TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው " - አቶ ከበደ አሰፋ

የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ፣ በመቐለ ዙሪያ ስለሚስተዋለው፦
* የመሬት ሊዝ ሁኔታ፣
* ስለወልቃይትና ራያ ተፈናቃዮች፣
* ስለፕሪቶሪያው ስምምነት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አቶ ከበደ በመቐለ ዙሪያ የመሬት ጉዳይ ምን አሉ?

70 እንደርታ ውስጥ፣ እንደ አጠቃላይ መቐለና ዙሪያው ያለውን የመሬት ወረራ በልዩ ሁኔታ እንቃወማለን። ይሄ የመሬት ፓሊሲ አርሶአደሩን የሚያደኸይ ነው። ይሄም በተጨባጭ እየታዩ ነው።

የስርዓቱ ሰዎች ከአርሶ አደሩ መሬቱን በጉልበት ይቀማሉ። ለሚፈልጉት ባለሃብት ያቀርባሉ። ከባለሃብቱ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የመሬት ፓሊሲ የኪራይ ስብሳቢነት፣ የሙስና ምንጭ ነው።

በሊዝ ስም መሬት በካሬ በ85,000 ብር ይገዛሉ። ይህን 20፣ 30 ፐርሰንት እየከፈሉ ይወስዳሉ። ይሄ ገንዘብ ከሕዝቡ በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደ ነው። የሕዝብ ሀብት ዘረፉ፣ መልሰው የድሃውን መሬት በመግዛት ሕጋዊ እያደረጉ ነው ያሉት። ምንጩ ግን ሕገ ወጥ ነው። ጭቆናው ድርብ ነው።

ባለን መረጀ መሠረት 1867 አካባቢ መሬት የመጀመሪያው ሊዝ ተዘጋጅቷል፣ በመቐለ ዙሪያ ለምሳሌ ስራዋት፣ እግረወንበር…ብዙ ናቸው። 

ያካተቷቸው አንሷቸው ተጨማሪ 13 ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ መቐለ አካተው፣ የእንደርታ ህዝብን መሬት ሸጠው ለመበልጸግ ዝግጅት ላይ ናቸው።

ስለተፈናቃዮች ምን አሉ ?

የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከምንም ነገር በላይ ለወልቃይትም ሆነ ለራያ ሕዝብም መታሰብ አለበት። ማዶና ማዶ ባሉ ሊህቃን ምክነያት ይህን ሕዝብ የጦር ሜዳ እየሆነ ነው። እየተፈናቀለ፣ የገፈቱ ቀማሽ እየሆነ ያለው ይሄ ሕዝብ ነው።

ስለኘሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ?

- ትግራይ ውስጥ እስቲል #ታጣቂዎች ትጥቃቸውን #አልፈቱም። እኛ መፍታት አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለን። ለምን ዓላማ ነው ከነመሳሪያቸው እስካሁን የሚቆዩት ? ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም።

- ኢትዮጵያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መከላከያ ሠራዊት ነው። ከዛ በመለስ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ይፍቱ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አንዱ ይህ ነው። 

- ለምን እንደተቀመጡ አናውቅም ስጋት አለን።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia