TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ⬆️የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ተከፍቷል። ፕሬዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ እና ለኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ #ኢሳያስ_አፈወርቂ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መከላከያ ሃይላችን እንደዜጋ መደመጥ ይኖርበታል!" ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን

* * *
"ለውጡ እንዳይደናቀፍ ሃገራዊ ግዳጃችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን!" የመከላከያ ሰራዊት አባላት
~~~~~~~~~~~©
ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ~ጦር የተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር #ተወያይተዋል

አባላቱ ከተጣለባቸው ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዳጅ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በውይይቱ የመከላከያ አባላት እንደዜጋ ጥያቄያቸው ሊደመጥ እና በተግባር መመለስ እንዳለበት አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።

መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች የሚመቻቹ መሆኑን አቶ ደመቀ አስረድተው፤ በቀጣይም መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ አረጋግጠዋል።

የመከላከያ አባለቱም በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንዲፈታ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ #ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
~~~~~
በመቀጠል አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዓብይ_አህመድ ጋር ውይይት አድርገዋል።
~~~~~
30/01/11

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያልተለመደ ተግባር በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ዓብይ_አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ለማሾም ወደ ፓርላማ ሲመጡ ከጽሕፈት ቤታቸው #በእግራቸው ተራምደው ነበር የገቡት፡፡ ከአራት ኪሎ ወደ አዋሬ የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን #ባልተለመደ ሁኔታ በእግራቸው ከጽሕፈት ቤታቸው አንስቶ እስከ ፓርላማው ቅጥር ግቢ እየተጓዙ ሲመጡ በዚህ ከሪፖርተር የተገኘው ፎቶ ያሳያል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶ/ር አብይ ድንገተኛ ጉብኝት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ የጠቅላይ አቃቤ ህግና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቶችን ባዛሬው ዕለት በድንገት ጎብኝተዋል።

የጉብኝቱ ዓላማም የሁለቱ መስሪያ ቤቶች የመስሪያ ቦታን በማስተካከል ውጤታማነትንና አፈፃፀምን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድንገት የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን የሚጎበኙበት ምክንያትም መስሪያ ቤቶቹ በእቅዳችው መሰረት ስራቸውን በአስፈላጊው ፍጥነት እያከናወኑ መሆኑን ለማየት መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ሃገር ለረጅም ጊዜ በግጭት ውስጥ ቆይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ጊዜው ዕይታችንን በማስተካከል የኢኮኖሚ ልማታችንን በትኩረት የምንሰራበት ወቅት ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይም የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን በድንገት በመጎብኘት የስራ አፈፃፀማቸውን የሚገመግሙ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ epa
ፎቶ - በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተቃዋሚዎችም በሩ ክፍት ነው...‼️

የኢሕአዴግ መሥራች የሆኑትን አራት ድርጅቶችና አጋሮችን በማካተት በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚመሠረት በተገለጸው አንድ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ፣ #መካተት ለሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሩ ክፍት መሆኑን ግንባሩ አስታወቀ።

ከጥቂት ቀናት በፊት ከኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮችና አጋር ፓርቲዎቹ ከሚመሯቸው ክልሎች ከተወጣጡ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ የተወያዩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር #ዓብይ_አህመድ (ዶ/ር)፣ ኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶችን አካቶ በመዋሀድ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚመሠረት መግለጻቸው ይታወሳል።

በኢሕአዴግ ውሳኔ ብቻ የሚመረጥ #የአገር_መሪ የመሰየም አካሄድ እንደሚያበቃና የአጋር ድርጅቶች ሲያነሱ የቆዩት የፓለቲካ ውክልና ጥያቄም በዚህ እንደሚመለስ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ከጥቂት ወራት በኋላ የአፋር፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ የሶማሌ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ ... ፓርቲ እያልን አንሄድም። እንደ ኢሕአዴግ ከጫፍ ጫፍ ያሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በነፃነት የሚሳተፉበት አንድ አገራዊ ፓርቲ እንመሠርታለን፤›› ብለዋል።

ይኼንን ጉዳይ በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ #ሳዳት_ነሻ የኢሕአዴግንና የአጋሮቹን ውህደት በተመለከተ የተከናወነው ጥናት መጠናቀቁን ገልጸው፣ በጥናቱ የተለዩት ግኝቶችን መሠረት በማድረግ ሁሉም የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች በቅርቡ ከሚመሩት ማኅበረሰብ ጋር በተናጠል ውይይት ማድረግ እንደሚጀምሩ አስረድተዋል። በውይይት ከዳበረ በኋላም መሟላት የሚገባውን ሥነ ሥርዓት ተከትሎ በዓመቱ መገባደጃ ላይ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስችለው ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ እንደሚገመት ገልጸዋል።

በኢሕአዴግና በአጋሮቹ ውህደት በሚወለደው አዲስ አገር አቀፍ ፓርቲ ውስጥ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ መካተት እንደሚችሉ፣ ለዚህም ኢሕአዴግ በሩን ክፍት እንደሚያደርግ አቶ ሳዳት ገልጸዋል።

በሚመሠረተው አገር አቀፍ ፓርቲ ውስጥ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ ማሟላት የሚጠበቅባቸው፣ የኢሕአዴግን መሠረታዊ ባህሪያት መቀበል እንደሆነ አስረድተዋል።

#ኢሕአዴግና አጋሮቹ የሚያደርጉት ውህደትም ነባር የኢሕአዴግ መሠረታዊ ባህርያትን ሳይለቅና እነዚህን መሠረታዊ ባህሪያትም ለሚመሠረተው አገር አቀፍ ፓርቲ በማውረስ የሚፈጸም መሆኑን  ገለጸዋል፡፡ የብሔርና የቋንቋ ማንነቶች፣ እንዲሁም የፌዴራሊዝም ሥርዓት መርሆች ተጠብቀው፣ ከሚቀጥሉት የኢሕአዴግ መሠረታዊ ባህርያት መካከል ዋናዎቹ መሆናቸውን ለአብነት ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia