TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በዛሬው ዕለት በሴቶች የማራቶን ውድድር #የወርቅ እና #የብር ሜዳልያዎችን ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ያመጡት አትሌት አማኔ በሪሶ እና አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ሜዳልያቸውን ተረክበዋል።

Via @tikvahethsport (ሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት)

@tikvahethiopia 
#ኢትዮጵያ❤️

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን በዛሬው ዕለት መካሄዱን በጀመረው የሪጋ የአለም የጎዳና ላይ ሻምፒዮና የተለያዩ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል።

በወንዶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት በሀጎስ ገብረሕይወት #ወርቅ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ #የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።

ሀገራችን የአለም ሪከርድ በሰበረችበት የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በሴቶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር አትሌት እጅጋየሁ ታዬ #ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።

የሜዳሊያ ሰንጠረዡን የሚመሩት ሀገራት እነማን ናቸው ?

1. ኢትዮጵያ :- ሁለት ወርቅ ፣ ሁለት ብር እና አንድ ነሐስ

2. ኬንያ :- አንድ ወርቅ ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ

3. አሜሪካ :- አንድ ወርቅ እና አንድ ነሐስ

via @tikvahethsport

@tikvahethiopia