TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbabaPoliceCommission

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ትምህርት ቤት ጀርባ ዛሬ ከቀኑ በግምት 8:30 ሁለት ህፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦንብ ሲነካኩ ፈንድቶ የአምስት ዓመት እድሜ ያለው ህፃን ፀጋዬ ተክለማርያም ህይወቱ ሲያልፍ የአምስት ዓመቱ ህፃን ግዛው አንተንአየሁ በእግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እንደተደረገለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የገና በዓል በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ “የመዲናዋን ሠላምና ጸጥታ ለማስከበር ከወጣቶች ጋር እየሰራሁ ነው” ብሏል።

ኅብረተሰቡ በዓሉን በሠላማዊ ሁኔታ እንዲያከብር ለማድረግ ከሃይማኖት አባቶችና ከወጣቶች ጋር ውይይት እንደተካሄደ አሳውቋል።

ፖሊስ የወቅቱን የፀጥታ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ጥበቃ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቆ ፥ ሕዝቡ በዓሉን ለማክበር ሲንቀሳቀስ ስጋት እንዳይገባው እየሰራን ነው ብሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በዓሉ በሠላም እንዲከበር ከፖሊስ ጋር መተባበር ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ~ ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AddisAbabaPoliceCommission

የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የ2013 ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

ለውድድሩ በሰላም መጠናቀቅ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት፤ የፕሮግራሙ አዘጋጆች እና የተሳታፊዎች ላደረጉት ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሠላም መጠናቀቁን አስታውቋል፤ ህብረተሰቡ ለበዓሉ በሠላም መጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋፅኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ228 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና ከ85 ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት አደረኩት ባለው ክትትል ነው ገንዘቡን በቁጥጥር ስር ያዋለው።

ገንዘቡን በቁጥጥር ስር የዋለው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው "መናኸሪያ ግቢ" ውስጥ ነው።

ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ 2 ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሲዘጋጁ ግንቦት 10/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሠዓት ገደማ በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ብርበራ በላስቲክ ተጠቅልሎ የተቀመጠ 205 ሺህ 512 የአሜሪካ ዶላር ተይዟል።

በተጨማሪ የተለያዩ የባንክ ሰነዶችና ፓስፖርት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ መረጃ ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥናት ላይ ተመስርቼ አከናወንኩት ባለው ተግባር ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 11/2013 ዓ/ም በግምት 9 ሰዓት ገደማ ለህገ ወጥ ዝውውር የተዘጋጀ 23 ሺ 300 የአሜሪካ ዶላር ፣ 85 ሺ 600 የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም 17 የተለያዩ የኤ.ቲ.ኤም ካርዶች እና 29 የተለያዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር እንደያዘ ሪፖርት አድሯል።

በአጠቃላይ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሰኔ 3 ቀን 2013 በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚደረግ እየተላላፈ ያለው መረጃ የተዛባ ነው ብሏል።

ኮሚሽኑ፥ ህገወጥ ስብሰባ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳውያን ለወጣቶችና ጎልማሶች ማህበራት ሕብረት በቁጥር ዘ1(1) 804 - መ1-13 -10 ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ/ም በፃፈው ደብዳቤ የኮቪድ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ በአዳራሽ ስብስባ እንዲደረግ እንደፈቀደ ነገር ግን በማይመለከታቸውና እና ውክልና ባልተሰጣቸው አካለት በስህተት በመስቀል አደባባይ ስብሰባው እንዲደረግ የተሰጠው ፈቃድ አግባብ አለመሆኑን ለኮሚሽኑ በግልባጭ አሳውቋል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎችና በከተማው በተለጠፉ ማስታወቂያዎች ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ/ም ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ህዝባዊ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የሚገልፅ መረጃ እየተሰራጨ ቢሆንም ፤ የሰላም ሚ/ር ስብሰባውን በመስቀል አደባባይ ማደረግ የማይቻልበትን ዝርዝር ሁኔታ ለጥያቄ አቅራቢዎቹ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ፥ በተጠቀሰው እለት በመሰቀል አደባባይ ይካሄዳል የተባለው ስብሰባው በከተማ አስተዳደሩም ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅንጅት በጥቁር ገበያ ሊሸጥ የነበረ ሽጉጥና የተለያዩ ጥይቶችን ከእነ ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡

ከእህል ጋር ተደባልቆ ወደ ክልል ሊጓጓዝ የነበረ ጥይትም በህብረተሰቡ ትብብር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሁለቱ አካላት ከህብረተሰቡ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ባደረጉት ክትትል ሦስት ግለሰቦች በቢጫ ታክሲ፦
- 25 ቱርክ ሰራሽ ኢኮልፒ ሽጉጥ ፣
- 586 ፍሬ የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣
- 69 ፍሬ የብሬን ጥይት በጥቁር ገበያ በመገበያየት ላይ እንዳሉ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ዘነበወርቅ አካባቢ ሀምሌ 28 ቀን 2013 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ሀምሌ 23 ቀን 2013 አንድ ግለሰብ 730 ፍሬ የክላሽን ኮቭ ጥይት ከገብስ ጋር በመቀላቀል ወደ ስልጤ ዞን ለማዘዋወር ሲሞክር በዘነበ ወርቅ መናኸሪያ ተይዟል፡፡

በጥቁር ገበያ የጦር መሳሪያ ሲገበያዩ የተገኙት ሦስት ተጠርጣሪዎችና የክላሽን ኮቭ ጥይት ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ ታስረው ጉዳያቸው እየተጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፦

1ኛ. በከተማ ደረጃ የደመራ ስነ-ሰርዓት ወደ ሚከናወንበት መስቀል አደባባይ ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ፣ ስለታም ነገሮችን እና ህገወጥ ቁሳቁሶችን ይዞ መምጣት የተከለከ ነው።

2ኛ. ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር ሁሉም ህብረተሰብ ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል።

3ኛ. በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የደመራ ፕሮግራምን መጠናቀቅ ተከትሎ በከተማው በተለያዩ ደብሮች እና መንደሮች ደመራ የማብራት ስነ-ስርዓት የሚካሄድ ሲሆን  በየአካባቢው ደመራ ሲበራ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደረግ ይገባል። በማንኛውም ሁኔታ ርችት መተኮስ ፍፁም ክልክል ነው።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም 0111110111፣ 0111264359፣ 0111010297፣ መጠቀም ይቻላል።

የሚዘጉ መንገዶች #ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/73882?single

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን  በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው  ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia