TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AU_led_PeaceProcess

" መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነው " - አቶ ደመቀ መኮንን

" የአውሮፓ ህብረት (EU) በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ይደግፋል " - ሪታ ላራንጂንሃ

ዛሬ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆኑት ሪታ ላራንጂንሃ ውይይት አካሂደው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ደመቀ ፤ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በሰሜን ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ስላደረገው የሰላም ግንባታ ጥረት ገለጻ እንዳደረጉ ተገልጿል።

አቶ ደመቀ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ፤ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ሪታ ላርንጃንሃ በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቱን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ዳይሬክተሯ ፤ የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚደግፍ ገልፀው ፤ የሰላም ሂደቱን መደገፍ በሚፈለግ ጊዜ ለመርዳት ህብረቱ ፍላጎት እንዳለው አፅንኦት ሰጥተዋል።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia