TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update ጥቅምት 30 ሊወጣ የነበረው የአዲስ አበባ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ #ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡ የዕጣው መውጫ ቀን ለመራዘሙ አንዱ ምክንያት በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ስር የነበረውን የዕጣ ማውጫ ከሶፍት ዌር ለሕጋዊነት፣ ፍትሃዊነት እና ታማኝነት ሲባል ወደ አስተዳደሩ ማዞር በማስፈለጉ ነው፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በረራው ተቋርጧል‼️

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ40 ዓመት በኃላ ወደ ሶማሊያ #ሞቃዲሾ ጀምሮት የነበረውን በረራ #ማቋረጡን ሸገር FM ዘገበ።

ተጨማሪ፦ ከትናንት በስትያ ዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነ ግለሰብ ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ በረራ ላይ #ተቀጣጣይ ነገር ይዞ ሊገባ ሲሞክር በኤርፖርት ጥበቃዎች #ተይዟል#ከአልሽባብ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ተብሎም ተገምቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ #ላልተወሰነ ጊዜ በረራውን አቋርጧል ሲል ሸገር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ባጃጅ ታግዷል "

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ የካቲት 30 ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ።

ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ አገልግሎት መታገዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ " የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ እገኛለው " ብሏል።

የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ #ላልተወሰነ_ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል። ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው። ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት…
#ተራዘመ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአዲስ እና የሬሜዲያል ተማሪዎችን መግቢያ ቀን #ላልተወሰነ ጊዜ አራዘመ።

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን ያራዘመው የመግቢያ ቀኑ ሊደርስ 3 ቀን ሲቀረው ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር (Freshman) ተማሪዎች እና ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከጥር 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።

ነገር ግን ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንና ወደፊት ጥሪ እስኪደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

ተቋሙ ለምን የመግቢያ ቀኑ እንደተራዘመ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል ፤ በዘንዘልማ ካምፓስ ሰሞኑን ማታ ማታ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ተኩስ ከፍተው መስተዋላቸውን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የዘንዘልማ ካምፓስ ተማሪ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ በግቢያቸው ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ገልጿል። በአካባቢው የቦንብ ፍዳታም እንደነበር ጠቁሟል።

ይኸው ተማሪ " በዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ አዲሳችን አልነበረም " ሲል ገልጾ ከትላንት በስቲያ በአጥር ዘለው የገቡ አካላት ጥይት እየተኮሱ እስከ ዋና መግቢያ በር መሄዳቸውን ጠቁሟል።

" የገባነው ‘ግቡ’ ተብሎ ነው፤ ብዙ ተማሪ የለም። ወደ 100 ብንሆን ነው " ሲልም አክሏል። ተኩስን ኖርማል ሲቪል ልብስ የለበሱ ሰዎች መክፈታቸውን ነው የተናገረው።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ/ም በተጨማሪ ማብራሪያ የሰጠ አንድ የግቢው ተማሪ ፤ በዘንዘልማ ያለው ሁኔታው ስለሚያሰጋ ወደ ዋናው ካምፓስ መሄዱንና የቀሩት ጓደኞቹ በሁኔታው መጨነቃቸውን እንደገለፁለት ተናግሯል።

" እስከ 18 ድረስ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ " የሚል ወረቀቶችም መበተኑን ከጓደኞቹ ዘንድ እንደሰማ በመግለፅ ያለንበትን ሁኔታ የሚመለከተው አካል ይወቅልን ብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ሁነኛ አካል ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ጉዳዩን #እንዳልሰሙና አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ቢገልጹም፣ በድጋሚ ሲደወልና የፅሑፍ መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia