TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GebreGuracha

በ " ገብረ ጉራቻ " ከተማ በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን በታጣቂዎች ሲገደል ፤ 11 አገልጋዮች ደግሞ በታጣቂዎች መታገታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ አሳወቀ።

የቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ፤ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ገርበ ጉራቻ ከተማ በምትገኘው በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም ሌሊት የማኅሌተ ጽጌ አገልግሎት ላይ በነበሩበት ወቅት #ታጣቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት አንድ ዲያቆን በመግደል ሌሎች 11 አገልጋዮችን ማገታቸውን ገልጿል።

በአካባቢው ላይ ተደጋጋሚ ችግሮች በመከሰቱ ምእመናን ስጋት ላይ በመሆናቸው ለመንግስት አካላት የማሳወቅ ሥራ ቢሠራም መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋዊ #የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሽፈራው ለተ.ሚ.ማ. በሰጡት ቃል የተፈጠረውን ጉዳይ እንደሰሙና ለዞኑ አስተዳደርና ለጸጥታ ዘርፉ ማሳወቃቸውን አስረድተዋል። በተለይ በቦታው ቅርብ ርቀት ላይ የመከላከያ ካምፕ መኖሩን ገልፀው ጉዳዩ ሲፈጠር የወሰዱት እርምጃ እንደሌለና ጉዳዩም አዲስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ይህ ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ስለሆነ ጉዳዩን ለቤተ ክህነት ማቅረባቸውን በአካባቢያው ለሚገኙ ቀሪ ምእመናን መፍትሔ እንዲሰጥ እንደጠየቁ እና ምላሽም እየተጠባበቁ ስለመሆኑ ለሚዲያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia