TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦባንግ ሜቶ⬆️

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ፕሬዝዳንት ኦባንግ ሜቶ ከቡራዩ ከታና ከሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በዊንጌት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተጠለሉ #ዜጎችን ጎበኙ። እንዲህ አይነቱ አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ መገለጫ ባለመሆኑ ልንታገለው ይገባል ብለዋል አቶ ኦባንግ። ጥቃት አድራሾቹ ተለይተው መታወቅና ድርጊቱ እንዳይደገም ህጋዊ #እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ሲሉም #አሳስበዋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መጋቢት 29 በሚጀመረው የህዝብና ቤት ቆጠራ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችና #የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ #ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል ከለውጡ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሁለት ወራት በፊት ስብሰባ ተደርጎ መገምገሙን በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ሁሉም ክልል የየራሱን ሪፖርት ካቀረበ በኋላ፣ የቆጠራ ኮሚሽኑ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ በሰፊው ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ በዚህም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህዝብና ቤት ቆጠራውን ለማካሄድ እንደ አማራጭ ክልሎች በአስቸካይ ተነጋግረው ችግሮችን በፈቱባቸው አካባቢዎች የቆጠራ ካርታ መሰራቱንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳፊ እንደሚሉት ክልሎች ችግሩን መፍታት ባልቻሉባቸውና የቆጠራ ካርታ ባልተሰራባቸው አካባቢዎች ‘’ልዩ የቆጠራ ቦታ’’ ‘’Special Enumeration area’’ ተብሎ ተይዞ ቆጠራው ይካሄዳል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia