TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጉዳት አድራሿ ጦጣ በአ/አ⬇️

ከአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ አምልጣ ወጥታ በአካባቢው ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰችዋ ጦጣ እስከ አሁን አለመያዟ እንዳሳሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተማሪ ነቢዩ ኢሳኢያስ በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ አንድ ነዋሪ ነው፡፡ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ በአቅራቢያው ወዳለ ሱቅ በማምራት ላይ ሳለ ጦጣዋ ከኋላው ዘላ እግሩን ነክሳው ጉዳት አድርሳበት አምልጣለች፡፡

በግል ስራ እንደሚተዳደር ወጣት ድልነሳው ይገዙ እንደተናገረው ደግሞ ወደ ስራ ለመሄድ ፊቱ በመታጠብ ላይ ሳለ ይሕችው ጦጣ ከኋላው በኩል እግሩን ነክሳ #ከፍተኛ የሚባል ጉዳት አድርሳበታለች፡፡ በጦጣዋ ከፍተኛ ጉዳት በማስተናገዱ መንቀሳቀስ እንደማይችል የገልጿል። ወጣት ድልነሳው በመሃል ከተማ ከሚገኝ ፓርክ እንስሳት በዚህ መልኩ ማምለጥ መቻላቸው #አሳሳቢ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የልጆችን ጩኸት ሰምቶ ወደ ውጪ በወጣበት ጊዜ ከጦጣዋ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጠው ህጻን አቤኔዘር አጥናፉ ራሱን ለማዳን የግቢውን በር ቢዘጋም በአጥር ዘልላ ታፋውን እንደነከሰቸው ነው ተናግሯል፡፡

የወላጅ አቤኔዘር እናት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ተክሌ ለኢዜአ እንዳሉት ፓርኩ የእንስሳት ማቆያ እንደመሆኑ መጠን በቂ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባ ነበር፡፡ የጦጣዋ አለመያዝ #አሁንም ድረስ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

የስድስት ዓመት ህጻን ልጃቸው በጦጣዋ ጉዳት እንደረሰበት የተናገሩት ወይዘሮ አጃይባ ዋባ በበኩላቸው ልጃቸውን ለማሳከም 3 ሺህ 500 ብር ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላዋ የአካባቢው ነዋሪ ወይዘሪት ሶፊያ አወል እንዳለችው ሰዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በላይ የጦጣዋ ጤንነት አሳስቧታል፡፡

ተቋሙ መሰል እንስሳት አምልጠው ከዚህም የባሰ ጉዳት እንዳያደርሱ የጥበቃ ስራውን ሊያጠናክር እንደሚገባም ጠቁማለች፡፡

የአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ አስተባባሪ አቶ ይርጋለም አያሌው ጦጣዋ የማደሪያዋን ኮርኔስ ገንጥላ ማምለጧን ገልጸው ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት ቢደረግም አለመሳካቱን አምነዋል፡፡

አሁንም ዳርት /ማደንዘዣ/ በመጠቀም ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያብራሩት አስተባባሪው ካልተሳካ ሌሎች አማራጮችን እንደሚጠቀሙ አረጋግጠዋል፡፡

ፓርኩ በሚቀርብለት ደረሰኝ መሰረት ተጎጂዎች ያወጡትን ወጪ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተዘጋው መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተከፈተም‼️

በተቃውሞ ሳቢያ የተዘጋው የአዲስ አበባ፤ አዋሽ ጅቡቲ መንገድ ዛሬም ሙሉ በሙሉ #አልተከፈተም። ወደ #ጅቡቲ የሚያመራው እና የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ የደም ሥር እንደሆነ የሚነገርለት የመኪና መንገድ አዋሽ ሰባት ከተማ ላይ ዛሬም ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪ ለDW አረጋግጠዋል።

ተቃዋሚዎች ከትናንት ጀምሮ ዋናው መንገድ ከሚያልፍባት የአዋሽ ከተማ መውጪ እና መግቢያዎች እንደዘጉ መሆናቸውን የዐይን እማኙ ተናግረዋል።

በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዋሽ ነዋሪ "መንገዱ አልተከፈተም፤ ምንም የሚንቀሳቀስ ነገር የለም" ብለዋል።

በሎጊያ አካባቢ የሚገኘው የመንገዱ ክፍል ግን በዛሬው ዕለት ተከፍቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል። ትናንት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት መንገድ ላይ ማደራቸውን ለDW የገለጹት አሽከርካሪ ዛሬ ወደ ሎጊያ ከተማ ለመግባት መቻላቸውን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ላይ ስለመሆኑ መረጃ እንደደረሳቸው የገለጹት የከባድ መኪና አሽከርካሪ "ሕዝቡ ለሰባት ቀን ጊዜ ሰጥቶ አሁን መኪና መንቀሳቀስ ጀምሯል። በሰባት ቀናት ውስጥ ጥያቄያችን ካልተመለሰ #አሁንም_እንዘጋለን ብለዋል" ሲሉ ኹኔታውን አስረድተዋል።

በአዋሽ ሰባት የሚኖሩት ነጋዴ ግን የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ክፍኛ ያስተጓጎለው የመንገድ መዘጋት "እስከ ነገው ዕለት ይቀጥላል" የሚል መረጃ ደርሷቸዋል። "ሶስት ቀን እያሉ ነው። ነገንም ይጨምራል መሰለኝ" ያሉት የአዋሽ ሰባት ነዋሪ ከመንግሥት መፍትሔ ካልተገኘ ሊከፈት እንደማችል በተቃውሞው የተካፈሉ ሲዝቱ መስማታቸውን ለDW አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይርጋለም #ሞረቾ #አገረሰላም~የፀጥታ ሁኔታ!

ትናንት ግጭት እና ተቃውሞ በታየባት ሐዋሳ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንደሚታይ የጀርመን ራድዮ ገለፀ። የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ እንደገለፀዉ ከሐዋሳ ውጪ በሞሮቾ፣ ይርጋለም እና አገረሰላም በተባሉት ከተሞች #አሁንም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንዳሉ የዓይን እማኞች ሰቅሶ ዘግቧል። በሞሮቾ የሚገኝ አንድ የዓይን እማኝ እንዳለው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በነበራቸው ግጭት «የሚያውቃቸው ወጣቶች #ሞተዋል። መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮች #ተዘግተዋል። ከሐዋሳ በዲላ በኩል ወደ ሞያሌ እና ኬንያ የሚወስደውም መንገድ ተዘግቷል።» አገረሠላም የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደገለፁት ደግሞ «ትናንትና ሰዎች ሞተዋል። ወጣቶች ቤት #አቃጥለዋል።» በከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ዛሬ ላይ መጠነኛ መረጋጋት ይታያል። «ሆኖም ከተማዋ ውስጥ ዛሬም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል።» የሲዳማ ዞን ፖሊስ በሐዋሳ አጎራባች አካባቢዎች አሁንም አለመረጋጋት መኖሩን ለ ጀርመን ራድዮ አረጋግጧል። በሲዳማ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩትን አለመረጋጋቶች ተከትሎ ደረሰ ስለተባለዉ ጉዳት ግን ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_19_Feb_2022.png
#SituationReport :

#Tigray #Amhara #Afar📍

የሰሜን ኢትዮጵያ #ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ወይም #UN_OCHA የዚህን ሳምንት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

#Afar

• በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች #አሁንም ግጭት ቀጥሏል። በዋናው ኮሪደር (A1) [አፋር ሰመራን ከመቐለ ትግራይ የሚያገናኘው] እና ትግራይ እና አፋር በሚዋሰኑባቸው ኤሬብቲ ፣ በርሀሌ እና መጋሌ ወረዳዎች ፣ በኡሩህ እና ዋህዲስ ቀበሌዎች፣ በሁሉም የኬልበቲ ዞን ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።

• በአፋር ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። መጠነ ሰፊ መፈናቀል በመኖሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

• በአፋር ክልል በተከሰተው ግጭት እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ በመጋሌ፣ በርሀሌ፣ ኮነባ፣ ኢረብቲ እና ዳሎል ወረዳዎች መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ። አካባቢዎቹ በመንገድ ሁኔታ እና በፀጥታ ስጋት ምክንያት ለሰብአዊ አጋሮች ተደራሽ አይደሉም።

#Tigray

• በትግራይ ክልል እ.ኤ.አ. የካቲት 12 በምስራቅ ዞን አፅቢ ከተማ ላይ በደረሰ የአየር ድብደባ የንፁሀን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እና ሰዎች መቁሰላቸውን ተመድ አመልክቷል። የተመድ አጋሮች እስካሁን የተጎጂዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

• በትግራይ ክልል በአብዛኛው ሰሜናዊ ክፍል [ከኤርትራ ድንበር በሚዋሰኑ ቦታዎች] የተወሰኑ ቀበሌዎች በማዕከላዊ ዞን ራማ ፣ በምስራቅ ዞን ኢሮብ፣ በምስራቅ ዞን ዛላ አምበሳ ከተማ ጨምሮ ተደራሽ አይደሉም። በእነዚያ አካባቢዎች ላለፉት ጥቂት ወራት ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ የቆዩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉ።

• እኤአ ከታህሳስ 15 አንስቶ የፀጥታ ችግሮችና ግጭቶች ወደ ትግራይ ክልል በየብስ በ #ሰመራ- #አብዓላ- #መቐለ መንገድ እርዳታ እንዳይገባ እንዳገዱ ይገኛሉ። ከታህሳስ አጋማሽ በፊት ተፈቅዶ የነበረው የአቅርቦት መጠን በዋናነት በቢሮክራሲያዊ እክል ከሚያስፈልገው በታች በመሆኑ አሁን በፀጥታ ችግር እና በግጭት መንገድ መዝጋቱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን የሰብአዊ አቅርቦት ችግር የበለጠ እንዳባባሰው ተገልጿል።

• እ.ኤ.አ. ከሀምሌ 12 አንስቶ አጠቃላይ 1,339 የጭነት መኪናዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል የገቡ ሲሆን ይህ በትግራይ ክልል ያለውን ሰፊ ​​የሆነ የሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስፈልጉት አቅርቦቶች ውስጥ 8 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ተጨማሪ 17 የጭነት መኪናዎች ባለፈው ህዳር ወር ከኮምቦልቻ ፣ አማራ ክልል ወደ ትግራይ ገብተው ነበር።

• የዓለም ጤና ድርጅት-WHO የላከው የህክምና ቁሳቁሶች መቐለ ቢደርሱም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ምክንያት በክልሉ ወዳሉ ጤና ተቋማት መላክ እና ማከፋፈል እንዳልቻሉ ተመድ ገልጿል። በተለይም ከ800 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ወዳስጠለለው የሰሜን ምእራብ ዞን ማድረስ አልተቻለም። በዞኑ ከአጠቃላይ የውስጥ ተፈናቃይ 1.8 ሚሊዮን 44 % ይሸፍናል።

• በሰሜን ምዕራብ ዞን ተፈናቃዮችን ባስጠለሉ ቦታዎች የእከክ በሽታ እና ወባ ኬዞች መጨመራቸው ተመላክቷል። ከ1,100 በላይ የእከክ በሽታ ኬዝ በ22 ሳይቶች ፣ከ1800 በላይ የወባ ኬዞች በዞኑ ከዓመቱ መጀመሪያ (የፈረንጆች) ጀምሮ ተመዝግቧል። የአቅርቦት ችግር፣ የመድሃኒትና የነዳጅ እጥረት ተመድ የጤና አጋሮቹ የበሽታዎችን ስርጭት እንዲቀንስ ለማድረግ የሚሰሩትን ስራ እየገደበ መሆኑን ገልጿል።

• ተ.መ.ድ. በትግራይ ክልል ላሉት የሰብአዊ ድጋፍ አጋሮቹ ያለው ነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና አቅርቦቶች በጣም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ይህም ሁኔታ የሰብአዊ አገልግሎቶችን በተለይም የምግብ ፣ የውሃ ፣ የጤናና የስነ - ምግብ አገልግሎቶች ስርጭትን በእጅጉ እየቀነሰው መሆኑን አመልክቷል።

#Amhara

• በአብዛኛው የአማራ ክልል በአንጻራዊ የተረጋጋ ሁኔታ ያለ ሲሆን በሰሜን ወሎ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ግን ውጥረት እንደነገሰበት ነው።

• አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያዋሱ አካባቢዎች አሁንም ባለው የፀጥታና የደህንነት ስጋት ተደራሽ አይደሉም። መድረስ አልተቻለም። ይህም በሰሜን ጎንደር፣ ዋግ ኽምራና ሰሜን ወሎ ያሉ አካባቢዎች ያካትታል። ባለው ሁኔታ ህዝቡ የአስፈላጊ የምግብ እደላ ጨምሮ አጠቃላይ ሰብአዊ ርዳታ እንዳያገኝ ሆኗል።

• በሰሜን ጎንደር ፣ ዋግ ኽምራ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ዞኖች አካባቢዎች አዲስ መፈናቀል መኖሩ ተመላክቷል።

• በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። በርካታ ሰዎች በተደጋጋሚ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በአዋሳኝ አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች ውስን የሰብዓዊ ዕርዳታ ብቻ እንዳገኙ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ በዋናነት በዝቋላ ወረዳ እና ሰቆጣ ወረዳ በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

• ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ12,000 በላይ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ራያ ቆቦ አማራ ክልል ገብተዋል።

• በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ከ21 ሺ የሚበልጡ ተመላሾች አስቸኳይ የመጠለያ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የመኖሪያ ቤታቸውን መልሶ የማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በዞኑ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶችና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የመንግስት ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia
#ሸገር

" እየፈረሱ ያሉት ቤቶች #አሁንም በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ባሉ ሃላፊዎች ይሁንታ የተሰሩ ስህተቶች መሆናቸዉን እናምናለን " ሲሉ የሸገር ከተማ ከንቲባ አስታወቁ፡፡

በቅርቡ የተቋቋመውን የሸገር ከተማ ተከትሎ በተለይ ከቤት ፈረሳ ጋር ተያይዞ በርካታ ቅሬታዎች ከመነሳታቸው ባሻገር ዜጎች በመንግስት አካላት ፍቃድ ቤቱን እንደገነቡ ቢገልጹም መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ ይገለጻል፡፡

ፍቃዱን የሰጡ የመንግስት አካላት አሁንም በሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው የዜጎች ቤት እንዲፈርስ እያደረጉ ነው የሚለው ቅሬታም በተደጋጋሚ ጊዜ ይነሳል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከአሃዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሸመ አዱኛ  ፤ ባለፈው የመንግስት መዋቅር ውስጥ በነበሩ የስራ ሃላፊዎች ስህተት ቤቶቹ እንደተሰሩ እንደሚያምኑ አስታዉቀዋል፡፡

#አሁንም እነዛ ሃላፊዎች በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለጽ ሆኖም ግን ለሰሩት ስህተት እርምጃ አለመወሰዱ ጥያቄ እያሥነሳ ቢሆንም ካለፈው ይልቅ ስለ ወደ ፊቱ በማሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለዉ መሰል ስህተቶች እንዳይደገሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ዜጎች ለሚያነሱት ጥያቄ ምንም እንኳን በከተማዋ አስተዳደር ህገ ወጥ ስለሆናችሁ ነው የሚል ምላሽ ቢሰጣቸውም #ከመንግስት_አካላት ፍቃድ አግኝተው እንደሰሩ እየገለጹ ያሉ ግን በርካቶች ናቸው፡፡

Credit : Ahadu Mederk

@tikvahethiopia
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia