TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

ጉዞ ዓድዋ 6 ተጀመረ!! ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ የዘንድሮ ጉዞ መነሻ ተደርጋ ተመርጣለች።

"ፍቅር ለኢትዮጵያ" የሚል መርሕ የያዘው የዘንድሮ የእግር ጉዞ መነሻውን ከሀረር ከተማ በማድረግ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን በመቀላቀል የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ይጠናቀቃል።

በትናትናው ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የመሸኛ ስነሥርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ባደረጉት ንግግር "ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ህብረት ያታየበት ሁላችንም የምንኮራበት ድላችን መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚዘጋጀውን የጉዞ ዓድዋ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚያግዝ አረጋግጠው የዘንድሮው 123ኛ የዓድዋ ድል በዓል አከባበር መጀመሩን በይፋ አብስረው፤ ለተጓዦች መልካም መንገድ ተመኝተዋል።

በታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የምስራቅ ኢትዮጵያን ጦር የመሩት የቀዳሚው ጦር አዝማች ልዑል ራስ መኮንን ከተነሱበት የሐረር ከተማ በ5 ተጓዦች የተጀመረው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በተለያዩ ደማቅ ሥነስርዓቶች ለመካሔድ በዛሬው እለት ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች በስልክ እንዳረጋገጡት የከተማ አስተዳደሩ ከሀረር የተነሱ ተጓዦችን ተቀብሎ በመሸኘት እና ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን አሰፈላጊውን ስንቅ አሟልቶ በመሸኘት የከተማ አስተዳደሩ አጋርነቱን ያሳያል።

፨፨፨
የፍቅር ዘመቻው ሠላምን እና አብሮነትን ሰንቆ በዓድዋ ተራሮች አናት ላይ የካቲት 23 ቀን በድል ይጠናቀቃል።
የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች
መሐመድ ካሳ
ያሬድ ሹመቴ
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም !!
#ጉዞ_ዓድዋ_6
#ከሐረር_አዲስ_አበባ_ዓድዋ
#1540ኪ .ሜ

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia