TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዶክተር_ተወልደብርሃን_ገብረእግዚአብሔር

የአካባቢ ጉዳይ ተመራማሪ ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር  ማን ነበሩ ?

- ከአባታቸው ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ መዓዛ ወልደመድህን በትግራይ ክልል፣ ዓድዋ  ርባገረድ መንደር በ1932 ዓ/ም ነው የተወለዱት።

- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በንግስተ ሳባ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዊንጌት ተምረዋል፤ 1959 ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ቀዳማይ ኃላይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ  / በኃላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

- በአካባቢ ጉዳይ ላይ ለዓለም የሚጠቅም ተጠቃሽ ሥራዎችን ሰርተዋል።

- በብዝሐ ሕይወት ፣ በማሕበረሰብ (የአርሶ አደሮችን መብት) ማስከበር እና በዘረመል ምሕንድስና በሚመረት እህል ላይ ያደረጓቸው ምርምሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት አስገኝቶላቸዋል።

- ካገኟቸው ከዓለም አቀፍ ሽልማታቸው መካከል " የአማራጭ የኖቤል ሽልማት " እና " የምድራችን ጀግና " በሚል ሲንጋፖር ላይ በፈረንጆቹ 2006 ላይ የተሸለሙት ይጠቀሳሉ።

- ሕይወታቸው እስከአለፈበት ድረስም አዲስ አበባ ይኖሩ እንደነበር።

- ዶ/ር ተወልደብርሃን በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

- ዶክተር ተወልደ ብርሃን የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ፡፡ እንዲሁም ከ60 በላይ ሌሎች ልጆችን አሳድገዋል፡፡

Credit : #ኤፍቢሲ #ኤኤምሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ #ይነሳ #አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ…
#Update

ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
" ከአፍጥርና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንታደግ " - ደም ባንክ

በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ባንኩ በዚህ ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋብኮ ተናግረዋል።

#ሕይወትን_ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እንዲሁም ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች እንዲሁም በሥራ ቀናት በትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በመዘዋወር የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ ቅዳሜ አደባባይ ላይ ድንኳን በመትከል የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በመቀስቀስ እና እሁድ በቤተ እምነቶች የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

More : @tikvahethmagazine
#ነዳጅ

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል።

ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር እንደሚያደርግ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

የነዳጅ ግብይቱ በ #ቴሌብር አማራጭ የሚከናወን ነው የተባለ ሲሆን በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሁሉም የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር አሳውቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ አርብ ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ የተገኘው የአርቲስት ዳዊት ፍሬው አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል። ትላንት በሮም ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍታት እንዲሁም የአስክሬን ሽንት ፕሮግራም ተካሂዷል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ግንቦት 6 /2015 ከቀኑ 6 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት  ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን…
#Update

የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ።

የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

አርቲስት ዳዊት ፍሬው በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን 'ሜጀር ክላርኔት' በማድረግ የተመረቀ ሲሆን የአልቶ ሳክስፎን እና ክራር ተጨዋችም ነበር።

በአስደናቂ ክላርኔት ጨዋታው የሚታወቀው ዳዊት ፍሬው በሙዚቃ ትምህርት ቤት ቆይታው፣ የታላላቅ ሙዚቃ አቀናባሪዎች /ኮምፖዘሮችን/ የክላርኔት ሥራዎች ተጫውቷል።

በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ አልበሞችንም ለአድማጮች ማቅረብ ችሏል።

አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ውስጥ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ መገኘቱ ይታወሳል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#PropertyTax

ኢትዮጵያ ውስጥ " ፕሮፐርቲ ታክስ " እስካሁን እንዳልተጀመረ ነገር ግን ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ይፋ አደረጉ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ ፕሮፐርቲ ታክስ መላው ኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ ጨምሮ እንዳልተጀመረ ገልጸው በአ/አ እየተከናወነ ያለው ከዚህ ቀደም የነበረውን የጣሪያ እና ግርግዳ ግብር ህግ በማሻሻል እየተሰበሰበ ያለ ግብር ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

" ይህ የተሻሻለው የጣሪያ እና የግድግዳ ግብር ማለት ፕሮፐርቲ ታክስ ማለት አይደለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ወደፊት የፕሮፐርቲ ታክስ አዋጅ በዝርዝር የሚታይ ጉዳይ ነው ብለዋል።

" ፕሮፐርቲ ታክስ " ካቢኔው አፅድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ አዋጁ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

ከጣሪያና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ ያለው የታክስ ምንጭ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አምጥቶ ያልተገባ ሀብት ወስዶ ከሆነ ቅሬታ የሚሰማበት ስርአት ስላለ በዚያው ስርአት ቅሬታ ቀርቦ ሊታይ እንደሚችልም አስገንዝበዋል።

በአዲስ አበባ እየተሰበሰበ ያለው የጣራ እና የግድግዳ ግብር መሆኑንና ይህም ከ1937ዓ.ም ጀምሮ የመጣ እና ማሻሻያ የተደረገበት ነው ብለዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
" ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ከ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የተለያዩ እንከኖች በዚህኛው ዓመት መስተካከላቸውን የትምሕርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ምዝገባው በማንዋል በመሆኑ ተፈጥሮ የነበረውን የተፈታኞች መረጃ አያያዝ ጥራት ጉድለት ለማረም ዘንድሮ ምዝገባው በበይነ መረብ መካሄዱን አገልግሎቱ ገልጿል።

በተጨማሪም ከዩኒቨርሲቲ ድልድል፣ ዝግጅት እና አቀባበል ጋር በተያያዘ እክሎች የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ችግሩ መቀረፉን አረጋግጧል።

አምና ካጋጠመው ጉድለት በመማር የፈተና ማስፈጸሚያ ማንዋል እና መመሪያውን በማዘጋጀት እና በመከለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል።

ባለፈው ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ማዘጋጀት አለመቻሉ ዋና ችግር እንደነበር የጠቀሰው አገልግሎቱ በዚህ ዓመት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጿል።

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 869 ሺህ 802 ትክክለኛውን የምዝገባ ሂደት ያላሟሉ 1 ሺህ 213 ተፈታኞች ምዝገባ መሠረዙንም ተገልጿል።

ዘንድሮ ፦

- በመደበኛ 667 ሺህ 483
- በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ።

ፈተናው በሁለት ዙር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሳጣል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን፤ ሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 25 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ አገልግሎቱ አረጋግጧል።

የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 16 እስከ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እ
የሚገቡ ሲሆን ሐምሌ 18 ገለጻ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ገብተው ሐምሌ 24 ቀን ገለጻ ይሰጣቸዋል።

ተፈታኞች ፈተናውን በራሳቸው ጥረት እንዲሠሩ አሳስበው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባለፈው ዓመት የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 17 ሺህ ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን አስታውሷል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE የውጭ ምንዛሬ ክፍፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የብሄራዊ ባንክ ቦርድ መወሰኑን " ካፒታል " ጋዜጣ ዘግቧል። በዚህም ውሳኔ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ክፍፍሉ ቀደም ሲል ከነበረው 70/30 ወደ 50/50 እንዲስተካከል ተደርጓል። በውሳኔው መሰረት ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው 50 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ 40 በመቶውን የውጭ ምነዛሬውን ላመነጨው አካል እንዲሁም ቀሪውን 10 በመቶ ለባንኮች እንዲከፋፈል…
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፤ የዋጋ ንረትን ለማርገብ የሚያስችል የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።

ይህ በተመለከተ የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫው ምን ምን ነጥቦችን አነሱ ?

- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያየለ የመጣውን የዋጋ ንረት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቆጣጠር የብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።

- ከውሳኔዎቹ መካከል ለመንግስት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር ባለፈው አመት ከተሰጠው ከ1/3ኛ እንዳይበልጥ ይደረጋል።

- መንግስት ቅድሚያ የግምጃ ቤት ሰነድ አማራጭን አሟጦ እንዲጠቀምና አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ብቻ የቀጥታ ብድር ይጠቀማል።

- በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሰኔ መጨረሻ የሃገር ውስጥ ብድር ዕድገት በ14 በመቶ ጣሪያ ይገደባል። ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሰረት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል።

- ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስዱት ብድር የብድር ፋሲሊቲ ላይ የሚከፍሉት ወለድ ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።

- ቁልፍ የሆኑ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ላኪዎችን ለማበረታታት ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ምንዛሬ የማስተላለፍ ግዴታ ከ70/30 ወደ 50/50 እንዲሻሻል ይደረጋል። ላኪዎች 50 በመቶውን ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስገቡ፣ 10 በመቶውን አብረው ለሚሰሩት ባንክ እንዲሰጡ እና 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

- በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የዋጋ ንረቱ ከ20 በመቶ በታች እንዲሆንና በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ይሰራል።

ህብረተሰቡ ውሳኔውን በመደገፍ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፈተናው ተራዝሟል ፤ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እናሳውቃለን " - ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ፈተናቸውን ያልወሠዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል። ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም። ይሁን እንጂ በኢንተርኔትና ተዛማጅ ምክንያቶች ፈተናው መራዘሙን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በቅርቡ ይፋ በሚደረግ የፈተና ጊዜ ፈተናቸውን የሚወስዱ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያመጡ የሬሜዲያል ተፈታኞች ቀደም ብለው የሬሜዲያል ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካመጡ ተማሪዎች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ጊዜ ተመሳሳይ ስለሆነ ስጋት እንዳይገባቸው ብሏል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኤፍቢሲ በሰጡት ቃል ፤ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የሬሜዲያል ፈተና የተራዘመው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ስላልተጠናቀቁ ነው ብለዋል።

መጠናቀቅ ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በአግባቡ ለማጠናቀቅ ሲባል የፈተናውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም አስፈልጓል ያሉት ዶ/ር ኤባ ፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተጠናቀቁ በቅርቡ ተፈታኞች ለፈተና ስለሚጠሩ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ባለፈው ጊዜ ፈተና ያልወሰዱ እና የማካካሻ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ 46 ሺህ የሚጠጉ የመንግሥትና የግል ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል፡፡

ፈተናውን ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት የሚያመጡ የሬሜዲያል ተማሪዎች ቀደም ብለው ከተፈተኑት እኩል ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ዶ/ር ኤባ ሚጄና ገልጸዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia