TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአዲስ አበባ ያመለጠው የኮቪድ-19 ታማሚ!

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ሰባት (7) መሆናቸውን ገልጿል።

ከነዚህ ሰባት (7) ሰዎች መካከል አንደኛው ከአዲስ አበባ ከተማ #አምልጦ የተያዘ እንደሆነ ቢሮው በዛሬው ዕለታዊ መግለጫው ጠቁሟል።

ይህ ከአዲስ አበባ ከተማ አምልጦ የተያዘው ግለሠብ #በትላንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴር አዲስ በቫይረሱ መያዛቸው ካረጋገጠው 61 ሰዎች ውስጥ አንደኛው ነው።

ግለሠቡ በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ ላይ ተይዞ እዛው በይቶ ማቆያ እንዲቆይ ተደርጓል። ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው 30 ያህል ሰዎች ተለይተው በማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በነገራችን ላይ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት ባለፉት 24 ሰዓት 76 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዘ ሰው #አልተገኘም። እስካሁን በአጠቃላይ ለ1,072 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" ... መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉት 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ናቸው " - ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

ከቃሊቲ ማረሚያ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ነበሩ የተባሉ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት  መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉር የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች መሆናቸው ተነግሯል።

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለኤፍ ቢ ሲ የሰጡት ቃል ፦

" ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት #አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል።

ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች አሉ።

ማረሚያ ቤቱ  ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ ውሏል።

ታራሚዎቹ  ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ተገቢ የሆነ  የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላል። "

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
" . . . ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " - የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን

ከትላንት በስቲያ በሶማሌ ክልል፣ ቀብሪደኀር ከተማ አንድ የመከላከያ ሠራዊትን ከድቶ ከካምፕ ያመለጠ ነው የተባለ አባል ድንገት ተኩስ በመክፈት አራት ሰዎችን ገድሎ ሶስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተሰምቷል።

የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ለቪኦኤ ሬድዮ በሠጠው ቃል ፤ ድርጊቱን የፈጸመው ወታደር ከካምፕ #አምልጦ የጠፋና ለሦስት ቀናት ክትትል ሲደረግበት የቆየ እንደሆነ ገልጾ አስቀድሞ ተኩሶ የመታውም ተከታትለው የደረሱበትን የቀብሪ ደኀር ነዋሪ እና የከተማዋን አመራር አባል ነው ሲል ገልጿል።

ግድያውን የፈጸመው ወታደር ተጨማሪ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ርምጃ እንደተወሰደበት ተገልጿል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ግድያውን የፈጸመው ወታደር ከ3 ቀናት በፊት ከመከላከያ ካምፕ ያመለጠና ክትትል እየተደረገበት የነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆኑን ገልጾ " ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " ብሏል።

በሌላ በኩል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ ፤ ከቀብሪድሃር ከተገደሉት አራት ሰዎች ሶስቱ ፓርቲው አባላት እንደነበሩ አንዱ ሰው ደግሞ የብልፅግና ፓርቲ አመራር እንደነበር ገልጿል።

የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት እንዲሁም የጦር ሰራዊቱ ድርጊቱን በፍጥነት አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት አካባቢውን ለቆ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደ ሶማሌ ክልል ከተመለሰ በኋላ ይህን መሰል ጥቃት በልዩ ልዩ ከተሞች እየተሰማ ነው ሲል ኦብነግ በመግለጫው አመልክቷል።

ኦብነግ፤ የሠራዊቱ ካምፖች ከከተሞች እንዲርቁና የመከላከያ አባላት ትጥቅ ይዘው ወደ ከተማ ከመግባት እንዲከለከሉ ጠይቋል።

የሶማሌ ክልል ሕዝብ በዘመነ " ኢሕአዴግ " በርካታ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንደተፈጸሙበት ያስታወሰው ኦብነግ ዛሬም የመከላከያ ሠራዊቱን እንደ ጠላቱ እንዲያይ ከሚያደርጉ አካሔዶች መቆጠብ ተገቢ ነው ሲል አስጠንቋል።

ተመሳሳይ ጥቃቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ ርምጃዎች መወሰድ አለባቸውም ብሏል።

ትላንት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና የሶማሌ ክልል አመራሮች የቀብሪደኀር ከተማ ነዋሪዎችን ሰብስበው ስለ ጉዳዩ እንዳወያዩዋቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ  አስታውቀዋል።

መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት ነው።

ፎቶ፦ ኦብነግ

@tikvahethiopia