TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam🇪🇹

የህዳሴው ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሃይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ ቤት አስታውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በአማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "አንድ እቅድ፤ አንድ ሪፖርት ለተቀናጀ የአባይ ተፋሰስ ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር እያካሄዱት ባለው ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናት ላይ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሃይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱ እና ግንባታው ከ81 በመቶ በላይ መከናወኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም #ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲውን የበላይነት እንድትጎናጸፍ ማስቻሉን ተገልጿል።

ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 65 ሚሊየን ለሚበልጥ የሀገራችን ህዝብ መብራት እንዲያገኝ ያደርጋል የተባለ ሲሆን ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን #ለመላ_አፍሪካዊያን በፖለቲካው የተጎናጸፉትን ድል በኢኮኖሚው መስክ ለመድገም የሚያስችል ነው ተብሏል።

የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በተፋሰሱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር በምርምር የተደገፈ የአፈር መከላትን በማስቀረት የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ በባህር ዳሩ መድረክ ላይ ገልጿል።

በባህር ዳት ትላንት የተጀመረው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ዛሬም ይቀጥላል።

@tikvahethiopia