TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል። መልካም ፈተና! @tikvahethiopia
#Update

የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተሰጥቷል።

#Amahra

በአማራ ክልል ከ37 ሺ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና ሲሰጥ ውሏል። ፈተናው በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችና በደሴ ከተማ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በ1 የፈተና ጣቢያ ፈተናው ነው የተሰጠው።

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ በቡሬ በተቋቋመ የመፈተኛ ጣቢያ ተፈትነዋል።

#OromiaRegion

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች 14,228 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸው ፤ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከተጠበቁት 16,608 ተማሪዎች መካከል 1, 243 በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ላይ አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

በምዕራብ ወለጋ የቤጊ እና ቆንደላ ወረዳዎች 1,137 ተማሪዎች በአራት የፈተና ጣቢያ ፈተናው ላይ የተቀመጡ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ፈተናው ላይ እንዳልተቀመጡ ተገልጿል።

#Afar

በአፋር ክልል ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 257 ተማሪዎች 154 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን አንፃራዊ ሠላም ተመዝግቦባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

• የሁለተኛው ቀን ፈተና ይቀጥላል።

መረጃ ፦ ኢብኮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራክ ክልል ትምህርት ቢሮ

ፎቶ ፦ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ የወልዲያ ከተማ ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ፣ የቤ/ጉ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amahra

" የባልደረባችንን አስክሬን ማምጣት አልቻልንም ፤ እዛው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ነው ያለው " -ዶ/ር ፋሪስ ደሊል

ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ወደ አማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሄዱ እና በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት  መመለስ ያልቻሉ መምህራንን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አሳውቀዋል።

በርከታ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን ወደ አማራ ክልል በሄዱበት በተባባሰው ግጭት ምክንያት ከክልሉ መውጣት ባለመቻላቸው ችግር ላይ መሆናቸውን እየገለፁ ናቸው።

መምህራኖቹ አማራ ክልል ከሚገኙ ተቋማት አንዱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ፤ መምህራኑን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፤ ባለፈው ሳምንት በጎንደር የተገደለው መምህር የተቋማቸው ባልደረባ መሆኑን ገልጸው እስካሁን እስክሬኑ ከከተማው እንዳልወጣ ጠቁመዋል።

ሌሎችም መምህራን ጎንደር እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ዶ/ር ፋሪስ ፤ " ለመፈተን ከሄዱ መምህራን አንዱ መምህር ታደሰ አበበ አስክሬኑን ማምጣት አልቻልንም እዛው ነው ያለው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ " ያሉ ሲሆን " ሌሎች ለመፈተን የሄዱ መምህራንም አሉ እነሱን በስልክ እያገኘናቸው ነው መመልስ አልቻሉም " ብለዋል።

ካሉበት ወጥተው ለመምጣት ደህንነት የለም ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የጥይት ድምፅ በተለያየ ቦታ ይሰማል ዩኒቨርሲቲው ባላችሁበት ቆዩ ነው ያላቸው። " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምህራኑ ጉዳይ እየተነጋገርን ነው ያሉት ዶ/ር ፋሪስ " መንገዱ ሰላም ሆኖ መውጣት የሚችሉበት ሰዓት ደርሶ እስኪመጡ በትግዕስት መጠበቅ እንዳለብን ነው የምንነጋገረው ፤ እዛው ከለው የዩኒቨርሲቲ አመራር ፣ ፕሬዜዳንቱም ጋር እየተደዋወልን ነው በትዕግስት ጠብቀን መንቀሳቀስ ሲችሉ መምህራኖቻችን እና የባልደረባችንን አስክሬን እንደምናገኝ ነው የምንነጋገርው " ብለዋል

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፤ 53 መምህራን በጎንደር ፣ ደባርቅ እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች እንደተመደቡና ሁኔታቸውን በቅርበት እየተከታተልን ነው ብለዋል።

ደህንነታቸው ተጠብቆ በሚወጡበት ሁኔታ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር እየተነጋገርን ነው ሲሉ አሳውቀዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፤ ፈታኝ መምህራንን ቀደሞ ወደመጡበት መሸኘቱን ተፈታኝ ተማሪዎች ግን በመንገድ መዘጋት ምክንያት ከግቢ መውጣት አልቻሉም ብሏል። ተቋሙ ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑትን እና ቤተሰብ ያላቸውን የሸኘ ሲሆን ወደ ወረዳ እና ዞን መመለስ የነበረባቸውን በመንገድ መዘጋት መሄድ ስላልቻሉ ግቢ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን ለሬድዮ ጣቢያው (ቪኦኤ) ገልጿል።

የአውሮፕላን በረራ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፈተና አስፈጻሚዎች / መምህራን " ያለው ሁኔታ እስከሚረጋጋ ድረስ ትንሽ ቀን " መጠበቅ እንደሚኖርባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ባለፈው አርብ በሰጡት መግለጫ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ? በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ ? #ባሕርዳር ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው…
#Amahra

በአማራ ክልል ከተሞች ላይ ያለው አንፃራዊ ሰላም አሁንም መቀጠሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ፤ ከተማዋ ወደ ቀደመው መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ገልጸዋል።

የሰዎች እንቅስቃሴም ካለፉት ቀናቶች በተሻለ መኖሩን ጠቁመው አሁንም አንዳንድ በትልልቅ ቋጥኞች የተዘጉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ፤ ካለፉት ቀናት ጀምሮ በከተማው የቱክስ ድምፅም ሆነ ግጭት እንደሌለ አመልክተዋል።

በጎንደርም አንፃራዊ ሰላም ያለ ሲሆን ታክሲዎች፣  የቤት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን ፤ ሱቆች እና አንዳንድ ተቋማት መከፈታቸውን ነዋሪዎች አመልከተዋል።

አንድ ነዋሪ ፤ ትላንት በርካታ የከተማው ነዋሪዎች በወፍጮ ቤት እህል ለማስፈጨት እና ሱቆች ላይ እቃ ለመሸመት ተሰልፈው መመልከቱን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ግጭቱትን ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ በመናሩ ህብረተሰቡ እየተቸገረ መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ ተቀስቅሶ የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በሸቀጦች ላይ በእጥፍ ጭማሪ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ የደሴ ነዋሪ ፤ ውጊያ ከመቀስቀሱና መንገድ በመዘጋቱ በፊት 6,800 ብር ይገዛ የነበረው አንድ ኩንታል ነጭ የዳቦ ዱቄት 8,800 ብር መግባቱን ገልጸዋል። ውጊያው ከፈጠረብን ጭንቀት በላይ የተጋነነው የሸቀጦች ዋጋ ያሳስበናል ብለዋል።

እስከ 800 ብር ይገዛ የነበረ 5 ሊትር ዘይት 1150 ብር ፤ 50 ብር የነበረው አንድ ኪሎ ሽንኩርት እና ቲማቲም 100 ብር ፣ እስከ 90 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ስኳር 120 ብር መግባቱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነጋዴ ከአዲስ አበባ ያመጣንበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ጭማሪ ለማድረግ ተገድጃለሁ ያሉ ሲሆን ይህ የነጋዴው ምላሽ ግን ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከነዋሪዎች አስተያየት የሰጡ ገልጸዋል።

ውጊያ ከተነሳ በኃላ መንገድ ተዘግቶ ስለነበር ነጋዴ በውድ ዋጋ ሊያመጣ የሚችልበት መንገድ የለም ፤ ቀድሞ ከውጊያ በፊት የገባን ምርት ጨምሮ መሸጥ ሸማቹን ለችግር መዳረግ ነው ብለዋል።

እኚሁ አስተያየት ሰጪ ምርቶችን የመከዘን ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

በባህር ዳር በግጭቱ ሳቢያ ውሃ 1 ሳምንት መጥፋቱን አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ውሃ ፍለጋ ጉድጓድ ወዳለበት ጄሪካን ይዞ ለመሄድ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በጎንደር በግጭቱ ምክንያት ለ6 ቀን ውሃ ተቋርጦ መቆየቱን አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ባልደረባ ገልጸዋል።

የውሃ አገልግሎት መቋረጡ በቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል አገልግሎቱን የሚያገኙ ወላድ እናቶች ላይ እንዲሁም በሌሎች ህሙማን ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።

ውሃ ባለመኖሩ ሃኪሞች የሚለብሱት ጋዋን ፣ ቀዶ ህክምና የሚደረግላቸው ህሙማን የሚለብሱት አልባሳት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሳይታትጠብ መቆየቱን ገልጸዋል። እንደ አማራጭ ከሌሎች ህክምና ተቋማት አልባሳትን መዋስ ፣ የዝናብ ውሃ እስከመጠቀም ተደርሶ ነበር ብለዋል።

ማክሰኞ እና ረቡዕ ችግሩ ተባብሶ ቀዶ ጥገና ተቋርጦ እንደነበር አስተውሰዋል። ከትላንት ጀምሮ ግን የተቋረጠው የሆስፒታሉ ውሃ መምጣቱን የህክምና ባልደረባው አመልክተዋል።

መረጃው ከቪኦኤ (መስፍን አራጌ) የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara #Oromia ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።…
#Amahra #Oromia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ወደቄያቸው ለመመለስ ከሰሞኑን በክልሎቹ መካከል የተደረሰበትን የመግባባት ስምምነት በተመለከተ ለሁለቱም ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ተከታዮችን ጥያቄዎች አቅርቧል።

👉 ከሞት ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመመልስ ፈቃደኛ ናቸው ? ይህንን ማወቅ ተችሏል ወይ ?

👉 በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ / መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/ መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር መቅደም አልነበረበትም ወይ ?


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ለእነዚህ ጥያቄዎች የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ ፤ ሥራው በሂድት የሚረጋገጥ እንደሆነ፣ ተፈናቃዮቹ ለመመለስ ፈቃደኛ እንደሚሆኑ፣ ድርድሩ የበላይ አካላትን እንደሚመለከት መልሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " ከቄያቸው፣ ከንብረቱ ተፈናቅሎ ያለ ሰው ዳግም ወደቄየው መመለስ ይፈልጋል የሚል እምነት አለኝ። ተቸግሮ እንጅ ፈልጎ የመፅዋች እጅ ለመጥበቅ የሚፈልግ ይኖራል ብለን አናስብም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#በተጨማሪ ፦ ለአማራ ክልል ኮሚኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ አሁንም ድረስ በንጹሐን ላይ ግድያ እየተፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች በሚገልፁበት ወቅት ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቦ ፤ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን መንገድ ሁለታችንም አንሰራም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Amahra

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል።

የሟች ቤተሰቦች በሰጡቅ ቃል የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፦

- " ፋኖን ታስጠልላላችሁ " ፣

- " ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ "

- " እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ " በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ገልጸዋል።

አሁን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በዛሬው ዕለት በትክክል የተገኘ እንደሆነ እና በሰዓቱም በጉባኤ ቤቱ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ወደተለያየ አቅጣጫ ስለተበታተኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ከ12 ያላነሱ የአቋቋም ተማሪዎች በአዴት ፍልሰታ ደብር ተገድለው እንደነበር ተገልጿል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስለ ጉዳዩ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። #ተሚማ

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም " ማንነታቸው አልታወቀም " የተባሉ #ታጣቂዎች አንድ መነኩሴ ሲገድሉ የገዳማት ንብረት ተዘርፏል።

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት ገዳማት " ማንነታቸው ያልታወቀ  ታጣቂዎች " ባደረሱት ጥቃት አንድ መነኩሴ ሲገደሉ የገዳማቱ ንብረቶች እንደተመዘበሩ ተገለጸ።

ሀገረ ስብከቱ ስለጉዳዩ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ምን አለ ?

- በሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም በሀ/ስብከቱ በሚገኙት በተለያዩ ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ጦርነትና እየተፈጠረ ባለው ግጭት ብዙ ጉዳት ደርሷል።

- በማቻክል ወረ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 27 / 2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-

1ኛ. የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት

2ኛ. የገዳሙ መጠበቂያ የሆኑ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፤

3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፤

4ኛ. ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን

5ኛ. ለመነኮሳቱ በየጊዜው የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ

6ኛ. ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5

7ኛ. አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች

8ኛ. የጥበቃ ክፍሉን መጽሐፍና ብር 2000.00 በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል።

- በአዋባል ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢያ ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የተፈጠረ ችግር ጥር 27 ለ28 አጥባህ ከሌሊቱ በ6፡00 ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ በቁጥር 5 የሆኑ ታጣቂዎች ገዳሙ ውስጥ ገብተዋል።

2 ክላሽ ጠበንጃ ፣ 1 ገጀራ ፣ 1 ሽጉጥ ፣ 1 አለንጋ የያዙ ታጣቂዎች የገዳሙን አበምኔት ቤት እንዲያሳዩአቸው ዘበኞችን በማፈን ይዘው መ/ሃይማኖት ቆ/አባ ሊባኖስን ፀበልተኛ እንደታመመ አስመስለው " ክፈቱ " ሲሏቸው " እኔ አልከፍትም " ወደ አባ ገ/ሕይወት ሂዱ ሲሉ ይነግሯቸዋል።

አባ ገ/ሕይወትም ጋር ሄደው በመሳሪያ አስገድደው ወደ ገዳሙ አባት መጋቢ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ሊባኖስ አስታጥቄ በድጋሚ ሄደው " ክፈቱ " ሲሏቸው " ያለ ሰዓት አይከፈትም " የሚል ምላሽ ሲመልሱ የቤቱን በር በ5 ጥይት ደብድበዋል።

በድጋሚ የካቲት 20 ለ21 አጥቢያ ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ከገዳሙ ገብተው የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶች7 ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው፦

👉  አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው #ገድለዋቸዋል

👉 ዲ/ን ዮሐንስ እና አብርሃም አያና ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል።

👉 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል።

በቁጥር ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ወስደዋል።

በዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያኗ፣ በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጓጉሳ እሽኩዳዶ ወረዳ፣ “ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ንጹሐንን ገድለዋል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ በአካባቢው ከ16 በላይ ንጹሐን መገደላቸው እና ከ37 በላይ ወጣቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አመልክተው " ይንን ያደረጉት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ናቸው " ብለዋል።

ግድያው የተፈጸመው አሽፋ ማርያም፣ አሽፋ አዲስ ዓለም እና ወንጀላ በሚባሉት ቦታዎች ከሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ ጠቁመዋል።

አሽፋ ቀበሌ 8 ሰዎች መገደላቸውን ከ8ቱ 2ቱ ቄሶች እንደሆኑ አንዲት እመጫትም ከእነ ልጇ እንደተገደለች ቀሪዎቹ ደግሞ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ በወረዳው ' ፋኖዎች ' እንደነበሩ ከዛ በፊት መከላከያ እንዳልገባ ፤ ያለፈው እሁድ ግን ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ ከገባ በኋላ እዛ የነበሩ ፋኖዎች ምንም ሳይታኮሱ ነው ቦታውን ለቀው እንደሄዱና ከዛ በኋላ ንጹሐን እንደተገደሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የነዋሪዎቹን ቃል ይዞ የዞኑን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢሻውን አነጋግሯል።

" ነዋሪዎች ከ16 በላይ ንጹሐን ተገድለዋል፣ ከ37 በላይ ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል " ብለዋል ይህ ለምን ተደረገ ? በማለት ጠይቀናቸዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " እኔ የጸጥታ ኃላፊ ሆኘ የምመራው አካባቢ ላይ የደረሰ ማንኛውም አይነት ጥቃት የለም። ኦፕሬሽን የተሰራበት አሽፋ ቀበሌ ነው። በስነ ስርዓት የጽንፈኛ ካምፕ ነው የወደመው " ብለዋል።

" ሐሙስ በነበረው ኦፕሬሽን ላይ በተመሳሳይ ከዛ የተረፈው የታጠቀ ኃይል እንጂ መንግስት የቆመው ለንጹሐን ህዝብ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ታዲያ ሳይገደሉባቸው ማልቀስን ከየት አመጡት ? በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ " ንጹሐን ሰዎች አልተጎዱም " ብለው ፤ " የጸጥታ ኃይል ላይ ብረት ያነሳ፣ የተኮሰ ኃይል ሰላማዊ ኃይል ነው ብለን አናምንም " ሲሉ መልሰዋል።

እንደ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊነትዎ የሞቱ ንጹሐን እንዳሉ ያውቃሉ ? ወጣቶቹስ የት ገቡ ? ለሚለው ጥያቄ ፥ " የሞቱ ሰዎች ፅንፈኞች ናቸው በእኛ እውቅና። ነገም እንዲህ አይነት እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

አክለው፣ " ሐሙስ በነበረ ኦፕሬሽን ላይ 3 ሰዎች በውጊያ መካከል ተይዘዋል። ሰላማዊ ሰዎች ናቸው፤ አሉ በሕይወት። ሕጋዊ የማጣራት ሥራ ይሰራባቸዋል። 37 ሰዎች አይደሉም " ነው ያሉት።

" ከዚያ ውጪ አሽፋ ላይ ደግሞ የተያዘ ሰው የለም። በውጊያ መካከል እርምጃ የተወሰደበት ሰው ሊኖር ይችላል " ያሉት ኃላፊው፣ " ውጊያ መካከል ንጹሐን ላይ ጉዳት አይደርስም ማለት አይደለም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል ፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ፤ ጅጋ ከተማ እሁድ እለት ከቀኑ 11:30 ገደማ ሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የአካባቢዎች ነዋሪዎች በርካታ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይል መገደላቸውን ከሟቾቹ ውስጥ ከባንክ ሰራተኞች እንዳሉበት ጠቁመዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ቃል ፥ አንድ ባለ አንድ ጋቢና መኪና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎችን ጭኖ ከደምበጫ ወደ ፍኖተሰላም ሲጓዝ ጅጋ ፀደይ ባንክ አካባቢ በ ' ፋኖ ' ታጣቂዎች የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞበታል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን አድርሰው ወደጫካ ካፈገፈጉ በኃላ ከጥቃቱ በኃላ የደረዱ ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎች ግድያ መፈጸቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል።

አንድ ነዋሪ ፥ " ድንገት ምንም ሳናስበው ነው አካባቢው በተኩስ የተናወጠው ፤ ከጫካ የመጡ የፋኖ ኃይሎች ናቸው፤ አንደኛውን ፓትሮል ላይ ጥቃት ፈጸሙ ከኋላ የሚከተል ፓትሮል ነበር ' ጎህ ' የሚባል መናፈሻ ነገር አለ እዛ ተኩስ ነበር። ብዙ ሰው ተገደለ። አንድ የአቢሲንያ ማናጀር፣ አንድ የአዋሽ ባንክ አካውንታት ፤ አንድ ምንም የማትናገር ዝናሽ የምትባል ሴት አጠቃላይ 13 ሰዎች መጠጥ የሚጠጣ፣ በቦታው የነበረ ተመቷል የመዝናኛ / የእረፍት ቀን ነበር። የሞቱት ከጫካው ኃይል ወይም ከተማው ውስጥ ካለው የጸጥታ ኃይል ገለልተኛ የስራ ሰው ነው " ብለዋል።

ሌላ ነዋሪ ፥ " የተኩስ ልውውጥ ነበር። መጀመሪያ ' ፋኖ ' ነበር የተኮሰው ፤ አጋጣሚ ሆኖ በፓትሮሉ ላይ ከነበሩት የሰራዊት አባላት አንድ ስናይፐር ተኳሽ አንድ ጥቁር ክላሽ የያዘ ልጅ ከመኪናው ፈጥነው ዘለው እነሱ ብቻ ነው የቀሩት ፤ ከዛ ከኃላ ሲመጣ የነበረ ሌላ የጸጥታ ኃይል ' ጎህ ' የሚባል የመዝናኛ አካባቢ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የባንክ ሰራተኞች ፣ መምህራን የነበሩበት እዛ ያገኙትን በአሰቃቂ ሁኔታ በብሬን ገድለዋል። የሟቾች ቁጥር ከ20 ይበልጣል ነው እንደሰማነው። የአብዛኞቹ በየአካባቢያቸው ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል " ሲሉ ተናግረዋል።

የጅጋ ከተማን እና የአካባቢውን ህዝብ ወክለው የተመረጡት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠናቋል በተባለበት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደምም በሌሎችም ከተማዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ስለሚደረስ ግድያ በተለያዩ መድረኮች መናገራቸውን አስታውሰው " ግን ሃሳባችን ሳይሰማ ቀርቶ ይሄ ሆኗል " ብለዋል።

" በጣም የሚያሳዝነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠናቋል የሽግግር ፍትህ ይኖራል ምክክር ኮሚሽን ስራውን ይሰራል ከታጣቂዎች ጋር ድርድር እና ውይይት ይደረጋል በተባለበት ሰዓት ይህ መፈጠሩ ያሳዝናል " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ አበባ በዕለቱ ተገድለዋል ያሏቸውን የ13 ሰዎች ስም ዝርዝር በእጃቸው እንዳለ ይህን ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መላካቸውን አሳውቀዋል።

የም/ቤት አባሉ ፥ " በክልሉ በመንግስት የጸጥታ ኃይል እና በፋኖ መካከል የሚደረገው ውጊያ ህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ሁለቱም ኃይሎች ወደ ድርድር ሊመጡ ይገባል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሁኔታው እየተጣራ ነው ብሏል።

የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ለማድመጥ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደወለም አላነሱም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን ' ታጣቂዎች ' ባደረሱት ጥቃት አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛን ጨምሮ 3 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በጥቃቱ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የጥቃቱ ባለፈው እሁድ ሰኔ 9/2016 መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃት የተፈጸመው ከገንደ ዉሃ ወደ ነጋዴ ባህር ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ " ደረቅ አባይ " በተባለ ስፍራ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጥቃቱ ከቀኑ 10 ሰዓት መድረሱን አሳውቋል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኃላ አንድ ውስጥ የነበረ የመንግስት የጸጥታ አባል ወርዶ የታጣቂዎቹ ጥቃት ለመከላከል ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመኪናው ውስጥ የነበረች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን አስረድቷል።

" የጥቃቱን መድረስ ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ኃይል በአፋጣኝ ባይደርሱ ኖሩ ከአሁኑ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊከሰት ይችል ነበር " ሲልም ገልጿል።

የተፈጸመው ጥቃት በዘፈቀደ እንጂ በስደተኛዋ ላይ ያነጣጠረ እንዳልነበር አክሏል።

ስደተኛዋ በወቅቱ ፤ መድሃኒት ገዝታ ወደ መጠለያዋ እየተመለሰች ነበር ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያቸው እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም አንዳንዶቹ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው  ለአደጋ እየተጋለጡ ሲል ገልጿል።

የመረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
#Amahra

" ከ4 በላይ ወረርሽኞች ተከስተዋል። ከ2,400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል። ከፍተኛ ሞት አለ " - የዋግኸምራ ብሔረሰብ ጤና መምሪያ

በአማራ ክልል ፤ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከተከሰተ በሰነበተው ድርቅ ሳቢያ ከአራት በላይ ወረርሽኞች መከሰታቸውን ተከትሎ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊው አቶ አሰፋ ነጋሽ በሰጡት ቃል፣ " ከ4 በላይ ወረርሽኞች ተከስተዋል። ከ2,400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል። ከፍተኛ ሞት አለ " ብለዋል።

በወረርሽኙ ምን ያህል ሰዎች ሞተዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ሞቱ ከፍተኛ ነው። ቁጥሩን Specifically ለመናገር እርግጠኛ አይደለሁም " ነው ያሉት።

ቢያንስ ከ5,000 በላይ እንስሳት እንደሞቱ፣ ለመከተብ አቅም እንዳልተገኘ፣ በሽታው (አባሰንጋ) ከእንስሳት ወደ ሰው እየተላለፈ መሆኑን ገልጸው፣ ከአንድ ወረዳ ብቻም ወደ  140 ሰዎች አባሰንጋ እንደተላለፈባቸው አስረድተዋል።

- ኮሌራ
- ኩፍኝ
- እከክና
- አባሰንጋ (የከብት በሽታ) እና ሌሎች ወረርሽኞች በሁሉም በሚባል ደረጃ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ላይ ተከስተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

" ኩፍኝ በሁሉም ወረዳዎች ተከስቷል። በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ህፃናት ታመውብናል " ያሉት አቶ አሰፋ፣ " ለወረርሽኙ ምላሽ ክትባት እየሰራን ነው " ብለዋል።

" እከክ በተለይ ድርቁ በስፋት ባጠቃቸው ወረዳዎች ተከስቶ ነበር ለመቆጣጠር እየተሞከረ ነው። የውሃ አቅርቦት፣ የንጽህ እና መጠበቂያ ግብዓት ካልቀረበ እሱንም መቅጣጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው " ነው ያሉት።

ድርቅ ከመከሰቱ በፊትም አካባቢው ትርፍ አምራች ስላልነበር የምግብ እጥረት እንደነበር አሁን የድርቁ መከሰት የምግብ እጥረቱን እጅጉን እንዳባባሰው ፤ የሥርዓተ ምግቡን ችግርም መቀልበስ እንዳልተቻለ አስረድተዋል።

ሞቱን ለመከላከል የሚሰጠውን ህክምና አጠናክረው እንደቀጠሉ የገለጹት ኃላፊው፣ " በተለይ መካከለኛ የምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናትና እናቶች ተደራሽ ለማድረግ የጸጥታ ችግሩ በጣም አስተቸጋሪ ሆኗል " ብለዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታዎች እንደተቀዛቀዙ አስረድተው፣ " በጸጥታ ምክንያት ተደራሽ ያልሆኑ እናቶችና ህጻናት ምንም እየተደረገላቸው አይደለም " ብለዋል።

ያለው የምግብ እጥረት በቋሚነት ካልተቀረፈ ችግሩን መቀልበስ ፈተና ስለሆነ አጋር ድርጅቶች ርብርብ ኦንዲያደርጉ ዞኑ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Amhara

" የፋኖ ኃይሎች ወደ ድርድር መግባትን በመርህ ደረጃ ይቀበሉታል፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ላይ እምነት የላቸውም " - የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል

በአማራ ክልል በሚፋለሙት የፌዴራል መንግሥት እና የፋኖ ኃይሎች መካከል ያለው ሥር የሰደደ አለመተማመን ሰላም ለማውረድ የሚያደረገው ጥረት ፈተና እንደሆነበት፣ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አስታውቋል።

የካውንስሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ምን አሉ ?

(ለሪፖርተር ጋዜጣ)

- የፌዴራል መንግሥት አመራሮችን ለማግኘት ጥረት ተደርጎ ነበር ግን አልተሳካም። እስካሁን ከፌዴራል መንግሥት በኩል ተገናኝቶ መወያየት የተቻለው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ብቻ ነው። የሰላም ሚኒስቴርም ካውንስሉ የሚያቀርበውን ጥሪ እንደሚቀበል አሳውቋል።

- ከተለያዩ የፋኖ ኃይሎች ጋር ንግግር ተደርጓል። ወደ ድርድር መግባትን በመርህ ደረጃ ይቀበሉታል፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ላይ እምነት የላቸውም። ' ጊዜ መግዣ ነው ' ብለው ያምናሉ፣ እኛንም የፈተነን ይኸው ያለመተማመን ችግር ነው።

- ከፌዴራል መንግሥት በኩል ካውንስሉ ተጨማሪ ሥራዎች ይጠብቁታል። የፌዴራል መንግሥት ለሰላም ዝግጁ መሆኑን መናገር ብቻ ሳይሆን ምቹ ሁኔታን መፍጠር አለበት።

- በሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች መካከል መተማመንን ለመፍጠር ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እገዛ ለማግኘት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር፣ ከኢጋድና ከአፍሪካ ኅብረት አመራሮች ጋር በቅርቡ ውይይት ተደርጓል።

- ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ንግግር ተደርጓል፤ እነሱ ለማገዝም ዝግጁ ናቸው። በካውንስሉ በኩል ደግሞ እየደረሰ ካለው ጉዳት አንፃር " የአማራ ክልል ሁኔታን ችላ ብላችሁታል " ብለናቸዋል።

- የአሜሪካ አምባሳደርን ጨምሮ ከስድስት ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የክልሉን የሰላም ዕጦት ችላ ማለታቸውን ተጠቁሞ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ማሳደር እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ካውንስሉ የሚያደርገውን ጥረትም ሆነ ድርድሩ እንዲሳካ ለማገዝ ፈቃደኛ ነው። ነገር ግን በፋኖ አደረጃጀት ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡ 

ካውንስሉ አግኝቼ አናገርኳቸው የሚላቸው የፋኖ ኃይሎች እነማን ናቸው ? የትኛውን የአደረጃጀትስ ነው ያናገረው ? ለዚህ ጥያቄ ፦

" ይህንን መናገር አያስፈልግም፣ ምክንያቱም አንዳንዶች ነገሩን ' እገሌ ሊደራደር ነው ' በማለት መበሻሸቂያ አድርገውታል፡፡ በመሆኑም ከየትኛው የፋኖ አመራር ጋር እንደተወያየን መግለጽ ጠቃሚ አይደለም።

' እገሌ ሊደራደር ነው ' የሚለውን ጉዳይ የፋኖ ኃይሎች እንደ መበሻሸቂያ እየተጠቀሙበት ስለሆነ፣ ካውንስሉ የተደራጀ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በፋኖ በኩል እገሌ እንዲህ ብሏል ከማለት እንቆጠባለን። " ሲሉ መልሰዋል።

የፋኖ ኃይሎች ድርድርን በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉት ነገር ግን " የፌዴራል መንግሥት ድርድሩን እንደ ጊዜ መግዣነት ሊጠቀምበት ነው " የሚል እምነት እንዳላቸው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ካውንስሉን" ሀቀኛ ድርድር ለማድረግ ሳይሆን ለማምታታት ነው " የሚል ሐሳብ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

ይሁንና አለመተማመኑን ለመቅረፍ የሁሉንም አካላት ቅንነት ካውንስሉ እንደሚፈልግ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል አመላክቷል።

#Amahra #Ethiopia

@tikvahethiopia