TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል። አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል። የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ…
#NATO

NATO በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ሁሉንም መረጃዎች የቅርብ አጋሮቼ ናቸው ላላቸው ስዊድን እና ፊንላንድ እያካፈለ መሆኑን ዋና ጸሃፊው ጄንስ ስቶልተንበርግ ዛሬ አስታውቀዋል።

ስቶልተንበርግ ዛሬ በብራስልስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ለሩሲያ ወረራ ምላሽ ለመስጠት ከፊንላንድ እና ስዊድን ጋር ያለንን ትብብር እና የመረጃ ልውውጥ ለማጠናከር ወስነናል " ብለዋል።

አክለውም ፥ " ሁለቱም ሀገሮች አሁን ላይ ስለ ቀውሱ በሁሉም የNATO ምክክር እየተሳተፉ ነው። ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከቀናት በፊት ሩሲያ ፥ ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል #ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አጥብቃ ማስጠንቀቋ የሚዝነጋ አይደለም።

ሩስያ ሁለቱን ሀገራት አርፋችሁ ቁጭ በሉ ስትል ማስጠንቀቋ በዩክሬን ተባብሶ የቀጠለው ጦርነት ላይ ሌላ ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ስጋት እና አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል ሲነገር እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ምንም እንኳን ሁለቱ ሀገራት የNATO አባል ባይሆኑም NATO ከሁለቱም ሀገራት ጋር ያለውን ገኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ወስኗል።

@tikvahethiopia