TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የDAS ተሸላሚ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የዘንድሮው የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን (DAS) ተሸላሚ ሆነዋል።

ፋውንዴሽኑ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው ዶ/ር ዳንኤል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ላበረከቱት የህይወት ዘመን አስተዋፅኦ ከፍተኛውን ሽልማት ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል።

ዶ/ር ዳንኤል ከ30 ዕጩዎች መካከል #በሙሉ_ድምፅ የተመረጡ ሲሆን ሽልማታቸውንም በኅዳር ወር እንደሚቀበሉም ተገልጿል።

ዶ/ር ዳንኤል ኮሚሽኑ ነፃ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ፋውንዴሽኑ አሳውቋል።

ሽልማቱ "የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከፍተኛ ደረጃ እንዲለወጥና ገለልተኝነቱ እንዲረጋገጥ ፣ ሥልጣንና ኃላፊነቱ እንዲሰፋ ለተጫወቱት ቁልፍ ሚና እውቅና የሚሰጥ" መሆኑ ተገልጿል።

ከ25 ዓመታት በላይ በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው ይህ ሽልማት ፣ በሙያቸው የላቀ አመራር ላሳዩና ለእድገትና ለመሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ ነው።

Credit : EHRC

@tikvahethiopia