TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የፖሊስ_ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በትራፊክ መብራቶች  እና በመስቀለኛ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድ እና የልመና ተግባራት ላይ በተሰማሩ ግለሰቦችና #ገንዘብ_በሚሰጡና በሚገበያዩ አሽከርካሪዎች ላይ በህጉ መሰረት ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ።

በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሚሰጡ እና ግብይት የሚፈፅሙ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

በሚኒስትሮች ም/ቤት የወጣው የትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 #በትራፊክ_መብራት ላይ ወይም #በመስቀለኛ_መንገድ ላይ በልመና ተግባር ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት የፈፀመ አሽከርካሪ ቅጣት እንደሚጣልበት ይደነግጋል፡፡

" ይሁን እንጂ #የአሽከርካሪዎች ደንብ አክባሪ አለመሆን በእነዚህ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድና የልመና ተግባራት እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።

የትራፊክ ደንቡ አለመከበር #ለትራፊክ_አደጋ መጨመር እና ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዳይኖር እንቅፋት ከመፍጠሩ ባሻገር በተለይ የትራፊክ መብራቶች ባሉባቸው ጎዳናዎች የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የሚፈፀምባቸው ቦታዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Addis-Ababa-Police-01-04

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ዙሪያ ቤቶች እየፈረሰባቸው እንደሆነ ከሚገለፅባቸው አካባቢዎች አንዱ ወደ ዓለም ባንክ ሲሆን ቤታቸው የፈረሰባቸው በአንድ ስፍራ ላይ ተሰብሰበዋል።

በርካታ ቤቶችም እንደሚፈርሱ የሚገልፅ ምልክት መደረጉ ተሰምቷል።

መንግስት እርምጃውን እየወሰደ ያለው ህገወጥ ቤቶች ናቸው በሚል እንደሆነ ተነግሯል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያነጋገሯቸው ነዋሪዎች እየተወሰደ ባለው እርምጃ የሰው ህይወት መጥፋቱንም አመልክተዋል።

በአካባቢው በርካታ አመታትን የኖሩ ዜጎች (እናቶች ፣ ህፃትናት ፣ አዛውንቶች) ቤታቸው ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ ብርድና ፀሀይ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ ፤ መፍትሄ እንዲፈልግላቸውም ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ዙሪያ ፤ ቤቶችን የማፍረስ እንቅስቃሴ ካለባቸው አካባቢዎች መካከል " አለም ገና ዳለቲ " ተጠቃሽ ነው።

ከላይ በአፋን ኦሮሞ የተያያዘው መልዕክት ከሰሞኑን አለም ገና ዳለቲ የተላለፈ ሲሆን መልዕክቱ ፤

" ጥር 24 ቀን 2005 በወጣው የሊዝ ውል መሠረት ከዚህ አመት በኋላ የሚገነቡ ግንባታዎች ሕገወጥ ስለሆኑ ማስረጃ ያላችሁ ሰዎች ማስረጃችሁን በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ  ያሌላችሁ ደግሞ ንብረታችሁን እንድታነሱ በአክብሮት እንጠይቃለን። " የሚል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ዙሪያ ፤ ቤቶችን የማፍረስ እንቅስቃሴ ካለባቸው አካባቢዎች መካከል " አለም ገና ዳለቲ " ተጠቃሽ ነው። ከላይ በአፋን ኦሮሞ የተያያዘው መልዕክት ከሰሞኑን አለም ገና ዳለቲ የተላለፈ ሲሆን መልዕክቱ ፤ " ጥር 24 ቀን 2005 በወጣው የሊዝ ውል መሠረት ከዚህ አመት በኋላ የሚገነቡ ግንባታዎች ሕገወጥ ስለሆኑ ማስረጃ ያላችሁ ሰዎች ማስረጃችሁን በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ  ያሌላችሁ…
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በዘመቻ መልክ ቤቶች እየፈረሱ ይገኛሉ።

የመንግስት አካል እነዚህ ቤቶች እያፈረሰ ሚገኘው ፤  " ህገወጥ ቤቶች ናቸው " በሚል እንደሆነ ተሰምቷል። በተለያዩ አካባቢዎች በ3 ቀን ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክትም መለጠፉን ተመልክተናል።

ነዋሪዎች በበኩላቸው ፤ ለረጅም ያህል ጊዜ የኖሩበት ቤት እየፈረሰ መሆኑን ገለፀው ልጆቻቸው ሜዳ ላይ በመውደቃቸው መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ተማፅነዋል።

ከሰሞኑን በለቡ ባቡር ጣቢያ በነበረ ቤት የማፍረስ እርምጃ ወቅት ደግሞ ነዋሪዎች ቤቱ አይፈርስም በማለት ባሰሙት ተቃውሞና በተከሰተ ግጭት በሰው ላይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር ተሰምቷል።

ቤት ፈረሰብን ካሉት መካከል ቤቱን ከዓመታት በፊት ከገበሬ ላይ እንደገዙ ፤ ከ2005 በፊት ለተሰሩት ቤቶችም የቤት ቁጥር ሲሰጥ እንደነበር ፤ " ህጋዊ ካርታ ይሰጣችኃል ጠብቁ " የተባሉም እንደነበሩ አመልክተዋል።

ቤቶች እየፈረሰባቸው ናቸው ከተባሉበት አካባቢዎች አንዱ በሆነው  " ዓለም ባንክ " አካባቢ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካል ሄደው ሁኔታውን ለመመለከት ችለዋል።

ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ዜጎች ሜዳ ላይ በአንድ ስፍራ ተሰባስበዋል ፤ ነዋሪዎቹ አዳራቸውን በዛው እንዳደረጉም ገልፀዋል። ቤቶች በሚፈርስበት ወቅት ጉዳት መድረሱንና ተኩስም እንደነበር ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላት ፤ በስፍራው ላይ በተገኙበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎችን ተመልክተዋል ፤ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሠቦችም " ከአካባቢው እንዲበተኑ " መልዕክት ሲያስተላለፍ ነበር።

አንድ ቤቱ የፈረሰበት ግለሰብ እሱን ጨምሮ ልጆቹና ባለቤቱ እንዲሁም ሌሎችም አዳራቸውን ውጭ (ሜዳ ላይ) ማደርጋቸውን ገልጾ ፤ በርካቶችም መጠጊያ ይሆነናል ወዳሉት ቤተዘመድ ምሽቱን ሲጓዙ እንደነበር ገልጿል።

በስፍራው ላይ ተሰብስበው የነበሩት ዜጎች መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን 10 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የኖሩበት ቤት እንዲፈርስ የተደረገባቸውም አሉ።

" ህገወጥ ቤቶች ፈርሶባቸዋል የተባሉ አካባቢዎች ህጋዊ ካርታ፣  መብራት፣ ውሃ የሌላቸው ናቸው " ሲሉ ደግሞ በወቅቱ ስፍርው ላይ የነበሩ አንድ የመንግስት አካል ነግረውናል። እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን የማስከበር ብቻ ነው ከሌላ ከምንም ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወቅቱን ያገናዘበ አይደለም ፤ እነዚህ ዜጎች ምንም መሄጃ የሌላቸውም ፣ በዚህ በበዓል ወቅት ይህ መደረጉ ፍፁም ህሊና ቢስነት ነው ፤ እርምጃም ከተወሰደ በኃላ መሄጃ ያጡትን ማብላት እና ውጭ ብርድ ላይ እንዲያደርጉ ከማድረግ አንድ ቦታ ላይ እንዲጠለሉ ማድረግ ይገባ ነበር " ሲሉ አንድ ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል።

" ከህገወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘም ከላይ እስከ ታች ያለው ሁሉም አካል ተጠናቂ መሆን ይገባዋል ይህ ሲደረግ ነው ህግ ተከበረ የሚባለው ፤ ይህ ሁሉ ሰው እየተንገላታ እየተጎዳ በወቅቱ ይህን ሲመለከቱ የነበሩ እና በይሁንታ ያለፉ አካላት ሁሉ ከህግ ተጠናቂነት ማለፍ የለባቸውም ሲል አክሏል።

ከላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ባለፈ በተለያዩ የአዲስ አበባ ዙሪያ አካባቢዎች ቤቶች እየፈረሱ እንደሆነ እየተሰማ ሲሆን እስካሁን ስለጉዳዩ ለህዝብ ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

(ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ)

የአፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመንግስትም ሆነ የግል  ቀጣሪ  ድርጅቶች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራቂ ሠራተኞቻቸው እና አዲስ ሰራተኞች ከመቅጠራቸው በፊት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነትና ትክክለኛነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል።

ተገልጋዮች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በኩል ይህን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ ከመምጣታቸው በፊት የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አገልግሎቱን ማግኝት  ይችላሉ ብሏል።

1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ  የተረጋገጠ  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ ፤

5. ዲግሪውን  ለመማር  በመግቢያነት  የተያዘው  ዲፕሎማ  ከሆነ  ዲፕሎማው  በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የስራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም  የደረጃ  4  ብቃት  ማረጋገጫ(COC) ካገኙበት ማዕከል የተረጋገጠ መሆን አለበት  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ እና

6. የስም ለውጥ ካለ የፍርድቤት ውሳኔ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ናቸው፡፡

የማስተርስ ዲግሪ ለማረጋገጥ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለጸው መንገድ መረጋገጥ ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል።

#ETA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መምህርት እና ፀሀፊ መስከረም አበራ ፍ/ቤት ቀረበች ። መምህርትና ፀሀፊ መስከረም አበራ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረበች ሲሆን ፖሊስ " ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ በማሰብ በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል ፤ ጉራጌ ዞን ንቃት በተባለ የበይነ መረብ ሚዲያና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም መንገድ እንዲዘጋ በማድረግና የመከላከያ ሰራዊት እንዳይታዘዝ በመቀስቀስ ወንጀል…
#Update

የፌደራል ዐቃቤ ህግ ዛሬ የ “ኢትዮ ንቃት” የዩ-ቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት በሆነችው መስከረም አበራ እና አምሀ ደገፋ በተባሉ የስራ ባልደረባዋ ላይ " በጥላቻ ንግግር " እና " በሐሰተኛ መረጃ ስርጭት " ሁለት ክሶች መስርቷል።

ክሱ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ መስከረም ክሷን በውጭ ሆና እንድትከታተል የ50 ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዷል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንዳይደር

@tikvahethiopia
ህፃን ልጇን እንደወለደች ጫካ የጣለች ግለሰብ በ2 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ተፈረደባት።

ተከሳሽ ግለሰብ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ፤ ፋሲል ክፍለ ከተማ አንቸው ቀበሌ በተለምዶ ፈሲል ከተማ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ በሠላም ወንድ ልጅ መውለድዋን የክስ መዝገቧ ያስረዳል።

ተከሳሽ የእናትነት ኃላፊነት ለመወጣት ያለባትን ግዴታ ወደ ጎን በመተው ከወለደችው በ40 ደቂቃ እድሜ ያለውን ወንድ ልጅ ህፃን በስሚንቶ መያዣ ማዳበሪያ በመጠቅለል ጫካ ውስጥ ትጥላለች።

ህፃኑ ከምሸቱ 1 ስዓት ከ20 ደቂቃ በአካባቢው ነዋሪ በሆነ ግለሰብ ተገኝቶ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምና ሳይንስ ኮለጅ በሀኪሞች እንክብካቤ እየተረዳ በመልካም ጤንነት ይገኛል፡፡

ወንጀል የፈፀመችው ግለሰብ የወለደችውን ህፃን ለአደጋ በማጋለጧ ክስ ተመስርቶባታል።

ተከሳሽዋ የመንግስት ጠበቃ እንዲቆምላት ተደርጎ በራሷ ነፃ ፈቃድ ጥፋተኛ መሆኗን አምና የእምነት ቃሏን ሰጥታለች።

የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በእምነቷ መሠረት ጥፈተኛ ብሎ በህግ የተፈቀደላትን ማቅለያ በመያዝ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ. ም በዋለው የወንጀል ችሎት በ2 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ተወስኖባታል፡፡

ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ የተሠጠው ቅጣት ተመሳሳይ ወንጀል ሠዎች ቢፈፅሙ ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻሉ አስተማሪ መሆኑ ተገልጿል።

ህፃኑን ለወደፊቱ ረጅ ድርጅቶች ወስደው እንዲያሳድጉት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር መጀመሩ ተገልጿል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር አቃቤ ህግ ነው፡፡

Credit : Gondar Communication

@tikvahethiopia
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኃላ ወደ ሩጫ ውድድር ልትመለስ መሆኑን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ እና የ5 ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊዋ አትሌት ጥሩነሸ ዲባባ ከ10 ቀናት በኃላ በሚካሄደው 22ኛው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ትሳተፋለች ተብሏል።

አትሌት ጥሩነሽ በግማሽ ማራቶን 66 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ የግሏ ፈጣን ሰዓት አላት።

በሂውስተን ግማሽ ማራቶንም በርቀቱ 67 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ያላት አሜሪካዊቷ ኤምሊ ሲሰን እና 66 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ ያላት ኢትዮጵያዊቷ ህይወት ገ/ኪዳን የጥሩነሽ ተፎካካሪዎች ናቸው።

#የኢትዮጵያ_ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ5 የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ማበረከቱ ተሰማ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ5 የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በከተማ አስተዳደሩና ባለሃብቶችን በማስተባበር የተገነባ የመኖሪያ ቤት እንዳበረከቱ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ለኪነጥበብ ባለሞያዎቹ የተበረከተው ካዛንቺስ የልቤ ፋና ትምህርት ቤት አካባቢ ከተገነባ መኖሪያ ቤት መሆኑ ተገልጿል።

ቤት የተበረከተላቸው ፦

- የዜማና ግጥም ደራሲ ይልማ ገብረአብ፣
- ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ፣
- ድምፃዊ አሸናፊ ከበደ፣
- ሻምበል በላይነህ እና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የሬዲዮና ቴሌቪዥን ድራማ ደራሲው መስፍን ጌታቸው ወላጅ እናት ወይዘሮ ሎሚናት ገብረመስቀል መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia