TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላለያ ሰራዊት🔝

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ #ልምምድ ማድረግ በመጀመሩ የፓርኩ ስነ-ምህዳር መናጋቱን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣ አስታወቀ።

ችግሩ የተፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ዓመታዊውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓርኩ ውስጥ ለማክበር በመወሰኑ ነው። የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ድርጊቱን ለማስቆም በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም #አለመሳካቱን ገልጿል።

በታንክ፤ በመድፍ፤ በጄት እንዲሁም በሄሊኮፕተር ተኩስና ትርዒት የታጀበ ልምምድ የሚካሄድበት አካባቢ የግሬቪ ዜብራ፤ የሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ የተለያዩ አዕዋፋት እና የሰጎኖች ዋና መኖሪያ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ሰራዊቱ በመጭው እሁድ ከፍተኛ ድምፅ የሚያስተጋቡ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም የተኩስ ትርዒት የሚያሳይ በመሆኑ በፓርኩ ስነምህዳር ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጠራል ያለው ባለስልጣኑ፣ መከላከያ ሚንስትር ለሚደርሰው ጉዳት #ሀላፊነት ይወስዳል ብሏል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ምሽቱን #በሞቃዲሾ ህዝብ በሚበዛበት ቦታ በተፈፀመ #የቦንብ_ጥቃት በትንሹ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ። ለጥቃቱ #አልሸባብ የተባለው የሽብር ቡድን #ሀላፊነት መውሰዱ ነው የተሰማው።

ፎቶ፦ Harun Maruf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ? በፎቶው የምትመለከቱት ቢንያም ኢሳያስ ይባላል። ተማሪ ቢኒያም ከልጅነቱ አንስቶ በትምህርቱ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ የልጅነት ህልሙ የሆነውን ህክምና ትምህርት ለመከታተል ወደ ጥቁር አንበሳ ሊገባ ችሏል። 4 ዓመት ድረስ ፈታኝ ነው የሚባለውን የህክምና ትምህርት (ሜዲስን) በከፍተኛ ውጤት ከተማረ በኃላ ግን ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በኃላ መማር አትችልም ሲል ገልጾለታል።…
#AAU

ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይም ይህን ብለዋል (ከኢፕድ የተወሰደ) ፦

- ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ 4ኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት 8 ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል።

- ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሀሳብ መሰረት ተማሪ ቢንያም ከጤና ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶችን እንዲማር ተወስኗል።
• በህክምና ፋርማሲ
• በህክምና ላብራቶሪ ሳይንስ
• በህክምና ላቦራቶሪ በመረጠው ዘርፍ እንዲማርና ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ እንዲሰጠው ተወስኗል።

- ተማሪው የአካል ጉዳት እያለበት ለህክምና ትምህርት ዘርፍ መመደቡና ለደረሰው ችግር ዋንኛ ምክንያት የህክምና ኮሌጁ ተማሪዎችን ራሱ መመልመል ያለመቻሉ ነው።

- የህክምና ኮሌጁ እና የትምህርት ክፍሉ አስቀድሞ ማድረግ የሚገባውን ነገር ማድረግ ባለመቻሉ በተማሪ ቢንያም ላይ ለተከሰተው ችግር #ሀላፊነት እንወስዳለን።

ዛሬ የተወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስና ቤተሰቦቹን በመጠየቅ ምላሻቸው ምን እንደሆነ እንልክላችኃለን።

ከዚህ ቀደም ተማሪ ቢንያም ያቋረጠውን የሜዲስን ትምህርት ቀጥሎ ሁለት እጅ የማይጠይቁ ስፔሻላይዜሽኖች ላይ መግባት እንደሚችል (ሳይካትሪ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ሌሎችም) ገልፆ ነበር።

ከልጅነቱ ጀምሮ " ሜዲስን " የመማር ህልሙን ለማሳካት የለፋው ተማሪ ቢንያም 5ኛ ዓመት ደርሶ በዩኒቨርሲቲው አሰራር ችግር ከሚወደው ትምህርቱ እንዲወጣ መደረጉ ተማሪውን ጨምሮ መላ ቤተሰቡን ያሳዘነ ድርጊት ነው።

(የተማሪ ቢንያም ጉዳይ - https://t.iss.one/tikvahethiopia/71823?single)

@tikvahethiopia