TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በደምቢ ዶሎ ከተማ መንገድ ለማስከፈት በሚሞክሩ ወታደሮች #በተተኮሰ ጥይት አንድ ወጣት ተመቶ ወደ ደምቢ ዶሎ ሆስፒታል መወሰዱ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዛሬ በደምቢዶሎ ከተማ ካልታወቁ ሰዎች #በተተኮሰ ጥይት የዞኑ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ መቁሰላቸውን የዞኑ የአስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ እንደተናገሩት ከተወሰኑ ቀናት በፊትም ኃዋ ገላን ወረዳ ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ መረጃ አላቸው። በትናንትናው ዕለትም በወለጋ ዩኒቨርስቲ በነበረ አለመረጋጋት ከተጎዱ አስር ተማሪዎች መካከል የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን የዩኒቨርስቲው ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አሰፋ ነገሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ‼️

የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ እሁድ ታህሳስ 14/2011ዓ.ም ከምሸቱ 2:30 ሰዓት አካባቢ በጥበቃ ሰራተኛ #በተተኮሰ ጥይት ተማሪ ዩሴፍ ገ/መስቀል ህይወቱ ያለፈ ሲሆን አንድ ተማሪ ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶበታል፤ በዚህም ምክንያት የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎችና ማህበረሰብ ትላንት ሰኞ ጧት ሃዘናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ተማሪዎቹ ^ወንጀለኛዉ ግለሰብ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ በሰላማዊ መንገድ የጠየቁ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ አመራረም ተማሪዎቹን አወያይቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻዉ ለተፈጠረዉ ችግር የተሰማቸዉን ኃዘን ገልጸዉ ወንጀለኛዉ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ ዩኒቨርሲቲዉ የበኩሉን እየሰራ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

ተማሪ ዩሴፍ የአምስተኛ አመት የመካኒካል ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን የቀብር ስነ-ስርዓቱ በትውልድ ቦታው ደቡብ ጎንደር ዞን ሃሙሲት ተፈጽሟል፡፡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እየተመኘ በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

የመቁሰል ጉዳት የደረሰበት ሌላዉ ተማሪ የሁለተኛ ዓመት የእጽዋት ሳይንስ ተማሪ ሲሆን አሁን በህክምና ላይ የሚገኝና ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲዉ ትላንት ከሰዓት በኋላ ያለዉ ሁኔታ ሰላማዊና የተረጋጋ ሲሆን ከዚህ የተለየ የሚሰጡ አስተያየቶችም ከእዉነት የራቀ መሆኑን ዩኒቨርስዉ ይገልጻል።

ምንጭ፦ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ‼️
----------------------
በተማሪ ዩሴፍ ገ/መስቀል ሞት ምክንያት የደብረ ታብር ዩኒቨርስቲ የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ይገልፃል፡፡

ተማሪ #ዩሴፍ የአምስተኛ አመት የመካኒካል ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 14/2011ዓ.ም ከምሸቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በጥበቃ ሰራተኛ #በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እየተመኘ በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ዩኒቨርስቲው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ አትክልት ተራ አካባቢ አንድ የ20 ዓመት ወጣት ከፖሊስ #በተተኮሰ ጥይት #መሞቱ ተገለጸ። የ20 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት ጅብሪል አህመድ በአትክልት ተራ አካባቢ የተለያዩ አትክሎትችን በመቸርቸር ስራ ህይወቱን ይመራ እንደነበር ኢትዮ ኤፍ ኤም በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አረጋግጫለሁ ብሏል። እናቱን በቅርቡ በሞት በማጣቱ ምክንያት ታናናሾቹን አንድ ወንድምና እህቱን ከዚሁ ስራ በሚያገኘው ገቢም ያስተዳደር ነበር። ይሁንና በትናንትናው ዕለት ጧት ላይ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ።

በሁለቱ ግገለሰቦች ምክንያት በአካባቢው የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች እንደመጡ በወጣት ጅብሪል አህመድ ላይ ሶስት ጥይት ተኩሰው እንደገደሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ወጣት ጅብሪል ወዲያውኑ ወደ አቤት ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። የሟች አስከሬንም ዛሬ ለአካባቢው ነዋሪዎች በመሰጠቱ ስርዓተ ቀብሩ በኮልፌ ሙስሊም መቃብር አካባቢ ተፈጽሟል። ፖሊስ ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ ጥይት መተኮሱም በተለይም በስፍራው የነበሩ ሰዎችን አስቆጥቷል።

ነዋሪዎቹ እንዳሉት ፖሊስ ጉዳዩን ሳያጣራ ነው ልጁ ላይ የተኮሰበት፣ መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በካናዳ ሀገር የቅርብ ጓደኛውን በመግደል የተጠረጠረው የ26 ዓመቱ ግለሰብ በአየር ትራንስፖርት ወደ #ኢትዮጵያ ማምለጡን የካናዳ ሃሚልተን ፖሊሰ አስታወቀ። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ኢብራሂም ኢሳክ ሁሴን የተባለው ግለሰብ፣ ከቶርንቶ ወደ ኢትዮጵያ ማምለጡን ተረጋግጧል ያለው ፖሊስ፣ የ29 ዓመቱን ኦብሳ ጁነዲ የተባለውን የቅርብ ጓደኛውን በመግደል መጠርጠሩ ታውቋል።

ሟች በጭንቅላቱ ላይ #በተተኮሰ_ጥይት የሞተ ሲሆን ወዲያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ከግድያው 20 ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል አለመግባባቶች እንደነበሩ ማስረጃዎች አሉኝ ያለ ሲሆን ይህንንም በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች ማረጋገጡን ገልጿል።

የአለመግባባቱ ምንጭ ምን እንደሆነ ባይረጋገጥም ፓሊስ ባደረገው ፍተሻ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት አደንዛዥ ዕፅ መገኘቱን ይፋ አድርጓል። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው #ካናዳዊው ግለሰብ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ቢሆንም ለምን ወደ ኢትዮጵያ ሊያመልጥ እንደቻለ አልታወቀም። ተጠርጣሪው ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት መሆኑንም ፖሊሰ ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሏቸው ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ…
#AmharaRegion

ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ተገደሉ።

የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

ወ/ሮ ሚሊሹ በዛሬው እለት ነው የተገደሉት።

እንደ ወረዳው መረጃ ፥ የመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ውለው ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የተገደሉት።

ግድያ የተፈጸመባቸው አመራሯ በእናትነት ላይ ነፍሰ ጡርነትን ይዘው እንደነበር ተገልጿል።

የወረዳው አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ " ግድያው የተፈጸመው በጽንፈኛ አካላት #በተተኮሰ ጥይት ነው "  ብሏል።

ከቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ አልብስ አደፍራሽ #በታጣቂዎች_መገደላቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ #የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ ነው የተሰማው።

ጥቃቱ አነጣጥሮባቸው ነበር ከተባሉት ውስጥ፦

➡️ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ

➡️ የወልዲያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ይገኙበታል።

መኖሪያ ቤታቸው ላይ ነበር ጥቃት የተፈጸመው።

ከዚህም ባለፈ የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

" #ባልታወቁ_አካላት " ተፈጽሟል በተባሉት ጥቃቶች በባለስልጣናቱ ላይ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጉባ ላፍቶ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ተነግሯል።

ባለፈው #ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia
#BBCAmharic

@tikvahethiopia