TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስልክአምባ " 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች " 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ ️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።…
#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia