TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንድማችን⬆️እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ኤርትራዊ ወንድማችን የሀገሩን #ጥሪ አስመልክቶ ካየው ዜና ጋር በተያያዘ አስተያየቱን ልኮልኛል። #ምንም ሳልጨምር ሳልቀንስ አስተያየቱን ወደናተ አቅርቤዋለሁ⬇️
.
.
Hii,Tesgsh thank you for everything you are doing. I am Eritrean. I live in Ethiopia. We need complete political change. Post this one on behalf of all Eritreans.

We need...

1.The constitution to be implemented

2.Rule of law should be respected

3.Innocent Eritreans in different prisons should be released.

4.The regime should apilogize for what it did in the last 20 years.

5.Our war heroes the so-called G-15 and journalists and other political prisons should be freed.

6.Religious fathers should be released

8.etc...

All in all complete political should be safeguarded. If you,tsegish, love the Eritrean people, do that for me and the Eritrean people. Post it in your information center. Thank you!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የከዱ (የኮበለሉ) አባላት እና የፖሊስ አመራሮች መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን #ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጁ መሰረት እስከ ግንቦት 30/2010 ዓመተ ምህረት ድረስ ከሰራዊቱ የከዱ አባላትና አመራሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የኮበለሉት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ከነሀሴ መጨረሻ ጀምሮ በመጪዎቹ ስድስት ወራት በምህረት አዋጁ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ የህግ ጉዳይ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲል_አሻግሬ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች በመገኘት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በክልል የሚገኙት ደግሞ ለክልላቸው ፍትህ ቢሮ ሪፖርት በማድረግ በምህረቱ ተጠቃሚ መሆኑን እንደሚችሉ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ አባላት እና አመራሮች ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ደብዳቤ ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ሌላ የስንብት ደብዳቤና የስራ ልምድ ማግኘት እንደሚችሉ ታውቋል።

የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑ አባላት የወሰዱትን የመንግስት ንብረት ሪፖርት ለሚያደርጉበት ተቋም በመመለስ የነጻነት የምስክር ወረቀት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ሆኖም በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ ፖሊሶች ወደ ስራ ቦታ እንደማይመለሱ የስራ አመራር ውሳኔ እንዳሳለፈ ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#update የመግቢያ ጊዜ⬇️

የ2011 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በትምህርት ፍኖተ- ካርታ ውይይት ምክንያት #መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ በሚደረገው ውይይት ምክንያት የ2011 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ #ሀረግ_ማሞ አስታውቀዋል።

መንግሥት በቅርቡ አዲስ ባዘጋጀው ረቂቅ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ የተጀመረው ውይይት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ስለሚደረግ ቀደም ብሎ ተላልፎ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪ መራዘሙን ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከመምህራኖቻቸው እና ከአስተዳደር ሠራተኞቻቸው ጋር በረቂቅ ፍኖተ-ካርታው ላይ ውይይት አድርገው ሲያበቁ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እንደ የዩኒቨርሲቲዎቹ መርሀ-ግብር የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ የቆየ ቢሆንም ውይይቱ እየተካሄደ በመሆኑ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ባለፉት ሁለት ወራት ውይይት ሲደረግበት የቆየው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ ጥናት ግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማኅበረሰብ አባላት ጋርም በዛሬው ዕለት በመላ አገሪቱ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በመሆኑም ውይይቱ ሲጠናቀቅ በማዕከል በኩል ለሁሉም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #ጥሪ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያለመ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር #ውይይት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥሪ_ማሳመሪያ ጥሪት ያተርፋል!

የመኪና፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ስማርት ቴሌቪዥኖች፣ የ5ጂ ስማርት ስልኮች፣ በርካታ የ5ሺህ ብር እና የሞባይል ጥቅል ሽልማቶች አሸናፊ ለመሆን:

ወደ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ከ 645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ።

መልካም ዕድል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#ኢትዮቴሌኮም

የመጀመሪያዋ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ደብረታቦር ገባች !

ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር የጥሪ ማሳመሪያ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ዛሬ አስረክበናል!

🎁 1 የ5ጂ ስማርት ስልክ ለአዳማዋ እድለኛ፣
🎁 2 ስማርት ቴሌቪዥኖች ለአዲስ አበባ እና ለአምቦ እድለኞች እንዲሁም
🎁 1 ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ደብረታቦር እድለኛ አስረክበናል!

በተጨማሪም እስከአሁን 2,352 የድምጽ ጥቅል፣ 1,030 የዳታ ጥቅል፣ 30 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋጋ ያለው የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ  ሽልማት ለዕድለኞች አበርክተናል፡፡

አሁንም ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ወደ 645 Y ብለው በመላክ ለሚደርስዎት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!

#ጥሪ_ማሳመሪያ_ጥሪት_ያተርፋል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” - ሴቭ ዘ ቺልድረን በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው…
#SavetheChildren

“ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች በኩፍኝ ሞተዋል ” - የህጻናት አድን ድርጅት

በሶማሌ ክልል በተለይም #የጎርፍ_አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች በተፈናቀሉ ወገኖች የተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነ የክልሉ የህጻናት አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ፣ የኮሌራ ወረርሽኙ እንደቀጠለ መሆኑን በሴፕተምበር 2023 ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በድምሩ 7, 480 ሰዎች እንደተጎዱ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በሰጡት ቃል፣ “ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ በኩፍኝ ሞተዋል ” ብለዋል።

በተጨማሪም ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ 533 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እንደተያዙ፣ 9ኙ ሰዎች ለሞት የተዳረጉት በጎዴ ከተማ፣ ጎዴ ወረዳ፣ በራኖ አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

📣 በጎርፍ ለተጎዳ ማህበረሰብ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረግ ምላሽ፣ የአደጋ ጊዜ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለማደረግ አቅርቦቶችን ማጎልበት። የኮሌራ ክትባቶች ከፍተኛ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ይገባል።

📣 የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ መሠረታዊ እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወሳኝ በሆኑ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በመገንዘብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የጤና መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ መዋዕለ ነዋይ ሊፈስ ይገባል።

📣 #ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ልዩ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። 

#ጥሪ

(አቶ አብዲራዛቅ አህመድ)

" ለለጋሽ ማህበረሰቡ አንድ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ወረርሽኝ እና ተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚያመጣውን ከፍተኛ ጉዳትና ተጽዕኖ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia