TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጤናሚኒስቴር

አንድ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳየ ግለሰብ በመለያ ማዕከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን እና ናሙናው ተወስዶ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ላብራቶሪ እተሰራ መሆኑን ገልጸን ነበር። ሆኖም በተደረገለት ምርመራ ግለሰቡ ከበሽታው ነጻ መሆኑ በላቦራቶሪ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

የአለም ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ #COVID19 እራሳችንን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ቀላልና ውጤታማ እርምጃዎች፥

- አዘውትሮ በአግባቡ እጅን በሳሙና መታጠብ

- ለሰላምታ በእጅ አለመጨባበጥ

- ፊትን በእጅ አለመንካት

- ትኩሳት፣ ሳል፣ ማስነጠስ ያሉ ምልክቶች ካጋጠሙን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ

- በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉ ጊዜ ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ሌሎችን እንዳይበክሉ መጠንቀቅ

ስለ ኮሮና ቫይረስ መረጃ ለማግኘት በነጻ የስልክ መስመር 8335 ይደውሉ ወይም 0112765340 #COVID-19 update free call 8335 or [email protected]

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ለመከላከል ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?

- ከሚያስነስጥሱ፣ ከሚያስሉ እና ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ

- እጅዎትን በሳሙናና ውሃ አዘውትረው መታጠብ

- አለመጨባበጥ

- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት

#share #ሼር

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ባለሙያ የቅጥር ማስታወቂያ!

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፦

· ጠቅላላ ሀኪም
· ቢኤስ ሲ ነርስ
· ጤና መኮነን
· አከባቢ ጤና አጠባበቅ እና
· ጤና አጠባበቅ ትምህርት

ባለሙያዎችን ለ6 ወራት በኮንትራት በመቅጠርና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ስር ባሉ የጤና ተቋማት ለማሰራት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ በተዘረዘሩ የሙያ ዓይነቶች ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪ ድግር ተመርቃችሁ ወደ ስራ ያልተሰማራችሁ ባለሙያዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ. ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ኦርጅናል የትምህርት ማስረጃ እና የሙያ ፍቃድ የማይመለስ አንድ ኮፒ ይዛችሁ ጤና ሚኒስቴር አንደኛ ፎቅ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

#ጤናሚኒስቴር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

- በአሁኑ ሰአት ከቻይና በተጨማሪ እንደ ጣሊያን፣ ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ እና የመሳሰሰሉ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

- ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሀገራት የሚመጡ መንገደኞችን ቅፅ በማስሞላት እና አድራሻቸውን በመያዝ በስልክ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።

- እስካሁን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 1 ሺህ 20 መንገደኞች ተጨማሪ ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን፥ 1 ሺህ 93 መንገደኞች ደግሞ በስልክ ከትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

- ጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ ቢከሰትም በፈጥነት መቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን፥ የሆስፒታል ዝግጅት፣ የግብአት እና የባለሙያዎች ዝግጅትም በስፋት እየተሰራበት ነው።

- የኮሮና ቫይረስ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን የሚያሳይ እና የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ቫይረስ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ላይ መዘናጋት አንደሌለበት ማሰስቢያ ተሰጥቷል።

- ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ መረጃዎች ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውን በማረጋገጥም የበኩሉን ደርሻ እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- መላው ህብረተሰብ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ቀድሞ ለመከላከል የግል ንፅህናን መጠበቅ እና ንክኪዎችን መቀነስ ላይ ትኩረት ማደረግ አለበት ተብሏል።

- ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር በተያያዘ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት ሆነ መረጃዎችን እና እርዳታዎችን ለማግኘት ወደ 8335 መደወል እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል።

#DrLiaTadesse #ኤፍቢሲ #ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ኢትዮጵያ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው International Community School (ICS) ከነገ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 11 ትምህርት ቤቱን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደሚዘጋ አስታውቋል።

- የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ትክክለኛውን መረጃ በመጠቀም ረገድ ከመንግስት ተቋማትና ግል ማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደርጓል።

- የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ከኢትዮዽያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ እምነቶች ጋር ምክክር አድርጓል።

- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ባለሙያዎች ለማሰልጠን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለህክምና ማዕከላት የሚውል 30 ሚሊዮን ብር አፅድቋል።

- ዛሬ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም የጤና ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ላይ ምክክር አድርጓል። ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ዶክተር ኤባ አባተ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳይገባ እያደረገች ባለው ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

#ጤናሚኒስቴር #አዲስፎርቹን #EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBOT
#ሼር #SHARE

ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው። ዋናው የመተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ወቅት ትንፋሽ ጋር በሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።

እንዴት መከላከል ይቻላል ?

- በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫዎን በክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን!

- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት!

- በውሃ እና በሳሙና መታጠብ፣ አልኮል ነክ በሆኑ የንፅህና መጠበቂያዎች እጅዎን በአግባቡ ማሸት!

- የተጠቀሙበትን ሶፍት በፍጥነት በጥንቃቄ መክደኛ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል!

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ [face mask] የሚከተሉት ሰዎች እንዲጠቀሙት ይመከራል፦

- የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

- ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ስያስለን ወይም ስያስነጠሰን፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

- የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ስሆን ብቻ ነው፡፡ ህብረተሰቡ መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ጤናሚኒስቴር #ፋናብሮድካሲንግ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ከታዩብኝ ምን ላድርግ?

የኮሮና ቫይረስ ሕመም ምልክት (ትኩሳት ፣ ሳል፣ የጉሮሮ ሕመም) የታየባቸው ሰዎች የትም መሄድ ሳይገባቸው 8335 ላይ በመደወል ባለሙያዎች ያሉበት ስፍራ እንደሚመጡ ማድረግ አለባቸው።

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia