TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እስካሁን ውጤቱ ያልታወቀው የኬንያ ምርጫ ከምን ደረሰ ?

በኬንያ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከተገኘው ውጤት ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆነው በምርጫ ኮሚሽኑ #የተረጋገጠ ሲሆን ሁለቱ ተፎካካሪ እጩዎች በቅርብ ርቀት በመፎካከር ላይ ናቸው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

እስካሁን በተረጋገጠ ድምጽ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 51 በመቶ ሲመሩ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 48 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ ማክሰኞ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ይፋ ማድረግ በጣም አዝጋሚ መሆኑን አምኗል።

በሁለቱ ዋና ዋና እጩዎች ደጋፊዎች ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎም ውጤቱን የማረጋገጥ ሥራ በተደጋጋሚ ተቋርጧል። 

የራይላ ደጋፊዎች ውጤቱን የማጣራት ሂደቱን በተደጋጋሚ ማስተጓጎላቸው ታውቋል። አንዳንድ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ድምጽ እያጭበረበሩ ነው በማለት ከሰዋል።

እስካሁን ባለስ ከ292 የምርጫ ክልሎች የ141 ቱ ውጤት ተረጋግጧል።

ዛሬም ድረስ የመጨረሻ ውጤቱ የሚታወቅበት ቀን ባይታወቅም የምርጫ ኮሚሽኑ ድምጽ የማጣራት ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

የአሸናፊውን ዕጩ ማንነት የሚያሳውቀው ኮሚሽኑ ይሆናል። 

ምርጫውን ለማሸነፍ ዕጩዎች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የመራጮች ድምጽ ማግኘት እና በ24 ክልሎች ከ25 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። 

ካልሆነ ምርጫው በድጋሚ ጷጉሜ ወር ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
#GebreGuracha

በ " ገብረ ጉራቻ " ከተማ በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን በታጣቂዎች ሲገደል ፤ 11 አገልጋዮች ደግሞ በታጣቂዎች መታገታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ አሳወቀ።

የቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ፤ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ገርበ ጉራቻ ከተማ በምትገኘው በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም ሌሊት የማኅሌተ ጽጌ አገልግሎት ላይ በነበሩበት ወቅት #ታጣቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት አንድ ዲያቆን በመግደል ሌሎች 11 አገልጋዮችን ማገታቸውን ገልጿል።

በአካባቢው ላይ ተደጋጋሚ ችግሮች በመከሰቱ ምእመናን ስጋት ላይ በመሆናቸው ለመንግስት አካላት የማሳወቅ ሥራ ቢሠራም መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋዊ #የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሽፈራው ለተ.ሚ.ማ. በሰጡት ቃል የተፈጠረውን ጉዳይ እንደሰሙና ለዞኑ አስተዳደርና ለጸጥታ ዘርፉ ማሳወቃቸውን አስረድተዋል። በተለይ በቦታው ቅርብ ርቀት ላይ የመከላከያ ካምፕ መኖሩን ገልፀው ጉዳዩ ሲፈጠር የወሰዱት እርምጃ እንደሌለና ጉዳዩም አዲስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ይህ ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ስለሆነ ጉዳዩን ለቤተ ክህነት ማቅረባቸውን በአካባቢያው ለሚገኙ ቀሪ ምእመናን መፍትሔ እንዲሰጥ እንደጠየቁ እና ምላሽም እየተጠባበቁ ስለመሆኑ ለሚዲያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" መግለጫው ዘግይቷል ፤ ነገር ግን ወደ በኃላ ይሰጣል "

ዛሬ ከሰዓት ላይ ሊሰጥ የነበረው የአፍሪካ ህብረት መግለጫ #መዘግየቱን ነገር ግን መግለጫው ወደ በኃላ #እንደሚሰጥ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።

መግለጫው ለምን ሊዘገይ እንደቻለ የተሰጠ ማብራሪያ የለም። ወደ በኃላ ይባል እንጂ ትክክለኛ ሰዓቱም አልተገለፀም።

በደ/አፍሪካ ፕሪቶሪያ እየተካሄደ ካለው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት " የሰላም ንግግር " ጋር በተያያዘ እስካሁን ስላለው ሂደት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሚሰጡት በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕ/ት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ናቸው።

በርካቶች እየጠበቁት ያለው መግለጫ  በደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት #የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ እንደሚተላለፍ  መ/ቤቱ ገልጿል👇
https://www.facebook.com/DIRCOza

@tikvahethiopia