TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Wolkite

ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ደቡብ ክልል፣ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ስለማድረጋቸው አሳውቀዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ፤ " የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው። " ያሉ ሲሆን " በዛሬው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለን ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ወልቂጤ ከተጓዙ ባለስልጣናት መካከል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይገኙበታል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቂጤ ጉዞ ጋር በተገናኘ ዛሬ የማህበራዊ መገናኛዎች ትኩረት ሆኖ የነበረው በከተማው የነበረው የእንቅስቃሴ / የስራ ማቆም አድማ እንዲሁም ደግሞ የሚጠበቀውን ያህል የከተማው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ አቀባበል አለማድረጉ ነበር።

በወልቂጤ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ ከተማዋ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ እንደነበር አመልክተዋል ፤ ይህ የሆነውን ህዝቡ እየጠየቀው ካለው #የክልልነት_ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

ምንም እንኳን የዞን ምክር ቤት በክልል መደራጀትን ውሳኔ አሳልፎ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢያስገባም እንዲሁም የክላስተር አደረጃጀትን እንደማይደግፍ በአብላጫ ድምፅ ቢወስንም የክልልነት ጥያቄው ግን ምላሽ እንዳላገኘ ይህ ደግሞ የህዝቡን ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" ህዝቡ መብቱን ነው የጠየቀው ፤ ለዚህ ደግሞ ኃይል ፣ እስር ፣ ማሳደድ፣ ማፈን መልስ አይሆንም መንግሥት አሁንም የያዘውን ግትር አቋሙን መልሶ ማጤን ይገባዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

በዞኑ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ አመራሮችን ጨምሮ በርካቶች ታስረው እንደነበር አይዘነጋም። በተጨማሪ ዞኑ ላይ የአመራር ለውጦችም ተደርገዋል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት ለመክፈል በተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ በወላይታ (እንዲደገም) ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ ዞኖች፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ፣ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ላይ በቅርቡ ህዝበ ውሳኔ መደረጉ ይታወቃል።

አንድ ላይ እንዲቀጥለው የተባሉት ሀዲያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል የጉራጌ ዞን የክላስተር የአደረጃጀትን ውሳኔ ቀደም ብሎ ያልተቀበለው / በምክር ቤቱም በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ያደረገው ዞን እንደነበር አይዘነጋም።

Photo : PM OFFICE & TIKVAH WOLKITE FAMILY

@tikvahethiopia