TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ይርጋለም #ሞረቾ #አገረሰላም~የፀጥታ ሁኔታ!

ትናንት ግጭት እና ተቃውሞ በታየባት ሐዋሳ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንደሚታይ የጀርመን ራድዮ ገለፀ። የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ እንደገለፀዉ ከሐዋሳ ውጪ በሞሮቾ፣ ይርጋለም እና አገረሰላም በተባሉት ከተሞች #አሁንም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንዳሉ የዓይን እማኞች ሰቅሶ ዘግቧል። በሞሮቾ የሚገኝ አንድ የዓይን እማኝ እንዳለው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በነበራቸው ግጭት «የሚያውቃቸው ወጣቶች #ሞተዋል። መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮች #ተዘግተዋል። ከሐዋሳ በዲላ በኩል ወደ ሞያሌ እና ኬንያ የሚወስደውም መንገድ ተዘግቷል።» አገረሠላም የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደገለፁት ደግሞ «ትናንትና ሰዎች ሞተዋል። ወጣቶች ቤት #አቃጥለዋል።» በከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ዛሬ ላይ መጠነኛ መረጋጋት ይታያል። «ሆኖም ከተማዋ ውስጥ ዛሬም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል።» የሲዳማ ዞን ፖሊስ በሐዋሳ አጎራባች አካባቢዎች አሁንም አለመረጋጋት መኖሩን ለ ጀርመን ራድዮ አረጋግጧል። በሲዳማ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩትን አለመረጋጋቶች ተከትሎ ደረሰ ስለተባለዉ ጉዳት ግን ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia