TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቴሌግራም

ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) ይጠቀማሉ ?

የተለያዩ የዲጂታል መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን ስንጠቀም ቀዳሚው ነገር ደኅንነቱን የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ይህም በሁለት አይነት መልኩ መመልከት ይቻላል።

የመጀመሪያው የምንጠቀመው መተግበሪያም ይሁን ድረ-ገጽ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል ሲሆን ሁለተኛው በራሳችን የምናደርገው የደኅንነት ማረጋገጫ ሂደቶችን ማጠንከር ነው።

💻 የደኅንነት ማረጋገጫ ሂደቶችን እንዴት ማጠንከር ይቻላል ?

- የምንጠቀመው የይለፍ ቃል (Password) በቀላሉ ተገማች መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ጠንካራ የይለፍ ቃል [ ፊደል፣ ቁጥርና ምልክቶችን ያካተተ] ቢጠቀሙ ይመከራል።

- ተጨማሪ የደኅንነት መጠበቂያ ሥርዓቶችን መጠቀም ያስፈልጋል። ይህም ድንገት እንኳን ሰዎች የይለፍ ቃላችንን (Password ) ቢያገኙት በዚህኛው በሁለተኛው የደኅንነት መጠበቂያ መያዝ እንችላለን። ይህም በአብዛኛው ጊዜ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) በመባል ይታወቃል።

- ስልክ ቁጥራችን በዚህ ሰዓት አንዱ ትልቁ የደኅንነት ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን የሂሳብ አካውንት ቁጥራችን ጭምር ነው። በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የምንጠቀመው ሲም ካርድ በስማችን መውጣቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ይህ ካልሆነም ሲም ካርዱ በእጃችን እያለ በስማችን ማዞር ይጠበቅብናል። በአንጻሩ በስማችን ተከፍቶ የነበረ ሲም ካርድ ካለ አሁን የሚገለገለው ግለሰብ ስሙን ወደ ራሱ እንዲያዞርም ማድረግ ይጠበቃል።

- የበመልዕክት ሚላኩልንን የማረጋገጫ ቁጥሮች (OTP) በምንም መልኩ ለሌሎች አሳልፈን መስጠት አይጠበቅብንም። በተመሳሳይ የትኛውም አካል የሚስጢር ቁጥራችንን ቢጠይቀን መናገርም ሆነ መላክ አይኖርብንም።

💻 ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) ባልጠቀምስ ?

- የይለፍ ቃል (Password) የሚያገኝ/ የሚያቅ ሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ግል አካውንቶ ይገባል።

- ተሳስተው በተለያዩ መንገዶች የሚላኩ ሊንኮችን ቢከፍቱና ስልክና የይለፍ ቃል እንዲያስገቡ ተጠይቀው ቢያስገቡ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ የማይጠቀሙ ከሆነ የግል አካውንቶ የሌሎች መጠቀሚያ ይሆናል።

💻 ቴሌግራም ላይ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) እንዴት መጠቀም እችላለሁ ?

በቴሌግራሞት ላይ Setting የሚለው ላይ ገብተው Privecy and Security በመጫን  Two-Step verification የሚለውን ON በማድረግ የይለፍ ቃል መፍጠር እንዲሁም የይለፍ ቃሉን ቢረሱት መልሰው የሚያገኙበትን ኢሜይል አስገብተው የደኅንነቶን ደረጃ ከፍ ማድረግ ይችላሉ። [ ሙሉ ሂደቱ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።]

#StaySafeOnSocialMedia
#DigitalLiteracy

Via 👋 @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM