TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በRomal የክር ጥበብ(String Art) እና በአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የክር የስዕል ጥበብ አዉደ-ርዕይ ከታህሳስ 2 ጀምሮ ለተመልካች ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ይገኛል።

ይህን አውደ ርዕይ እስከ ፊታችን እሁድ ታህሳስ 16 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ በመሆኑ ታዳሚያን #በዲሊኦፖል ሆቴል ተገኝተው በነጻ እንዲጎበኙ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የክር ጥበብ(String Art) እንዴት ይሰራል ?

የክር ጥበብ ያለ ምንም ቀለም በተለያዩ የክር ውጤቶች፣ ጥቃቅን ሚስማሮችና መደብ የሚሆን እንጨተት (MDF) አማካኝነት የሚሰራ የጥበብ ውጤት ነው።

ለአብነት ያክል ከላይ በፎቶ የተያያዘው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ መልክ የተሰራው የጥበብ ሥራ ከ4000 በላይ ሚስማሮች(የባከኑትን ጨምሮ)፣ 9 አይነት የክር አይነቶች ጥቅም ላይ ውለዋል።

በተጨማሪም ሚስማሩን ቅርጽ አሲዞ ለመምታት ወደ 11 ሰዓታት የፈጀ ሲሆን ቀሪው በ4 ቀናት ውስጥ ሥራው ተጠናቋል።

ይህ የጥበብ ሥራ በዚህ የአውደ ርዕይ ወቅት የሚሸጥ ከሆነ አዘጋጆቹ 180 ሺ ብር ተመን አውጥተውለታል።

በአውደ ርዕዩ ከ50 በላይ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን ሁለት ወጣቶች በዋነኛነት፤ በአጠቃላይ አራት ወጣቶች በሥራው ላይ ተሳትፈውበታል። በቀጣይ የተለያዩ ሥራዎችን አካተው የአርት ጋላሪ የመክፈት እንዲሁም በዲጂታል አማራጭ ሥራቸውን የመሸጥ ትልም አላቸው።

NB: ከላይ በፎቶ የምትመለከቷቸው የጥበብ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በክር የተሰሩ ሲሆኑ ክሮቹ ተጠላልፈው ከፈጠሩት ቀለም ውጭ ምንም አይነት ቀልም አልተጠቀሙም።

More : @tikvahethmagazine