TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሼህ አላሙዲ‼️

"ሼህ አላሙዲ ወደ #አዲስ_አበባ ይምጡ፤ #ሳዑዲ ይቆዩ #አናውቅም"- ጠበቃቸው
.
.
ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የቆዩት ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከእስር #መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ከእስር የተፈቱት ዛሬ ከሰዓት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል።

አቶ ተካ ሼህ አላሙዲንን #በስልክ ባይነጋግሯቸውም ከወንድማቸው ጋር አብረው እንዳሉ #አረጋግጩያለሁ ብለዋል። “ዛሬ ተፈትተዋል። አሁን ከሪያድ ወደ ጅዳ እየሄዱ ነው፤ ወደ ቤታቸው ማለት ነው። አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ተገናኝተናል። አዲስ አበባ ይምጡ፣ እዚያው ይቆዩ የምናውቀው ነገር የለም። እኛ አሁን #በመፈታታቸው ብቻ ደስታ ላይ ነው ያለነው።”

ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በከፈተው የጸረ-ሙስና ዘመቻ ከሌሎች ቱጃሮች፣ ልዑላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለስልጣናት ጋር በጥቅምት ወር 2010 ዓ. ም. ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከእርሳቸው ጋር ታስረው የነበሩ ቢሊየነሩ ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላልን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ እንደተፈቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ሼህ አላሙዲ ስለተፈቱበት ሂደት የተጠየቁት ጠበቃቸው “ዝርዝሩን አላወቅንም። እኛ የምናውቀው መፈታታቸውን ብቻ ነው” ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሳዑዲ አረቢያ በወጣቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ካቋቋመች በኋላ 11 ልዑላንን ጨምሮ 200 ገደማ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎችን አስራ ነበር። ልዑላኑ እና ቱጃሮቹ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት በሪያድ በሚገኝ ባለአምስት ኮከቡ ቅንጡ ሆቴል እንዲታሰሩ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ተጠርጣሪዎቹ ሆቴሉን እንዲለቅቁ ከተደረጉ በኋላ በታሰሩበት ስፍራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል የሚል ወቀሳ ሲሰማ ቆይቷል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ፈፅሞ ወደኢትዮጵያ መመለስ አይፈልጉም!

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ኢትዮጰያ ምህረት ቢደረግለትም የመመለስ ፍላጎት የለውም። በዝንቧቤ ለመንግስት ጋዜጣ የሚሰራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው የቀድሞ የኢትዮጰያ ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የዝነንቧቤ ፕሪዝዳንቱ ፀጥታ አማካሪ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጰያ መንግስት ከተፈረደበት ፍርድ ምህረት በያደርግለት እንኳን ሀገሩ #ፈፅሞ መሄድ እንደማይፈልግ ጋዜጠኛው ከሶስት ወር በፊት ቢሮው ለስራ በሄደበት እንዳጫወተው ገልጿል። "እድሜው ቢገፋም ሰውነቱ አሁንም ለስራ ብቁ ነው። እኛ ዝምቧቤያዉያን በሚድያ አይተነው #አናውቅም። ቢሮው ስንሄድ የመጫወት ችግር የለበትም። ድምፁን እንድትቀዳ፣ ፎቶ እንድታነሳው ወይንም ማስታወሻ ይዘክ እንድታወራው አይፈልግም። ወዳጁ ሙጋቤ ቢሞትም ፕሬዝዳንት ምንጋጋዋ ለመንግስቱ ከፍተኛ አክብሮት አለው። ወዳጅነታቸውም የቆየ ነው።" ብሏል ጋዜጠኛው።

ምንጭ፦ ተስፋዬ ጌትነት/ከካፒታል ጋዜጣ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 99.38 በመቶ ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ50 በመቶ በላይ ድምፅ ያገኘ እንደሌለ የሚወጡት ሪፖርቶች አሳይተዋል።

በምርጫው ትልቅ ግመት የተሰጣቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ፤ 49.42 ድምፅ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው ከማል ኪሊዳሮግሉ 44.95 ድምፅ አገኝተዋል።

በሌላ በኩል ትላንት ምሽት ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን በፓርቲያቸው ፅ/ቤት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገው ነበር።

ምን አሉ ?

- የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶች በሰፊ ልዩነት እየመራን መሆኑን ያሳያሉ።

- የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ድምፅ ቆጠራው ይቀጥላል። (በቱርክ ምርጫ በውጭ ያሉ የቱርክ ዜጎችም ድምፅ የሚሰጡበት መንገድ ያለ ሲሆን በአሁንም ምርጫ ድምፃቸውን ሰጥተዋል)

- እነሱ (ተቃዋሚዎች) " እየመራን ነው " እያሉ ሰዎችን ለማሞኘት እየሞከሩ ነው።

- ፕሬዜዳንታዊ ምርጫው በመጀመሪያው ዙር ይጠናቀቅ እንደሆነ እስካሁን #አናውቅም

- ከእኛ የቅርብ ተቀናቃኝ በ2.6M ድምጽ ርቀናል።

- በመጀመሪያው ዙር እንደምናሸንፍ እናምናለን።

- በታሪካችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምርጫ ነበር የተሳተፈው።

በቱርክ ምርጫ ላይ አንድ ተወዳደሪ ለማሸነፍ በመጀመሪያ ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ተወዳዳሪዎች 50 በመቶውን ድምፅ ማለፍ ካልቻሉ ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ይገናኛሉ።

አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫው ወደ ሁለተኛ ዙር የማምራቱ እድል ሰፊ መሆኑ ተነግሯል።

መረጃው የአናዱሉ እና የቲአርቲ ወርልድ ነው።

@tikvahethiopia