TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ፖሊስ⬇️

በሻሸመኔ ከተማ ዛሬ በተጠራ የድጋፍ ስልፍ በተከሰተ ግርግር እና መጨናነቅ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በግርግሩ በሰው አካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንም ገልጿል።

ኮሚሽኑ በህዝቡ አስተባባሪነት ለድጋፍ ሰልፍ በውጡ ዜጎች ላይ በተከሰተ አለመረጋጋት በተፈጠረው መገፋፋትና መጨናነቅ የሰው ህይወት ማለፉንና ንብረትነቱ የሻሸመኔ አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት የሆነ አንድ መኪና መቃጠሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አለማየሁ እጅጉ ለኢቲቪ ዜና ተናግረዋል።

በተለያዩ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና ድረ ገጾች እየተዘዋወሩ ያሉት መረጃዎች እውነተኛነታቸው ሳይረጋገጥ ወደ #ተሳሳተ ድምዳሜ ስለሚያደርሱ ጥንቃቄ ያስፈልጋልም ብለዋል።

እስከ አሁን ፖሊስ የግርግሩ መነሻ ምክንያት ለማጣራት በምርመራ ላይ መሆኑን ገልጸው በድጋፍ ሰልፉ ከሻሸመኔና ዙሪያዋ ከፍተኛ ቁጥር
ያለው ህዝብ መገኘቱን ገልጸዋል።

ኮሚሽነር ጄኔራል አለማየሁ እጅጉ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ሻሸመኔ ከተማ እና በዙሪያዋ የነበረው ግርግር ተረጋግቶ መደበኛ እንቀቃሴዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ፖሊስም በቀጣይ ቀናት ምርመራውን በማጠናቀቅ #ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ለማቅረብ ይሰራል ብለዋል።

ሕብረተሰቡም በመረጋጋት #ትክክለኛ_መረጃዎችን ከፖሊስ እና የጸጥታ ሀይሉ ማግኘት እንደሚገባው አሳስበዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia