TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ? ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል። ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት…
#USA #TikTok

" ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " - ግሌን ያንግኪን

በአሜሪካ የቨርጂኒያ ግዛት ገዥ ግሌን ያንግኪን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች " ቲክቶክ "ን እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳወቁ።

ያንግኪን ፤ " ቲክቶክ " የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ለህጻናት ልጆቻችን አእምሮአዊ ጤንነት እጅግ ጎጂ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው ወደዚህ እርምጃ እንደሚመጡ ያሳወቁት ባለፈው አመት ቲክቶክን ከማንኛውም የመንግስት ኤሌክትሪክ መሳሪያዎች እና ዋይፋይ #ካገዱ በኋላ ነው።

ያንግኪን ፤ በአጠቃላይ ማህበራዊ ሚዲያ በልጆቻችን ላይ ከባድ እና ቀጣይነት ያለው አሉታዊ ተጽእኖዎች እያሳደረ ነው ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
- የማህበራዊ ክህሎታቸው እንዲያጡ ፣
- በሳይበር አማካኝነት የማዋረድ፣ ስድብና ሌላም ጎጂ ድርጊት እንዲደርስ፤
- የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲስፋፋ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አመላክተዋል።

በመሆኑም " ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቲክቶክ " ን ልጆች እንዳይጠቀሙ ከሚያግደው ረቂቅ በተጨማሪ ልጆች ከማህበራዊ ሚዲያ ግብይት እና መረጃዎቻቸውን ከመጠቀም እና ከመሸጥ የሚከላከሉ ህጎች እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የቨርጂንያው ገዥ " ሱስ አስያዥ " ብለው ከጠሯቸው የማህበራዊ ሚዲያ የማርኬቲንግ ስልቶች ልጆችን እና ታዳጊዎችን ለመጠበቅ የሚረዱ ረቂቆችን ይፋ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ቢሆንም " መቼ ? " የሚለውን አልገለፁም።

በአሜሪካ እንደ አጠቃላይ እስካሁን " ቲክቶክ " ባይታግደም፤ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ግን ተደጋጋሞ ተነግሯል።

በተለይም በርካታ የሪፐብሊካን ዕጩዎች በቀጣይ ምርጫ አሸንፈው ፕሬዜዳንት መሆን ከቻሉ በአጭር ጊዜ መተግበሪያውን ለማገድ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለያዩ ግዛቶች ደግሞ ከደህንነት እንዲሁም ወጣቶችን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ " ቲክቶክ " ከመንግሥት የኤሌክትሪክስ መሳሪያዎች ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጅ ካምፓሶች ዋይፋይ እንዲታገድ ተደርጓል።

" ቲክቶክ " ባለቤት የሆነው የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን ወቀሳ ውድቅ ሲያደርግ መቆየቱ እየሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia