TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አክሱም ዩኒቨርሲቲ...
.
.
.
አለመረጋጋቱ የተከሰተው ባለፈው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምክንያቱ እስካሁን ባልታወቀ ድርጊት የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን ተከትሎ የተወሰኑ ተማሪዎች በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አመጽ ለማስነሳት በመሞከራቸው ነው ተብሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎቹ ድርጊት ተገቢነት እንደሌለው ሲመክር ቢሰነብትም ግጭት ተፈጥሮ የአንድ ተማሪ ሕይወት አልፏል፡፡

ግጭት እንደቀሰቀሱ ታምኖ እርምጃ የተወሰደባቸው ተማሪዎች እንዳሉና እርምጃው ተገቢ አለመሆኑን #በመቃወም ሌሎች ተማሪዎች ማታ ማታ ይረብሹ እንደነበርና ከትናንት ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ቀን ላይ ግጭት መቀስቀሱን በስፍራው የሚገኙ የዓይን እማኞች ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡

በዚህም የአንድ ተማሪ ሕይወት አልፏል፡፡ ተማሪዎቹ ግን ሁኔታው #ስላልተረጋጋ ስንት ተማሪዎች እንደተጎዱ መረጃ እንደሌላቸው ነው የተናገሩት፡፡

አሁን ላይ ሁኔታውን ለማረጋጋት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባታቸውንም ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት፡፡
.
.
የትግራይ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች ቢሮ የአንድ ተማሪ ሕይዎት ማለፉን #ከመስማት ውጪ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሌለው ነው ያሳወቀው፡፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሁኔታውን ለማረጋጋት ከተማሪዎች ጋር ዛሬ ጥዋት ተወያይቷል።

ምንጭ፦ አብመድ
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia