TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update-ታማኝ በየነ በአራት ቀናት ውስጥ ከሶስት ከተማዎችና ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ይገናኛል፡፡

📌ሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓም #ድሬ

📌ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓም #ሐዋሳ

📌እሁድ መስከረም 6 ቀን 2011 ዓም #ደሴ ከተማ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

©Dani
@tsegabwolde
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa " በሲሚንቶ ላይ በሚታየው ከከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ቤት መገንባት እስከማቆም ደርሷል ፥ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ ነው " - አቶ ከድር ጁሃር በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በየጊዜው በተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች ፣ የምግብ ፍጆታዎች እንዲሁም በኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ላይ ሲሚንቶን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ይታወቃል። ድሬድዋ…
#ድሬ

ትላንት ድሬዳዋ ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ሲሚንቶ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተነግሯል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከናሽናል ሲሚንት አክሲዮን ማህበር እህት ኩባንያ ከሆነው ኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በድሬዳዋ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት ፍትሀዊ ለማድረግ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ፋብሪካው ለኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ490 ከ36 ሳንቲም እያስረከበ ኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ደግሞ አስተዳደሩ ላደራጃቸው 200 ለሚጠጉ ቸርቻሪዎች አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ520 ብር ከ36 ሳንቲም እያስረከበ ይገኛል።

በዚህም በድሬዳዋ ከተማ ትስስር ከተፈጠረላቸው ቸርቻሪዎች ውስጥ ከኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ520 ብር ከ36 ሳንቲም ተረክበው 60 ብር ጭማሪ ተደርጎበት ለህብረተሰቡ በ580 ብር ከ36 ሳንቲም እንዲቀርብ ተብሎ ከፋብሪካው ሲሚንቶ የጫኑ መኪኖች ቢወጡም ሲሚንቶውን ለነዋሪው ህብረተሰብ ባለማድረሳቸው ምክንያት በተደረገው ክትትል 600 ኩንታል የሚሆን ሲሚንቶ የጫኑ 5 መኪናዎች ትላንት ምሽት በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መረጃውን የከተማውን ንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢኒቨስትመንት ቢሮ ዋቢ አድርጎ ያሰራጨው የከተማው ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ድሬ

በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ።

" ለጊዜው  ምክንያቱ ባልታወቀ  ሁኔታ  በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል " ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ " የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ " ላይ ነው፡፡

ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የፋብሪካው ንብረት የሆኑ ፦

👉 አንድ ትልቅ የምርት ማከማቻ መጋዘን፤
👉 አንድ  ቦንድድ ማሽን፤
👉 በርካታ የተጠናቀቁ የስፖንጅ ፍራሽ ምርቶች እንዲሁም ሁለት ሆዝ የእሳት ማጥፊያ በአጠቃላይ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር ንብረት ወድሟል።

አደጋው እንደደረሰ የድሬዳዋ ፖሊስ የእሳት እና ድንገተኛ ዲቪዥን እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከላካይ ቡድን በቦታው ላይ በመድረስ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። አደጋውን ለመከላከል አርባ ስምንት ሺ ሊትር ውሃ እና አንድ መቶ ሊትር ፎም መጠቀማቸው ተገልጿል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከንብረት ጉዳት ውጪ በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ ያልደረሰ መሆኑን የገለፀው የድሬዳዋ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ምንጭ፡ #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ድሬ

የድሬዳዋ ፖሊስ ፤ በአሽከርካሪነት ተመድቦ ከሚሰራበት ድርጅት እንዲያሽከረክር የተሠጠውን መኪና ሰርቆ በ290 ሺህ ብር የሸጠው ተጠርጣሪ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ CCECC በተሰኘ የመንገድ ስራ ድርጅት ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ነበር።

የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሠዓት ላይ የድርጅቱን የስራ ኃላፊዎች ወደቤታቸው ካስገባቸው በኋላ ያለማንም ፍቃድ ተሸከርካሪውን ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ በመውሰድ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመተውን ተሸከርካሪ ለአንድ ግለሰብ በ290 (ሁለት መቶ ዘጠና ሺ) ብር ሽጧጣ።

የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሁለት ቀን በኋላ ከድርጅቱ መኪና እንደጠፋ ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ከተጠርጣሪው አድራሻ በመነሳት ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪውን በሌላ ሰው እጅ በአዳማ ከተማ ሲሽከረከር በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉ አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት ተሽከርካሪውን ሰርቆ የሸጠውን አሽከርካሪ እና የገዛውን ግለሰብ ጨምሮ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን ድሬ ፖሊስ ገልጿል።

የድሬ ፖሊስ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለንብረታቸው ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው መልእክት አስተለልፏል።

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዛሬ በድሬዳዋ በደረሰው ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ከንቲባ አቶ ከድር ፥ ከጥዋት 1 ሰዓት ጀምሮ በተለምዶ ' አሸዋ ' በሚባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ፦ ሩዝ ተራ ማሽላ ተራ ሰልባጅ ተራ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ አሳውቀዋል። ሌሎች በከፊል የተረፉ እንዳሉ ጠቁመዋል።…
#ድሬ

ከቀናት በፊት ድሬዳዋ ' አሸዋ ገበያ ' ስፍራ እጅግ በጣም የከፋ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር ይታወቃል።

በአደጋው በርካታ ነጋዴዎች አንድም ሳይቀር ነገር ሳይቀር ንብረታቸው ወድሟል።

አሁን ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጎጂዎች እንዲረዱ ለማድረግ " ድሬዳዋ ትጣራለች !! " በሚል ዘመቻ ጀምሯል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረጊያ የሒሳብ ቁጥርም ይፋ ተደርጎ ድጋፍ እየተሰባደበ ነው። የሒሳብ ቁጥሮቹ  ፦
• ንግድ ባንክ ፦ 1000637750201
• ዳሽን ባንክ ፦ 5009786342011
• አዋሽ ባንክ ፦ 013211367855100
• የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፦ 1001300318808 ሲሆኑ ' BESAT ADEGA LETEGODU WOG DIGAF MAS ' ይላል።

በሌላ በኩል ፤ የስልጤ ልማት ማኅበር እና የስልጤ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ለተጎጂዎች እያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር (በድምሩ 2 ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ማድረጋቸው ተነግሯል።

#DireDawa

@tikvahethiopia
#DireDawa : ዶክተር ጌታቸው ጫካቤኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዶ/ር ጌታቸው ጫካቤኛ በድሬዳዋ የመጀመሪያው የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ነበሩ።

ከአርባ ዓመታት በላይ በድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስትነት ፣ በህክምና ዘርፍ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ወገናቸውን አገልግለዋል።

በስራ ልምዳቸውም በርካቶችን አብቅተዋል።

ድሬዳዋ " ባለውለታዬን አጣኋቸው " ብላለች።

ከንቲባ ከድር ጁሀር  " ለረጅም ዓመታት በከተማው የህፃናት አለኝታ በመሆን ጡረታ እስኪወጡ የድሬዳዋን ህዝብ በፍቅር ነው ያገለገሉት " ሲሉ በህልፈታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

በዶ/ር ጌታቸው የህክምና ጥበብ ከህመማቸው የተፈወሱ በርካታ ህፃናት እና ወላጆች እንደሆኑ ገልጸው ሀዘኑ የመላው ከተማ እንደሆነ በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።

#DireDawa #ድሬ

@tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

" አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር። ነግሬያችኃለሁ
!! " - ኮሚሽነር ዓለሙ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዓለሙ መግራ ድሬ ውስጥ ሰዎች ቤት ሲቀይሩ " ጫኝ አውራጅ ነን እያሉ የሚከተሉ ጎረምሶች እንዳይኖሩ " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ይህን እጅግ ጠንካራ ትዕዛዝ የሰጡት ከከተማውን የፀጥታ አመራሮች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

በህዝብ ላይ እንግልትና ዘረፋ በሚፈፅሙ ጫኝና አውራጆች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

ኮሚሽነር ምን አሉ ?

" ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

በየቀጠናችን ያለው የጫኝ አውራጅ ስቃይ ህዝቡን ብታዩ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም።

ይሄን ያደራጀ ሰው ካለ ኃላፊነቱን አናውቀውም።

አንድም ጫኝ እና አውራጅ በየትኛውም ቀጠና የውሃ ፋብሪካ ምናም ካልሆነ በስተቀር ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

ይሄ ከተገኘ እወቁ ! አንድም ቦታ ሰውዬው ሲፈልግ ተሸክሞ ያውርድ ሲፈልግ ይስበረው።

በቀደም አንዱ መጥቶ ነገረኝ ትንሽ እቃ ነው በዳማስ ሄዶ ቀስ ቀስ እያለ አወረደ ... ከዛ ሮጠው መጡና አንኳኩ ' ክፈቱ ' አሉ ግር ብለው ገቡ ፤ እቃው ወርዷል ከዛ ' ስጡን (ብር) ' አሉ ለምን ? ' የደንቡን ' የምን ደንብ ? እኛ አውርደናል እቃችንን አላቸው ' ሊሰጠን ይገባል አታውቅም እንዴ ይሄ የሰፈሩ ደንብ ነው ' አሉ።  ሰውዬው ወደ ፖሊስ ሲደውል ከግቢ ወጥተው በር ላይ ቁጭ አሉ። ትንሽ ሲቆይ አንድም ሁለትም እየሆኑ ሄዱ።

እኚህ ወጣቶች ሌላ ቀን ወንጀል ከመስራት ወደኃላ አይሉም። ለዚህ ነው ሰግቶ የነገረኝ።

ሰው በፍርሃት ነው ያለው።

አይቻልም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል !! ነግሬያችኃለሁ።

ቤት ሲቀየር ገና ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ነው ሰው የሚደራጀው ስራ ?

አይቻልም !

ብሎኬት ማውረድ ከፈለገ ሰውየው ቤት ሲሰራ እዛው ጋር የሚሰሩትን ሰዎች ማስወረድ ይችላል ፤ ሌላ ሰው ጠርቶ ዋጋ ተደራድሮ እሱ ባለው ዋጋ ማስወረድ ይችላል አለቀ።

' እኔ ማህበር ነኝ ፤ እኔ እንደዚህ ነኝ ' ማን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ።

አንድም እንዳይኖር ይሄን ሰፈራችሁ ላይ አወያዩ ፤ ማህበረሰቡ ይሄን ይወቅ ለናተ መረጃ ይስጣችሁ። ሰፈር መድረስ ማለት ይሄ ነው።

ጫኝ እና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።

ይሄ የጫኝ እና አውራጅ ስቃይ የድሬዳዋ ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ በየሰፈሩና በክልል ከተሞች ተመሳሳይ ነው።

ገና ሰው እቃ ይዞ ሲመጣ " እኛ ካላወረድን ማንም ማውረድ አይችልም " በሚል አምባጓሮ የሚፈጡ አሉ።

አውርዱ ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው የሚጠሩት ብር ደግሞ አስደንጋጭ ነው።  ሰው በስንት ድካም ገንዘቡን እንደሚያገኝም አይረዱም።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ በስንት መከራና ጭቅጭቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ እቃውን ያስወርዳል። " ነገ የት እኖራለሁ " ብሎ በመፍራት።

እራሱና ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ በጋራ የገዛ እቃቸውን እንዳያወርዱ ዛቻ ሁሉ ሊፈጸምባቸው ይችላል።

ይህንን ስርዓት አልበኝነትና ድንፋታ እንዲያስቆሙ የሚጠሩ አንዳንድ የፀጥታ አባላት ነገሩን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የሚሉት ' ከነሱ ጋር ተስማሙ ' ነው።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃውን ይዞ ይገባል። በገዛ ሀገሩ በገዛ ከተማው በገዛ እቃው ተሳቆ ነው የሚኖረው። ስቃዩ ብዙ ነው !

#TikvahEthiopiaFamily

#DirePolice #ድሬ

@tikvahethiopia