TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” - የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው። በአማራ ክልል በ “ፋኖ”…
#Amhara

“ ' 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ' በሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል ” - ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ፤ ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ እንደነበርና ቲክቫህ ኢትዮጵያም መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

በወቅቱ የአማራ ሴቶች ማኀበርን የወከሉት ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ስለሴቶች በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተሳታፊዎችና ኃላፊዎች ገለጻ ሲያደርጉ፣ “ አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች #ተደፍረዋል ” ሲሉ ገልጻ አድርገው ነበር።

ይህንንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቦት እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ፣ ዘገባው ከተሰራ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የወ/ሮ በላይነሽን ገለጻ መሠረት በማድረግ የተዘገበውን ዜና ጠቅሰው፣ “ የእናንተ ስህተት አይደለም በእርግጥ የልጆቷ ስህተት ነው ” ብለው ዘገባው #ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።

ወ/ሮ በላይነሽ በስብሰባው ላይ ያደረጉት ገለጻ የድምጽ ቅጅ እንደገና ሲረጋገጥ፣ “ 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ” የሚል ሆኖ እያለ፣ መረጃውን የት እንዳገኙት እንዲገልጹ የአማራ ሴቶች ማኀበር ሲጠይቃቸው፣ “ ‘4 ሺህ የተባለው እንደ ኢትዮጵያ የቀረበ እንጂ እኔ አላልኩም፣ 400 ነው ያልኩት " ሲሉ ለመካድ እንደሞከሩ ያስረዱት ም/ዳይሬክተሯ፣ “ 400 ከየት አመጣሽ ? ሲባል ‘ከሴቶች ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ሲባል ሰምቼ ነው’ የሚል ሀሳብ ነው ያመጣች ግን 400ም የእኛ መረጃ አይደለም ” ብለዋል።

አክለው “ የ6 ወራት ሪፓርታችንም ‘ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን’ ብለው ተቋማችን ድረስ የመጡ 4 ሴቶች ናቸው። እነዚያን ሴቶችም ሁለቱን ሰጥተናል። ሁለቱን ከፓሊስ ጋ ሁነን ገና በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ አንድ ሰው ከአንድ ተቋም ሲላክ ታምኖበት፣ ዘርፉን ያውቀዋል ተብሎ ነውና የሚላከው ባለሙያዋ የተናገረችው ስህተት መሆኑን እንዴት ነው የምታረጋግጡልኝ ? የሚል ጥያቄ ለም/ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሁሉአየሽ አቅርቧል።

“ እውነት የምነግርህ እኔ ምክትል ዳይሬክተር ነኝ ፤ ልጅቷ ፕላንድ የሚባል ፕሮጀክት አለ የእርሱ አስተባባሪ ነች ” ያሉት ም/ ዳይሬክተሯ፣ “ ዙሮ ዙሮ ግን እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ክልሉ ያለበት ሁኔታ ይታወቃል። ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊሆንም ይችላል፣ ሊያንስም ይችላል፣ ስትሰበስበው ነው የምታገኘው ” ሲሉ አስረድተዋል።

ተቋማቸው መልዕክቱን በሰነድ መልኩ እንዲልክ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጠይቀው ምክትል ዳይሬኮተሯ ፈርመው የላኩት ደብዳቤ ፦

- " ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ' በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 4,000 ሴቶች ተደፍረዋል ' የሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል " ይላል።

- ክልሉ በዚህ ወቅት በግጭት ላይ በመሆኑ በሴቶች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ቢገመትም ተቋሙ ግን ታች ድረስ ወርዶ መረጃ ለመሰብሰብ ባለው ግጭት ምክንያት ምቹ ሁኔታ ስለሌለና ኢንተርኔት በመዘጋቱ ምክንያት መረጃዎችን ሰብስቦ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ይገልጻል።

* የተባለው መረጃው በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ፤ ምቹ ሁኔታን ሲገኝ ታች ወርዶ ያረጋገጥነውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደሚያሳውቅ ያመለክታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረጉት ገለጻ ስህተት እንደሆነ የተነገረላቸው ወ/ሮ በላይነሽን በድጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#AATikvahFamily

@tikvahethiopia