TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሬዚደንት #JU

“ የ3 ወራት ያህል ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬዚደንት ሀኪሞች

“ ይህ ጉዳይ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው ” - ዩኒቨርሲቲው

በ2016 ዓ/ም በጤና ሚኒስቴር #በጅማ_ዩኒቨርሲቲ  ተመድበው በሆስፒታሉ ሥራና ስፔሳላይዜሽን ስልጠና የሚወስዱ 70 የአንደኛ ዓመት ሬዚደንት ሀኪሞች የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታ አቅርበዋል። 

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ከፍተኛ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቀናል ” ያሉት ቅሬታ አቅርቤዎቹ፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ‘ መፍትሄ እየፈለግን ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው በጀት የለውም ’ እንደተባሉ ገልጸዋል።

መጀመሪያ 100 ሬዚደንት ሀኪሞች እንደነበሩ ፤ በኋላ ግን ለቀው ለመሄድ በመገደዳቸው አሁን ላይ የቀሩት 70 ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ ጭምር ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ሬዚደንት ሀኪሞችም እንዳሉ ፤ የሚተዳደሩት ከደመወዝ በሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው። ደመወዙ በዚህ ሳምንት ሊገባልን ይገባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፣ “ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው። እኛን አይመለከትም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመጠየቅ ወደ #ጤና_ሚኒስቴር የተደረገው ሙከራ ኃላፊዎቹ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia