TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ICS #Ethiopia

" በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል " - ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት በትግራይ ተቋርጦ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን አገልግሎት ለማስጀምር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት 6 ወራት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌቶችን ከውጭ ሀገር በማስገባት 640 ሺህ ፓስፓርት ፐርሰናላይዜሽን ህትመት በመስራት ለተጠቃሚዎች ማድረሱን አሳውቋል።

• ለአዲስ አበባ 260,371፣
• በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣
• በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 እንደሆነ አመላክቷል።

የውስጥ ህትመት አቅምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቀን 2 ሺህ ይታተም የነበረው አሁን ወደ 10 ሺህ በላይ ወደማተም ደረጃ መደረሱን ገልጿል።

መ/ቤቱ በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ በይፋ አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ በእጁ ላይ 80 ሺህ ፓስፖርት ስላለ ያመለከቱና ተራው የደረሳቸው በስልክ በሚደርሳቸው መልዕክት መሰረት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ፓስፖርት ለማውጣት ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረው የአንድ አመት ጊዜ ከመጋቢት 16 /2016 በኃላ እንደሚቀረፍ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ገልጿል።

ከዚህ በባለፈ ፤ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ፦
➡️ከዋና ቢሮ፣
➡️ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
➡️ ከቦሌ፣
➡️ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ #ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው ለህግ አካላት እንዲቀርቡ እንደየጥፋታቸውም ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድቷል።

ህብረተሰቡ ፦

* ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ
* በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣
* ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣
* ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣
* አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM በጅቡቲ የባህር ዳርቻ የ38 ሰዎች አስክሬን ተገኘ። በጀልባ መስጠም አደጋ የህፃናትን ጨምሮ አጠቃላይ 38 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው መገኘቱን የዓለም አቀፉ የስድተኞች ድርጅት አሳውቋል። 6 ሰዎች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነግሯል። ከሞት የተረፉ 22 ሰዎች በጅቡቲ እርዳታ እየተደረገለቸው ይገኛል። @tikvahethiopia
" 38 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸውን እንዳጡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

ትላንትና ሰኞ በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ " #ጎዶሪያ " በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስልሳ (60) ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኤምባሲው ፥ በየዓመቱ ከ200 ሺህ የሚበልጡ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ባህር ዳርቻ የኤደን ባህረ ሰላጤ በመነሳት መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመድረስ በየብስና በባህር አደገኛ ጉዞ ያደርጋሉ ብሏል።

ባለፉት አምስት ዓመታት #በጀልባ_መስመጥ አደጋ ብቻ የ189 ዜጎቻችን ሕይወት እንዳለፈ ጠቁሟል።

በየጊዜው የሚደርሰው አደጋ እንዳለ ቢሆንም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግን አሁንም #እየጨመረ እንደሆነ ገልጿል።

ዜጎች በህገ ወጥ #ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

የፍትህ አካላት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን #ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopia