TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሃዊ_ጉዲና

ይህ የምትመለከቱት ጅማ ከተማ የሚገኝ "ሀዊ ጉዲና" የተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤቱ የተሰራው በህብረተሰቡ ርብርብ ሲሆን ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው። የመማሪያ ክፍሎቹ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለመሆናቸው ሀገር ተረካቢዎቹ ትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሲያሳድር ቆይቷል። ነገር ግን አሁን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የጅማ ከተማ ተወላጆች በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን አስገንብተው የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ያስመርቃሉ።

🏷እነሱ በውጭ ሀገር ሆነው ይህን ለሃገራቸው ካደረጉ እኛ እዚሁ ኢትዮጵያ ያለን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ደግሞ በጅማ ከተማ የሚሰባሰበውን የመማሪያ መፅሃፍ ለዚህ ትምህርት ቤት በማስገባት ለቀጣይ ትውልድ መልካም ስራን ሰርተን እናሳያለን!

•በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ የጅማ ከተማ ተወላጆች ላደረጋችሁት ነገር በTIKVAH-ETH ስም #እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia