TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" መንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር

የኢትዮጵየ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ባወጣው መግለጫ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት #እየተሸማቀቁ እና #እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ መታዘቡን ገልጿል።

ከሰሞኑን ፤ የማህበሩ መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ ፦
👉 ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ ፣
👉 ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ፣
👉 ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ፣
👉 ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ፣
👉 ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

አንዳንዶቹ ያሉበት ቦታ እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን ቤተሰቦቻቸውም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ እየታሰሩ፣ እየታፈኑና ቤታቸውና ቢሯቸው እየተበረበረ መሆኑ ባለሞያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ፤ የፕረስ ምህዳሩ የበለጠ እንዲጠብ እያደረገ ነው ሲል ገልጿል።

ማህበሩ የተቋቋመው እንደዚህ አይነት ሙያውን የሚያቀጭጩ ጫናዎችን ለመታገል መሆኑን በመግለፅ የመንግሥት እርምጃዎችን በፅኑ አውግዟል።

ጋዜጠኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ጉዳያቸውን እስር ቤት ሳይቆዩ መከታተል እንደሚችሉ ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቢደነገግም ይህ ግን #ተግባራዊ_አለመደረጉ ማህበሩ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር መንግስት፦
- የፕረስ ነፃነት እንዲረጋገጥ
- ያጸደቃቸውን ህገ-መንግስታዊና ዓለም አቀፋዊ ህጎች እንዲያከብርና ውስጡን እንዲፈትሽ
- ያለምንም የህግ አግባብ ያሰራቸውን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ
- ባለሙያዎች ላይ የሚያደርሰውን ማሸማቀቅ እንዲያቆም ጠይቋል።

@tikvahethiopia