክ የተሰጡ አስተያየቶችን አቅርቤ ነበር።

ይህን ያደረኩት መማሪያ እንዲሆነን ነው። ሌላ ጊዜ ስለ አንድ ነገር #በቂ መረጃ ሳይኖረን በጥርጣሬ ብቻ ስለ አንድ ነገር ከማውራት ልንቆጠብ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ‼️

የኢትዮጵያ መንግስት፣ በሠብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት የሚታሰሩበት አዲስ «ከተማ» (እስር ቤት) መገንባት እንደሚያስፈልገዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐስታወቁ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደነገሩት ኢትዮጵያ ያሏት እስር ቤቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን «ወንጀለኞች» ለማሠር #በቂ አይደሉም።

አሶሺየትድ ፕሬዝ የዜና ምንጭ (AP) የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ጠቅሶ እንደዘገበዉ መንግሥታቸዉ ያተኮረዉ ዋና ዋና በሚባሉ ጉዳዮች (ወንጀሎች) ላይ ብቻ ነዉ። «የተቀሩትን በመመሥረት ላይ ለሚገኘዉ ለእርቅ ኮሚሽን ትተነዋል»ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዳስታወቀዉ በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ 63 የቀድሞ የመረጃ (የስለላ) እና የጦር መኮንንኖች ታስረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በገና በዓል #የኃይል_መቆራረጥ ችግር እንዳይኖር #በቂ ዝግጅት መደረጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በበዓሉ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ሊከሰት ስለሚችል ከምግብ ፋብሪካዎች ውጪ የከፍተኛና የመካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ኃይል ቀንሰው እንዲጠቀሙ አገልግሎቱ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

" ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና የምንገለገልባቸው አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው " - አቤኔዘር እጸድንግል (ዶ/ር)

የአምቡላንሶች ቁጥር በጦርነቱ ወቅት መመናመንና፣ ደመወዝ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሙያዎች ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ፈተና እንደሆነበት የትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጤና ቢሮው የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤኔዘር እጸድንግል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

- የድንገተኛ ሕክምና ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ችግር ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ የወላድ እናቶች በቂ አገልግሎት ሲሰጥ አልነበረም። ዋነኛው፣ አንደኛውና ቀደኛ ምክንያቱ የአምቡላንስ እጥረት ችግር ነው። ያለ አምቡላንሶች ድንገተኛ ሕክምና የለም።

- ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድገተኛ ሕክምና የምንገለገልባቸው፤ አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው። በጣም ጥቂት አምቡላንሶች ናቸው የቀሩን።

- በአስተዳደራዊ፣ በነዳጂ፣ በበጀት ችግሮችና በተለያዩ ምክንያቶች 90ዎቹ አምቡላንሶችም ራሱ ለሁሉም አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

- ኅብረተሰቡ ሊያገኝ የሚገባው አገልግሎት እጅግ በጣም ቀንሶ ነው ያለው። ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ  በኳርተር ኦልሞስት እስከ #500,000 የሚጠጉ ድገተኛ ታካሚዎች ናቸው የነበሩን፤ አሁን በተመሳሳይ ወቅት ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ድንገተኞች #40,000ም አይሞሉም። በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ታካሚው ቀንሷል።

- የጤና ባለሙያዎችም ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት ላይ ፈተና ሆኗል።

- የጤና ባለሞያዎቹ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሲሉ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማለትም ወደ መሀል አገር ይሰደዳሉ ፤ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ #በጀት ስለሌለ #በቂ ደመወዝ ስለማያገኙ ነው።

* ይህ ሁሉ ተደማምሮ የአገልግሎት ጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ አድርጓል። ለቀጣይ ይሻሻላል፣ ለመሻሻልም ጊዜያዊው መግሥትም ብዙ እየሰራ ነው።

የአምቡላንሶቹ ቁጥር የቀነሰው በጦርነቱ ወቅት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቤኔዘር (ዶ/ር) ፦

" አዎ በጦርነቱ ወቅት በርከት ያሉ አምቡላንሶች ተወስድልውብናል። በርከት ያሉ ደግሞ ተቃጥለዋል። በእኛ እጅ ያሉት 90 ብቻ ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት ከ80 በላይ የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ውድመት ተከትሎ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ የተሻለ ቢሆንም የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተኝ ችግሮች ማጋጠማቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

መረጃው አዘጋጅቶ ያቀረበው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia