TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ የአማራ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ሹመቱ የተሰጣቸው በጸጥታው ዘርፍ ያላቸውን የረዥም ጊዜ ልምድና ብቃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ከምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል አ.ብ.መ.ድ.

አ.ብ.መ.ድ(የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት)
@Tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ‼️

የቅማንት ሕዝብ ወኪሎች ነን የሚሉ ጽንፈኛ ሃይሎች ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ መሆናቸውን የአማራ ክልል ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል #አሳምነው_ጽጌ ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው ከቢቢሲ- አማርኛ እንደተናገሩት ቡድኖቹ በትክክል ከእነማን ጋር እንደሚሰሩ በስም ባይጠቅሱም የክልሉን ሰላም ለመበጥበጥ ከጎረቤት ሀገር ወይም ከሀገር ውስጥ ከአጎራባች ክልል ጋር ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በምዕራብ ጎንደር እና መተማ አካባቢ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት በትግራይ እና በቅማንት ተወላጆች ላይ ጥቃት የተጸመ ሲሆን በገበሬ እጅ ሊገኙ የማይችሉ ጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡ ወደፊት የሚጣራ ቢሆንም ላሁኑ በጥቃቱ የሞቱት የአማራ ብሄር ተወላጆች ይልቃሉ ብለዋል፡፡

ትግራይ ክልል ትናንት ባወጣው መግለጫ በግጭቱ አንዳንድ የክልሉ ባለስልጣናት እጃቸው አለበት ሲል መግለጹን “ሃሰት” በማለት አጣጥለውታል፡፡

©WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ‼️

‹‹በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነው፡፡›› የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ
.
.
ከትላንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ 34 ቤቶች ወድመዋል፤ 6 የእህል ወፍጮዎች ተቃጥለዋል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሰማነው ጽጌ፤ ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ለአማራ ቴሌቪዥን በስልክ እንደገለጹት ለግጭቱ ምክንያቶች የሆኑት በአካባቢው የሌሎች እጅ እንዳለበትና የቅማንት አስተዳደር ራሱን ለማስተዳደር በህገመንግስቱ የተሰጠውን መብት ላለመጠቅም መፈለጉ ናቸው፡፡

በዚህም የመንገድ መዘጋት እና የሰው መታገት እያጋጠመ ነው፡፡ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ስለሆነም የተዘጉ መንገዶችን መክፈት እና የማህበረሰቡን ሰላም መመለስ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች ዘላቂ የሰላም መፍትሄ እንዲያገኙ የክልሉ መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተደጋጋሚ ግጭቶች በማጋጠሙ፣ ተሸከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲደረግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡

ትላንት ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተገኘው መረጃ መሰረት ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት ተለይተዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikahethiopia
ጠገዴ ወረዳ‼️

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የተማሪዎችን ሕይወት የቀጠፈው ቦንብ ተቀብሮ የቆየ አለመሆኑ ታውቋል።

የአማራ ክልል የሰላም ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ እንደተናሩት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ቡሬ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ ፈንድቶ 2 ተማሪዎችን የገደለውና ሌሎች ስድስት ተማሪዎችን ያቆሰለው ቦንብ እንዲሁ ተቀብሮ የቆዬ አይደለም፡፡

እንደ ጀኔራል አሳምነው ቦንቡ ሆን ተብሎ ለጥፋት የተዘጋጄና ሆን ተብሎ የገባ ነበር፤ የት አካባቢ ጥፋት ለማድረስ ታቅዶ እንደነበር ግን እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ከዚህ ቀደም ‹‹በመሬት ውስጥ ተቀብሮ ከቆየ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ ኤፍ 1 ቦንብ ፈንድቶ ነው ጉዳት የደረሰው›› ማለቱ ሲዘገብ ነበር፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ‼️

•‹‹አካባቢውን ለማወክ የሚፈልጉ ኃይሎች ሦስት ቀበሌዎችን ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ በማድረግ ላለፉት አራት ዓመታት የወታደራዊ ማሰልጠኛ አድርገዋቸዋል፡፡››

•‹‹በክልሉ ምዕራብና ምሥራቅ አካባቢ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡›› የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ
.
.
.
በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢ የሚስተዋሉት የፀጥታ ችግሮች ተመሳሳይነት ያላቸው መሆኑን የክልሉ የሰላም ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ ተናገሩ፡፡

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ በተለይ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አካባቢ የሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ለዓመታት በወታደራዊ የማሰልጠኛ ማዕከልነት እያገለገሉ ለአካባቢው አለመረጋጋት ምክንያት ሆነዋል፡፡ ጉባይ ጀጀቢት፣ ሌጫና መቃ የሚባሉ ሦስት ቀበሌዎችን አካባቢውን ለማወክ የሚፈልጉ ኃይሎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ በማድረግ ላለፉት አራት ዓመታት የወታራዊ ማሰልጠኛ አድርገው መቆየታቸውንም ነው ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ያስታወቁት፡፡

የክልሉ መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብ አባላት በሚኖሩበት 69 ቀበሌዎች የራሳቸውን አስተዳደር እንዲመሠርቱ ሕጋዊ ዕውቅና ቢሰጥም ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ የሆኑ ኮሚቴዎች ተጨማሪ ሦስት ቀበሌዎች እንዲካተቱ በመጠየቅ ችግሩ እንዲፈጠር ሰበብ እያደረጉ መሆናቸውን
አስታውቀዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊው ‹‹ለሰላም መደፍረስ ሰበብ የሚደረጉት ቀበሌዎች ወደ ቅማንት አስተዳደር እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ የመልክአ ምድር ትስስር የላቸውም፤ በመልክአ ምድር ያልተያያዙ አካባቢዎችን በአንድ አስተዳደር ማካተትን ደግሞ የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥትም የዓለም ልምድም አያሳይም›› ብለዋል፡፡

እስከ ትላንት እኩለ ቀን ድረስ ባለ መረጃ በቅማንት ሰበብ የተደራጁ ቡድኖች በጥቅም በመደለልና ከሌላ አካል ተልዕኮ በመቀበል ከሰሞኑ በቀሰቀሱት አለመረጋጋት በጭልጋ አካባቢ በሰባት ቀበሌዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤የሰው ህይወትም ጠፍቷል፡፡

የፀጥታ ችግሩን ለመቆጣጠር በአቅራቢያ ከሚገኘው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑ ታውቋል፡፡ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ማዕከላዊ ጎንደር ላይ ከሀገር ሺማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ለመወያዬት መታቀዱንም ጀኔራል አሳምነው ገልጸዋል፡፡

እንደ ቢሮ ኃላፊው መረጃ በማሰልጠኛ ማዕከልነት ሲያገለግሉ የቆዩትን ቀበሌዎች ወደ መንግሥት መዋቅር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያነጋገራቸው የጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ትላንትም በአንዳንድ ቀበሌዎች ግጭት ተከስቶ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው #የሰላም_መድረክ የአማራ ክልል ሰላም ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ጄነራል #አሳምነው_ጽጌ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጄኔራሉ ‹‹ከየትኛውም ወገን ያሉ አጥፊዎች #ዘርን_ሳያማክል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡›› ቅማንት እና አማራን ሽፋን አድርጎ ግጭትን ሲያነሳሳ የነበረ ማንኛውም አካልም ስርዓት እንዲይዝ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠው ህዝብ፤ አጥፊዎችን በመለየትና በማጋለጥ አንድነቱን ማጠናከር እንጂ መፍትሄውን ከሌላ አካል መሻት የለበትም ነው ያሉት፡፡

የአካባቢውን ሰላም የሚጠብቀው ህብረተሰቡ መሆኑን በመገንዝብ ይህን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ወጣቶች እና አርሶ አደሮችም ሰላምና አካባቢውን ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም እንዲያገኙ የክልሉ ሰላም ደህንነት ቢሮ ይሰራል፡፡

የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈታሉ፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ለሚፈጠሩ የብጥብጥ አጀንዳዎች መጠቀሚያ ላለመሆን ነቅቶ እና እየተናበቡ መንቀሳቀስ ይገባል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፡፡

ውይይቱም በዕለቱ ምክክር ላይ የተነሱ ሀሳቦችን የሚያጠናክሩ ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ ክልል‼️

የአማራ ክልል ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ነቅተው በመጠበቅ በሃገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ #ስኬታማነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አስገነዘቡ።

የቢሮው ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል #አሳምነው__ጽጌ ትናንት ከወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለፁት በአገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማነት የወጣቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት አማራው በክልሉ ውስጥም ሆነ በሌሎች ክልሎች ማንነቱን መሰረት ያደረጉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፀሙበት መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ሊያረጋግጥ የሚችል የለውጥ ብርሃን እየታየ ቢሆንም ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት ለውጡን ወደ ኋላ ለመመለስ እየተንቀሳሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

Via~አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ

"በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት #በአንድ መንደር 200 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 2 ሺ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ 55 ሰዎች ሞተዋል፡፡"
.
.

"ከሌላ አካባቢ መጥተው #በግጭት ሲሳተፉ የነበሩና የሞቱ ሶስት ሰዎች መኖራቸውን መታወቂያቸውን በመመልከት #አረጋግጠናል፡፡"
.
.

"ጥፋት #ለመፈጸም የተደራጀው ኃይል ለጊዜው #ተገቷል፤ የታጠቁ ኃይሎች በመሸጉበት ስፍራ ተደምስሰዋል፡፡ በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ አካባቢና በጎረቤት ክልልም ሕገወጥ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በቅርብ ርቀት አሉ። የእኛን እርምጃ ወስደናል፡፡ የቀረውንም ከሚመለከታቸው ጋር #መፍትሄ ለመስጠት በቅንጅት እየሰራን ነው፡፡"

©አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ግድያውን ብርጋዴር ጄኔራል #አሳምነው ጽጌ ብቻውን መርቶታል ማለት ከባድ ነው›› አምሳል ጌትነት ከበደ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞ ፖለቲከኛ
.
.
አቶ አምሳል፡- "አምባቸው እንዲህ በአጭር ጊዜና ባልተጠበቀ ሁኔታ ይገደላል ወይም ይሞታል ብዬ አልገመትኩም፡፡ ይሁንና የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሁኔታ ግን አይጥመኝም ነበር፡፡ አምባቸውን፣ እዘዝን ወይም ምግባሩን ይገድላቸዋል የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡"

ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢንጂነር አምሳል ጌትነት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ👇
https://telegra.ph/BGAT-07-21