TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። ከዚህ ቀደም አቶ ፍፁም አረጋ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ሀላፊነታቸው ሊነሱ እንደሆነ መረጃ አቅርበን ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጠቅላይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩትን አቶ #ፍጹም_አረጋን -- አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ ተክተዋቸዋል። አቶ ሽመልስ የኦዴፓ እና ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባል ናቸው። በያኔው ኦህዴድ አሁን ኦዴፓ በሚባለው ፓርቲ ውስጥ አሁን ለተገኘው ለውጥ #ህይወታቸውን ቤዛ ለማድረግ ቆርጠው በተግባር ከተራመዱ አመራሮች አንዱ ናቸው።

©ተስፋዬ አለነ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሁነው ተሾሙ፡፡ ጨፌ ኦሮሚያ ዘሬ ከሰአት ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ የሾመው፡፡ አቶ ሽመልስ በጨፌው ፊት ቆመው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት የተሾሙት አቶ ሽመልስ የርእሰ መስተዳድርነት ስራውን ጨምረው እንደሚሰሩ ተነግሯል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሽመልስና አቶ አዲሱ🛫ደንቢዶሎ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ እና የኦሮሞ ዴክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ #አዲሱ_አረጋ ከደንቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ዛሬ ወደ #ደንቢዶሎ አቅንተዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ለ7 ሺህ 29 የህግ ታራሚዎች #ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ አስታወቁ፡፡ በክልሉ መንግስት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በቆይታቸው መልካም ባህሪ ያሳዩ መሆናቸው ጉዳዩን የሚመለከተው ቦርድ እንዳረጋገጠ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ይቅርታው በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በዘር ጭፍጨፋ፣ በደን ጭፍጨፋ እና በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥቃት የፈፀሙ አካላትን እንደማይመለከት ነው የተነገረው። ማህበረሰቡም ይቅርታ የተደረገላቸው ሰዎች ከማረሚያ ቤት ውጭ ያለውን ህይወት እስከሚላመዱ ድረስ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የህግ ታራሚዎችም ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ በስራ ለመካስ መስራት እንደሚገባቸው ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት። ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎችም ከዛሬ ጀምሮም ህብረተሰቡን መቀላቀል ይጀምራሉ።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ ገለጹ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ከጅማ ዞንና እና ከጅማ ከተማ አስተዳድር ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።

በውይይት መድረኩ በመልካም አስተዳደር፣በልማትና ተጠቃሚነት ላይ ለተነሱ ጥያቄች አቶ ሽመልስ አብዲሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም መንግስት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ከአመራሩ ጎን በመቆም በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የተገኘውን ሰላም፣ መረጋጋትና ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሰሩ ሃይሎችን በጋራ በመከላከል የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ማሳካት እንደሚገባም ማንሳታቸው ተዘግቧል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

"#የሁላችንም የሆነች #ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቀን ከሌት እንሰራለን" የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በዩኒቨርስቲ የሚታዩ በዘርኝነት የሚከሰቱ መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም" አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢሬቻ በዓል ከግል ፍላጎታችን በላይ ነው!" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኢሬቻ በዓልን ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በጋራ ማክበር ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ድል ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ በዛሬው እለት የ2012 የኢሬቻ በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-5

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia