TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተጀመረው አገልግሎት የማቅረብ ሥራ እንዲፋጠን መመሪያ ሰጥተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ በትናትናው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው የመንግሥት የልዑካን ቡድን በመቐለ ከተማ የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ መስጠቱን  ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበላቸውን ማብራሪያ ካዳመጡ በኋላ  ለተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች የተጀመረውን አገልግሎት የማስጀመር ስራ #እንዲያፋጥኑ መመሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር ሬድዋን አመልክተዋል።

ይህንን መመሪያ ተከትሎ በነገው እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ መደበኛ በረራ እንደሚጀምር መገለጹን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ ኢትዮ ቴሌኮም ከሰሞኑ ተመሳሳይ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ እንደሚጠበቅም አምባሳደሩ ገልፀዋል።

በ2ኛው የናይሮቢ የሰላም ስምምነት መሠረትም እስከ ፊታችን ሀሙስ ድረስም ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ለመንግስት የማስረከብ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትም በመቐለ  ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሳውቀዋል።

Credit : Ethiopia Press Agency

@tikvahethiopia