TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PMOEthiopia

አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የውይይት ባህልንነና የሐሳብ የበላይነትን ለማዳበር ታልሞ ተቃርኗዊ ዕሳቤዎችን ለማቀራረብ የሐሳብ ብዝኃነትን ለማዳበር እንዲሁም ለነበሩና አዲስ ለተፈጠሩ ችግሮች ፈጠራ የታከለባቸውን መፍትሔዎች ለማበረታታት ታስቦ የሚዘጋጅ መድረክ ነው፡፡ ዛሬም ለሦስተኛ ጊዜ በሂልተን ሆቴል ከተለያዩ ከጋዜጠኞች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር "የሚዲያው ሚና ሐሳቦችን ለማቀራሀብ" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱን አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ዝግጅቱን ያስጀመሩ ሲሆን ቀጣይ በዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ " ሚዲያ በሽግግር ወቅት" በሚል የጥናት ውጤት ያቀረቡ ሲሆን ቀጣይ የውይይት መድረኩን ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሀ (ቪ.ኦ.ኤ ) እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ( AP ) በአወያይነት እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ ተሳታፊዎች ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተማሪዎች ከዩኒስቨርሲቲ ግቢ ውጭ ቆይታ ላይ ገደብ ተጥሏል...

1. ተማሪዎች ከዶርም ውጭ ቆይታ ከአራት ሰዓት እንዳያልፍና በፕሮክተሮች በየእለቱ ክትትል እንዲደረግ

2. ተማሪዎች ከንጋት 12:00 ሠዓት በፊትና ከምሽት 1:00 ሰዓት በኃላ ከግቢ ውጭ እንዳይገኙ ሆኖ የግቢ ጥበቃ በሽፍት ኃላፊዎች፣ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አካላት በዚህ ላይ መረጃ ተሰጥቷቸው እንዲያስፈፅሙ እያልኩ ተማሪዎች ከዚህ ውጭ በሚፈጠረው ጉዳት ኃላፊነት እንደሚወስዱ መረጃ እንዲደርሳቸው በጥብቅ አሳስባለሁ።

(ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም)

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል...

የኢህአዴግ መፍረስን የሚመለከት ጉዳይ ግን ተዘግቷል። አሁንም ከህዝባችም ጋር ተመካክረን ልንዘጋው ይገባል። አፍርሰውታል ከዚህ በኃላ ኢህአዴግ እንደሌለ አውቀን ነው መስራት ያለብን።

ሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የነበራቸውን መስመር ትተው ሄደዋል። እኛ ግን አልተውንም። ክህደት ነው ያለነውም ለዚህ ነው። እኛ ብቻ ሳይሆን በድህነት ውስጥ ያለው ህዝባቸውና ሀገራቸው ክደው ነው የሄዱት እነዚህም ከሃዲዎች ናቸው። ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን ከድተው ለውጭ ኃይሎች አሳልፈው ሰጥተውታል።

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስከ ረቡዕ ድረስ ትምህርት ካልጀመሩ ማንኛውም አገልግሎቱን ሊያቋርጥ ነው!

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ተማሪዎች እስከ ረቡዕ ታህሳስ 22/2012 ድረስ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ትምህርት የማይጀምሩ ከሆነ ተማሪዎች የክሊራንስ ፎርም በመሙላትና የሚመለከታቸውን የቢሮ ኃላፊዎች በማስፈረም፤ በእጃቸው ያለውን ማንኛውም የዩኒቨርሲቲውን ንብረት በመመለስ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ አሳልፏል።

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ዘመቻ...

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን (ሞዴስ፣ ፓንት..ወዘተ) የማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል፡፡ በዚህ በመክፈቻ ሰነ-ሥርዓት ላይ ከክፍለ ከተሞች 55,000 እንዲሁም ዛሬ ተካሄዶ በነበረው የማስ ስፓርት ላይ ከተሳተፉ የስፓርት ቤተሰቦች 100,000 ሞዴስ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በ አዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ አቅም ለማይፈቅድላቸው ተማሪዎች በዘንድሮ አመት ሙሉ ለሙሉ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ለማዳረስ ለታቀደው እቅድ ወደ 700,000 የሚጠጋ ሞዴስ ያስፈልጋልም ነው የተባለው፡፡

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-01-05

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጥያቄያችሁ መልስ...

ምርጫው የሚካሄድበት ቀን መቼ ነው?

- የጊዜ ሰሌዳው እስካሁን አልተወሰነም

የምርጫ 2012 የጊዜ ሰሌዳን በሚመለከት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። ምርጫ ቦርድ እስካሁን የጊዜ ሰሌዳውን እንዳልወሰነ፤ ምናልባትም በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊያሳውቅ እንደሚችል ገልፀውልናል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

#Election2012
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ባለድርሻ አካላት ለምርጫ 2012...

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ 2012ን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ውይይት ተጀምሯል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የውይይቱ ተሳታፊዎች ነን የሚነሱ ጉዳዮችን ከስር ከስር መረጃ እናካፍላችኃለን።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ለሆናችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

#TIKVAH_ETHIOPIA
#TIKVAH_SPORT
#TIKVAH_MAGAZINE
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• መልአከ ህይወት ቆሞስ አክሊለ ማርያም የአገልግሎት ስፍራቸው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንዳፋ በኬ ማርያም መሆኑን ይናገራሉ በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኝ መስጂድንና ቤተ ክርስቲያንንም በእኩል ቆመው ያሳንጻሉ። መልዕክታቸውን እንዲህ አስተላልፈዋል፡-

- ኢትዮጵያዊያን ድሮ የሚያስቡት ሰውን ሰው በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ያለው ነገር እንኳን በተማሩት በእኔ ባልተማርኩት፣ በኔ በታናሹ፣ በኔ በመነኩሴው ዘንድ ያሳስበኛል፡፡

- ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል ለትምህርት ሄደው የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ያሳስበኛል፡፡ እኔ ያደኩት አሁንም ያለውት በኦሮሚያ ክልል ነው በእውነት የኦሮሞ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው። ይህንን ስራ የሚሰሩት የፓለቲካ ትርፍ ያላቸው ናቸው፡፡

- እኔ በየዕለቱ ቅዱስ ቁርዓን አነባለሁ ቅዱስ ቁርዓን ማንበብ ከጀመርኩ በኀላ ኢትዮጵያ ብዙ እሴት ያላት ሀገር መሆኗን ነው የተረዳውት፡፡

- በአሁን ሰዓት በእምነት መኖር ሳይሆን በእምነት መሸጋገር ያስፈልጋል፡፡

🎧 11 MB [WiFi ተጠቀሙ]

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ! ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። አሁን ላይ 4ተኛ…
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት 4ኛ ዙር በማጠናቀቅ 240 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስቴም ፓወር በቀጣይ አምስተኛ ዙር ሰልጣኞችን መዝገባ በማከናወን ሥልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ሥልጠናው መሰጠት ይጀምራል። በኦላይን ለመሰልጠን ለተመዘገቡም ስለጠናውን እየተሰጠ ይገኛል።

ከ4ኛው ዙር የተመረጡ ምርጥ 4 ፕሮጀክቶች፦

1. ግብርና እና ምግብ ዘርፍ፦

- ዮፍታሔ ሳሙኤል - Mushroom Agro-processing

- ​​ስጦታው አበራ - Punt Flour from Gipto

2. አገልግሎት ዘርፍ፦

- Wujo Digital Iqub

3. ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ:

- መኮንን አስማረ - Agricultural Chemical Spray & Aerial Mapping Drone

በልዩ ዘርፍ፦ ዶ/ር ትዝታ አለሙ - Biruh Hiwot Mental Health Consultancy

#STEMpower #VISA #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል።

እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦

• ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

• በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው  ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል።

በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27,267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች)

- ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል።

#MoE #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል። እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - በ2014 ዓ/ም…
#MoE

" አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል "  - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል።

" በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው ፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል " ያሉት ሚኒስትሩ " አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው " ብለዋል።

" የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ " ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ " ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ' ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም ' የሚል ነው " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው " ለሁሉም የምለው አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል ፤ ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

#MoE #Tikvah_Ethiopia

@tikvahethiopia