TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አዕምሮ የሌለው ሕዝብ #ሥርዓት የለውም፤ ሥርዓት የሌለው ሕዝብ የደለደለ ሃይል የለውም፤ የሃይል ምንጭ ሥርዓት እንጂ የሠራዊት ብዛት አይደለም፤ ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግሥት ይልቅ በሕግ የምትኖር #ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች።"

▪️ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
”ኢመደበኛ አደረጃጀቶች #ሥርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ ይሆናሉ"- ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
.
.
የአገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ በየአካባቢው ያሉ በግለሰብ የሚመሩ የወጣት ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ተቋማዊ እንዲሆኑ ስርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ እንደሚሆኑ ተጠቆመ። የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅንነት ሽማግሌዎችን እና የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን እያቀረበ ነው። አንዳንድ የምሁራን ማህበር እየተባሉ ኢመደበኛ በሆነ መልኩ የሚሳተፉ አሉ። በተለያዩ አካባቢዎች ሌሎችም መደበኛ ያልሆኑ የወጣት አደረጃጀቶች አሉ። ወደፊትም ሌሎች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

ነገር ግን ከማናቸውም አደረጃጀቶች ጀርባ የግለሰቦች ፍላጎቶች መኖራቸው መዘንጋት የለበትም። ያንን መዘወር የሚፈልጉ የፖለቲካ ሃይሎች ይኖራሉ። እነዚህ አደረጃጀቶች ከጠነከሩ ማዕከላዊ መንግስቱ ያዳክማሉ።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia