TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaRegion #Gojjam

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል።

የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272 እንደሆነ ተነግሯል።

የድርጅቱ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ምን አሉ ?

" በአጠቃላይ 4 ሺህ ሰራተኛ ነው ያስፈቀድነው። 272 ሰራተኛ ከጋርዱላና አሌ ዞን ወስደን መንገድ ላይ ችግር ገጥሞናል። ችግሩን በአካል እኔው እራሴ ሄጄ በሽማግሌም፣ በምንም እንዲፈታ እየሞከርን ነው " ብለዋል።

ቁጥርን በተመለከተ ፤ " ከጋርዱላ 246 እና ከአሌ 38 በድምሩ 282 ሰራተኞች ነው የሄዱት " የሚባለው እጅግ በጣም ስህተት ነው ብለዋል። " ዶክመንት አለን እያንዳንዱ ዶክመንት ስላለን በዛ ነው የምናወራው ፤ የሰው ልጅ ነው የወስድነው ማንም እየተነሳ ይሄ ነው ማለት አይችልም። ስንወስዳቸውም በህጋዊ መንገድ ተፈራርመን ነው። ቁጥራቸው 272 ነው " ብለዋል።

ይሄን ያህል ብዙ ኪ/ሜ ርቀት ሄዶ ለህዳሴ ግድብ ሰራተኛ መመልመሉን ምን አመጣው ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ጠንካራ ሰራተኞች ስለሆኑን ነው " ሲሉ መልሰዋል። ባለፈው ዓመት ድርጅቱ በተመሳሳይ ከየክልሉ ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከደቡብ፣ ከሁሉም ሰራተኛ ወስዶ እንደነበር አስታውሰው በተደረገው ግምገማ በስራቸው ውጤታማ ስለሆኑ ነው ደብዳቤ ተፅፎ ሰራተኞቹ የተወሰዱት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በአማራ ክልል ውስጥ ጦርነት እንዳለና መረጋጋት እንደሌለ እየታወቀ ለምን በዚህ መንገድ እንዲሄዱ ተደረገ ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እኛ የያዝነው የሀገር ፕሮጀክት ነው። ውል ገብተናል በውሉ መሰረት መስራት አለብን። መንገዱም ሌላ መንገድ የለውም አምናም (በ2015 ዓ/ም) ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ከኮንሶ ስንወስድ በዚሁ በራሱ መንገድ ነው። አሁንም ህዳር ላይ ነበር የምንገባው ባለው ሁኔታ ሳንገባ ቀረን ሲረጋጋ ተረጋግቷል ግቡ ተባልን ገባን " ሲሉ መልሰዋል።

' ከፋኖ ታጣቂዎች ለታጋቾች #ገንዘብ ተጠይቋል ፣ ድርጅቱ ገንዘብም ሰጥቷል '' እየተባለ ስለሚነገረው ጉዳይ በተመለከተ ፤ " እኛ ሙሉ መረጃ በሁለት ቀን እንሰጣለን ከዚህ በላይ ማለት ያለብኝ የለም " ብለዋል።

የሰራተኞቹ ደህንነትን በተመለከተ " ደህንነታቸው በጣም ሰላም ነው " ብለዋል። ይህን ያረጋገጡት እዛው ቅርብ ስለሆነ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን በአካል እዛው አካባቢ በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ እና #በሽምግልና ልጆችን ከእገታ ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ የተመዘገበ ከመላው ሀገሪቱ ሰራተኞችን ለስራ እየመለመለ የሚቀጥር እንደሆነ አሳውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ 'ፋኖ ታጣቂ ኃይሎች' የተያዙ ሰራተኞች ቤተሰቦች ሰራተኞቹ ፦
* አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ፣
* ጫካ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ፣
* ምግብም እያገኙ እንዳለሆነ፣
* ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱና ወደ ውጊያ ውስጥ እንዲገቡ የማስገደድ ሁኔታ እንዳለ፣
* የግድያ / ርሸና ዛቻም እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ታግተው ከተወሰዱ 4ኛው ሳምንት እየጀመረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የሰጣቸው አካል እንደሌለ ቤተሰቦች ገልጸዋል። የፌዴራልም የክልል መንግሥትም ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፤ " ... ከተቻለ በ72 ሰዓታት ውስጥ ወጣቶቹን ለቀይ መስቀል እናስረክባቸዋልን " ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ምን አሉ ?

➢ " እኛ ያረጋገጥነው እነዚህ ልጆች አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ ነው ያገኘናቸው " ብለዋል።

➢ የታገቱ ወጣቶች ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ ስለመሆኑን ምን ማስረጃ አላችሁ ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ አለን። በወታደራዊ ቋንቋ ጠርናፊ የሚባል ቃል አለ ይህ ማለት አንድን የሚንቀሳቀስ ወታደራዊ ኃይል፣ ምልምል / የታጠቀ ኃይል የሚመራ ማለት ነው። የነዚያ ተጓዦች ተርናፊዎች የአስር አለቃ ማዕረግ ሳይቀርብያላቸው አክቲቭ ወታደሮች መሆናቸውን ከራሰቸው መታወቂያ ዕዛቸውን፣ ኮራቸው፣ ክ/ጦራቸውም ፣ ሻለቃቸውን የሚጠቅስ መታወቂያ ይዘዋል። የመከላከያ አርማ ያለው መታወቂያና አክቲቭ መሆናቸውን አረጋግጠናል " ብለዋል።

➢ "ከያዝናቸው ውስጥ ያነጋገርናቸው ወደ መሰረታዊ ውትድርና እንደሚገቡ እንደሚያውቁ ፣ በዛ ያሉት ግን ግንዛቤው እንደሌላቸው ግን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ነው ያረጋገጥነው" ሲሉ አክለዋል።

➢ ሌላው ከተለያየ ኢትዮጵያ ክፍል ወደህዳሴ ግድብ የሚሄዱ ሰራተኞችም ሆነ ጎብኝዎች አዲስ አበባን ረግጠው ፣ በአምቦ አድርገው በነቀምት ፣ አሶሳ ነው ወደ ጉባ የሚገቡት በአማራ ክልል አቋርጠው የሚሄዱበት ታሪክ አልነበረም ሲሉ ተደምጠዋል። " አሁን ላይ በአማራ ክልል ውጊያ እንዳለ እየታወቀ በአ/አ አማራ ክልል አድርገው ወደ ጉባ የሚሄዱበት ምክንያት የለም " ሲሉ አክለዋል።

➢ የወጣቶቹን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ በተመለከተ እኚሁ ቃል አቀባይ ፤ " ስለ ፋኖ ዓላማ ፣ ስለ አማራ ትግል አስፈላጊውን ትምህርት ሰጥተናቸው ለቀይ መስቀል ልናስረክባቸው በዝግጅት ላይ ነን " ብለዋል። " ቀይ መስቀል ወደኛ እየመጣ ስለሆነ ከተቻለ በ72 ሰዓት ካልሆነም በ100 ሰዓት ውስጥ ለማስረከብ ዝግጁ ነን። ሁኔታውን አጥንተው ስለሚገቡ በደረሱበት ሰዓት እናስረክባለን። " ብለዋል።

➢ በታጋቾች ላይ እየተፈፀመነው ስለሚባለው የግድያ ዛቻ፣ በግዳጅ ወደ ውጊያ እንዲገቡ የማድረግ ጉዳይ ተጠይቀው ፤ " ከያዝናቸው 240 ሰዎች ፦
• አንድም ሰው የአካል ድብደባ ደርሶበት ከሆነ፣
• በግድ ፋኖ እንዲሆን ጠብመንጃ እንዲሸከም ተገዶ ከሆነ ፣
• አንድም ሰው ያለ ፍላጎቱ እኛ የፈለግነውን ፕሮፖጋንዳ እንዲናገር ተገዶ ከሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ ሂውማን ራይትስዎች አስፈላጊው አጣሪ ኮሚቴ ልከው ማጣራት ይችላሉ " ብለዋል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ ምን አሉ ?

° የፌዴራል መንግሥት ፤ የአማራ ክልልም መንግሥት ከዞኑ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ነገር ግን እስካሁን ውጤት እንዳልመጣ ተናግረዋል።

° ታጋቾች #በነፍስ_ወከፍ_300_ሺ_ብር እንዲከፍሉ መጠየቁን ነገር ግን ለማስቀለቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ያገኘው ከቪኦኤ ሬድዮ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia