TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ140 በላይ ኢትዮጵያውያ ከእስር ተለቀቁ!

ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ጂፒ በተሰኘው የንግድ አካባቢ ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ታስረው ከነበሩ 150 ኢትዮጵያውያን ከ140 በላይ የሚሆኑት እስከ ትናንት ምሽት ድረስ መለቀቃቸው ተነገረ።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም ለቢቢሲ ሲናገሩ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፍቃድ እንዳላቸው ከተረጋገጠ በኋላ እንደተፈቱ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹ 450 የሚሆኑት እስረኞች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን ባላቸው መረጃ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል ኢትዮጵያዊያን እንዳልነበሩ አምባሳደሩ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ጨምረው እንደተናገሩት አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን በተመለከተ ኤምባሲው አስፈላጊውን ማጣራት እና ከሚመለከታቸው የሃገሪቱ ሃላፊዎች ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑን ያሰራቸው ተመሳሳይ ተደርገው የተሰሩ ሃሰተኛ ምርቶችን ይሸጣሉ በሚል ጥርጣሬ ነበር።

ተመሳሳይ ያልሆኑና በፖሊስ የተወሰዱ የኢትዮጵያዊያኑን እቃዎች ለማስመለስ ኢትዮጵያዊያኑ ጠበቃ ቀጥረው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱትና ኤምባሲውም ለዚህ ድጋፍ እንደሚያደርግ አምባሳደሩ አመልክተዋል።

Via #BBCአማርኛ
@tsegabwde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አከራካሪው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ!

ዶክተር ገረመው ሁሉቃ(ከትምህርት ሚኒስቴር)፦


"ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ስልጣንን በሚመለከት አሁንም መጣራት ያሉባቸው ነገሮች እንዳሉ እያየን ነው። ፍኖተ ካርታው ገና እየተሰራበት ያለ ሰነድ ነው። የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጣል ይላል፤ የ8ኛ ክፍል ፈተናም ብሄራዊ ፈተና ሆኖ ግን ተተርጉሞ ለክልሎች ይሰጣል ይላል እነዚህ ሁለቱ ጉዳዮች የክልል መንግስታትን ስልጣን ይነካሉ ህገመንግስቱ እንደሚለው ከ1ኛ ክፍል - 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መስጫ ቋንቋ የሚወስነው የክልሉ መንግስት ነው። ይህ መታየት ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ትምህርት ሚኒስቴር እየሰራበት ይገኛል።"

▫️ጉዶዮቹ የመጨረሻ ውሳኔ ያልተላለፈባቸው ከሆኑ ትላንት በትምህርት ሚኒስትሩ የተሰጠው መግለጫስ ተብለው ከቢቢሲ የተጠየቁት ዶክተር ገረመው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

"የትላንቱ መግለጫ በ2012 ዓ/ም ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ እንደሚሆን ለማስተዋወቅ እንጂ ስሱ ተብለው የተያዙና ውሳኔ ያልተሰጠባቸው ጉዳዮች አሉ። ፍኖተ ካርታው ገና እየተጠና ያለ ነገር ነው #የመጨረሻ አይደለም። በቀጣዩ ሳምንት በጅግጅጋ በሚደረገው የትምህርት ኮንፈረንስ ውይይት ይደረግበታል። ክልሎችም ስለሚሳተፉ እነዚህ ጉዳዮች #መፍትሄ ያገኛሉ።"

#BBCአማርኛ

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ፎቶ ናይጄሪያ -- አቡጃ ውስጥ ነው⬆️

ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች። ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት የተገደደችው በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በናይጄሪያ ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ነው። ባለፈው ሳምንት እሁድ የጀመረው በሌላ አፍሪካ ሃገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ ቀጥሎ የብዙዎች ንብረት ተዘርፏል፤ ወድሟልም።የናይጀሪያ መንግሥት ጥቃቱን ያወገዘው ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በበኩላቸው ድርጊቱ አሳፋሪ እንደሆነ ተናግረዋል።

Via #BBCአማርኛ
📸REUTERS
@tsegabwolde @tikvahethiopia