TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#REPOST

በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳትጭበረበሩ አዲስ ታትመው ስለተሰራጩት የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች መረጃ ይኖራችሁ ዘንድ ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱ።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት ምን ያስፈልገኛል ?

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት አመልካቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ይህን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሰነዶች ማዘጋጀት ፦

• ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ
• የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት/ማስረጃ

2. የሚያመለክቱት ለአስቸኳይ አገልግሎቶች ከሆነ ከሚከተሉት መካከል ቢያንስ አንዱ ሊኖርዎት ይገባል ፦

• የሕክምና ደብዳቤ
• የትምህርት እድል እና ዲቪ
• ከተፈቀደለት ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ
• የውጭ ሀገር የነዋሪነት ፍቃድ
• የግብዣ ደብዳቤ
• አስቸኳይ የስራ ጉዞ
• በሀዘን/ጋብቻ ምክንያት የሚደረግ ጉዞ

3. ለአዲስ ፓስፖርት የሚከፈለውን ክፍያ ያረጋግጡ ፦

• ለ32 ገጽ ፓስፖርት - 600
• ለ64 ገጽ ፓስፖርት - 2186 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍላችሁ online አድራሻ ላይ አባሪ ያደርጉታል።

ኦንላይ ላይ "ለአዲስ ፖስፖርት" አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎት ለማግኘት ይህን ሊንክ ተጠቁሙ👇
www.ethiopianpassportservices.gov.et

@TIKVAHETHIOPIA
#REPOST

በግጭቶች ፣ በሌሎች የብጥብጥ ሁኔታዎች / በአደጋዎች ወቅት ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ወይም ሊጠፉ ይችላሉ።

ይህ ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ላይ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይፈጥራል።

ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ወይም የጠፉ ዘመዶቻቸው ምን እንደገጠማቸው የማወቅ #መብት አላቸው።

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ እና የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሚጥሩ ቤተሰቦችን ይደግፋል ፤ ያግዛል።

የICRC አገልግሎትን ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የICRC ኢትዮጵያ ልዑክ 0943122207 / 011 552 71 10 ላይ በመደወል ማነጋገር ይቻላል።

(ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00 - 11:00 ሰዓት)

* የስልክ መስመሮቹ ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግማችሁ ሞክሩ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#REPOST

ኣብ ግጭታት እዋን ኣብ ካልኦት ናይ መጥቃዕቲ ኩነታት ወይ ከኣ ሓደጋታት ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ክጠፍኡ ወይ ክእሰሩ ይኽእሉ ፤ እዚ ድማ ኣብ ስድራቤቶም ጭንቀትን ዘይምርግጋዕን ይፍጠር።

ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ስድራቤቶም ናይ ምፍላጥ መሰል ኣለዎም።

ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ድማ ስድራቤቶም ዝጠፍእዎም ቤተሰብ አበይ ከምዘለዉ ንምፍላጥ ንምድጋፍ ይደሊ።

ኣገልግሎትና ዝደቢ ዝኾነ ሰብ ድማ ናብ ኢትዮጵያ ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ልኡኽ ፦
- 0943122207
- 0980192706
- 0980192709
- 011 552 71 10 ብምድዋል ምዝራብን ምርካብን ይኽእሉ ኢዮም።

(ካብ ሶኒ እስካብ አርቢ ካብ 2፡00 ሰዓት እስካብ 11፡00 ሰዓት)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ማን ናቸው? 

( በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ #Repost )

- ገና በሕጻንነታቸው የተደገሰላቸውን የጋብቻ ድግስ ጥለው አዲስ አበባ ገቡ።

- ለትምህርት ወደ ውጪ ሊላኩ ብለው በመጨረሻ ሰዓት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

- ወላጅ አልባ ሕጻናትን በማለታቸው የሞቀ ትዳራቸውን ጥለው በዶሮ ማርቢያ ቤት ውስጥ ተቀመጡ።

- ድርጅታቸው እራሱን ችሎ ገቢ ማግኘት ሲጀምር የለፋውበት ነው ብለው አንደም ሳንቲም ለግላቸው ተጠቅመው አያቁም፡፡ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ቢሆኑም ደሞዝ አይቀበሉም፡፡

- በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 1.5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ድጋፍ አግኝተው የሕይወት መስመራቸው ተስተካክሏል፤ 2700 በላይ ሕጻናት በእቅፋቸው አድገዋል።

- በዚህ ስራቸው የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ በርካታ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሽልማቶችን ወስደዋል።

Readmore https://telegra.ph/ይህንን-እንወቅ--ክብርት-ዶር-አበበች-ጎበና-ማን-ናቸው-06-04
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
#Repost

የደም እጥረት ተከስቷል።

አሁን ወቅቱ የፆም በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም የደም ባንኮች የሚሰበሰበው የደም መጠን በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሟል።

የብሔራዊ ደም ባንክ በላከልን መልዕክት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርቧል።

#ይህንን_መልዕክት_ያጋሩ !!

@tikvahethiopia
#Repost

ስለፊቼ ጨምባላላ ምን ያህል ያውቃሉ ?

- የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል።

- ፊቼ ጫምባላላ መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራል።

- በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል።

- ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል።

- 'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው'፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው።

- የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

- ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል።

- ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

- በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

- ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው።

- ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል።

- የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ይህ መረጃ የቀረበው ከ2019 የቢቢሲ ድረገፅ ላይ ከወጣው ፅሁፍ ነው።

@tikvahethiopia
#Repost

ግንቦት እና ኢትዮጵያ !

በቀረበኝ ኖሮ ለምን በላሁት
አያበቅለው የለ ሰኔና ግንቦት
የግንቦቱ ባሰ አረም በዝቶበት

ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ክስተቶችን ያስተናገደች ታሪካዊ ወር ናት።

ኢትዮጵያ በዚህ ግንቦት ወር ታዋቂ ልጆቿን ወልዳለች ፤ ወደማይቀረው ዓለምም ሸኝታለች ፤ መሪዎቿን ወደ ስልጣን አምጥታለች ፤ ከስልጣናቸው ሽራለች፤ አስከፊ ጦርነቶችን አስተናግዳለች፤ ከእነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች በተጨማሪ ግንቦት ያልተለመዱ ክስተቶች የተስተናገዱበት ወርም ነው።

አሁን አሁን ላይ እየቀረ መጥቶ ነው እንጂ በዚህ ወር ከተፈጠሩ መጥፎ አጋጣሚዎች ጋር በማያያዝ ወሩን በገደቢስነት በመፈረጅ በተለይ በመሃል ሃገር ጋብቻ አይፈፀምም ነበር።

በግንቦት ወር የተመዘገቡ አብየት ክስተቶች እጅግ በጥቂቱ ፦

➨ የታላቋ አክሱም ንጉስ አፄ ካሌብ ያረፉት በግንቦት ወር ነው። አፄ ካሌብ ከአክሱም እና አካባቢው አልፈው ቀይ ባህር ተሻግረው የደ/ አረቢያ ህዝቦችን ያስገበሩ ንጉስ ነበሩ።

➨ እቴጌ ምንትዋብ ያረፉት በግንቦት ወር ነው። እቴጌ ምንትዋብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሳ እንስቶች መካከል አንዷ ነበሩ።

➨ የውጫሌ ውል የተፈረመው በግንቦት ወር ነው።

➨ ለንግስና ያልበቁት ልጅ እያሱ ምኒልክ የተሾሙት በዚህ ወር ነው።

➨ ልዑል መኮንን ኃይለስላሴ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ህይወታቸው ያለፈው ግንቦት 1949 ነበር።

➨ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ህይወታቸው ያለፈው ግንቦት 29/1984 ነበር።

➨ ሀገራችን በታርክ በግንቦት ወር አስከፊ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።

➨ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የተወለዱት ግንቦት 19 ነው።

➨ በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኮ/ል መንግስቱ ኃለማርያም ላይ መፈንቅለ መንግስት የተሞከረው ግንቦት 8 ነበር።

➨ በኮ/ሌ መንግስቱ ኃ/ማርያም ላይ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት በአዲስ አበባ ግንቦት 8 ከሸፈ፥አስመራ ላይ ግንቦት 9/1981 ከሸፈ።

➨ በኮ/ሌ መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት አ/አ ላይ ሙከራውን ያደረጉት ጄነራሎች ራሳቸውን ገደሉ፣ ተገደሉ፣ ታሰሩ። አስመራ ላይ ግንቦት 9 የ102ኛ አየር ወለድ ክ/ጦር በምስራቅ እና በሰሜን የገጠማትን ጦርነት ሲመሩ የኖሩት ጄነራሎች ተገደሉ።

➨ ኮ/ሌ መንግስቱ ሀገር ጥለው የወጡት ግንቦት 13/1983 ነበር።

➨ 12 ከፍተኛ ጄነራሎች የተገደሉት ግንቦት 11/1982 ነበር።

➨ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ግንቦት 20/1983 ነው።

➨ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1 ነው።

➨ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ነው የተባለው ምርጫ የተካሄደው ግንቦት 7 ቀን 1997 ነው። በዚህ መነሻ በርካታ ወጣቶች በአደባባይ ተረሽነዋል ፥ ሺዎች ታስረዋል ፤ የተቃዋሚ አመራሮች ዘብጥያ ተጥለዋል።

➨ የደረግ ከፍተኛ አመራሮች ሞት የተፈረደባቸው ግንቦት 18 ቀን 1999 ነው።

➨ ሞት የተፈረደባቸው የደርግ አመራሮች ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረላቸው ግንቦት 2003 ነው።

ምንጭ ፦ ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ (አብዮቱና ትዝታዬ)፣ ታሪከ ነገስት-በደሴ ቀለብ ፣ፀሀፊ ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ኢፕድ ድረገፅ፣ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

" FIAS 777 " የተባለ ሰዎችን ትርፋማ አደርጋለው በሚል ከበርካቶች ኤጀንት በሚላቸው አካላት በኩል ገንዘብ ሲሰበስብ ከርሞ ዛሬ አድራሻውን ጥፍትፍት አድርጓል።

#ሌሎችም፦ መሰል ስራ የሚሰሩ አሉ፤ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ከዚህ በፊት ያሰራጨነውን በድጋሚ ለማቅረብ ወደድን ፦

#REPOST

" የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ ማትረፊያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።

እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ፤ የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው / የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ / ኢንቨስት ስታደርጉ እነዚህ ጥያቄዎች እንድትጠይቁ አደራ እንላለን ፦

1. ድርጅቱ / ተቋሙ እውቅና ያለው ፣ ፍቃድ ያለው ነው ? የሚሰራበትን ፍቃድ በይፋ አሳውቋል ?

2. በትክክል የሚታወቅ አድራሻቸው የት ነው ? ቢሯቸው ?

3. ለሚደርስብኝ ማንኛውም አይነት ነገር ማንን ተጠያቂ ማድረግ እችላለው ?

4. የሚሰራው ስራ ምን ያህል ቀጣይነት አለው ? ነገ እንደማይቆም ምን ማስተማመኛ አለ ? ይህንን ማንስተማመኛ ማን ይሰጠኛል ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊቶች እየሰፉ በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ብዙሃንን ሊጠቅም ያሚችል ማንኛውም ህጋዊ ስራ በሚስጥር፣ በድብቅ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም እና ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም እንቅስቃሴ ስትጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩ ጥያቄዎችን በቅድሚያ መልስ እንዳያገኙ አድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Repost

የካራማራ ድል !

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

ዘንድሮ ይህ ድል 45ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።

ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።

በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው  ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ45ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡

https://telegra.ph/Ethiopia-03-05

@tikvahethiopia
" ስቅለት "

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡

በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

11 ሰዓት

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።

#Repost
@tikvahethiopia